🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰3️⃣1️⃣
ይገባኛል ልዑሌ ግን በቃ አባት ሆነሀል ።
ደስ ስላለህ ደስ ብሎኛል ።
እውነት ለመናገር በጣም ደስ እንደሚልህ ገምቼ ነበር ግን በዚህ ልክ የሚሆን አልመሰለኝም የኔ አባት እንኳን ደስ አለህ አልኩት።
ሰላሜ በጣም እወድሻለሀ ይሄ ለኔ እንደ አዲስ የመወለድ ያህል ነው በጣም አመሰግንሻለሁ እንደ አዲስ ለመኖር እንድጓጓ ስላደረግሽኝ አለ
አረ ልዑሌ አንተ ለኔ ያደረከው መልካም ነገር መልሶ እየከፈለህ ነው ያለው ደሞኮ ይሄ ገና የመጀመሪያችን ነው ገና ደርዘን ነው ምወልድልህ ብዬ አቀፍኩት በቃ አረፍ እንበል እኔም ደክሞኛል አልኩት ።
አንቺ ተኚ እኔ እቆያለሁ አለኝ እንዴ ለምን እረፍት አድርግ እንጂ ወዴት ነው ምትቆየው ብዬ ስጠይቀው አይ ሰላሜ በዚህ ሁኔታ እንቅልፌ አይመጣም ተኚ አለ ።
እሺ በቃ አላስጨንቅህ ብዬው እኔ ዝም ብዬ ተኛሁ።
ሌሊት 8 ሰአት አካባቢ ከእንቅልፌ መጥፎ ህልም አይቼ ብንን ብዬ ተነሳሁ ልዑሌ ከጎኔ አልነበረም።
ተነስቼ ወደ ሳሎን ሄድኩኝ ሶፋ ላይ ጉልበቱን አቅፎ ቁጭ ብሎ እያለቀሰ ነበር ሳየው ደነገጥኩ እንዴ ልዑሌ ምን ሆነሀል በፈጠረኽ አምላክ አይንህን አይተኸዋል ሰው የሞተብህኮ ነው ሚመስለው እእእ ሁሉም ነገርኮ ልክ አለው ቆይ ምንድነው እንደዚህ ስሜትህን የነካው አባት መሆንህ ብቻ ነው ወይስ ሌላም ነገር አለ ግራ ተጋብተህ ግራ አታጋባኝ እኔ ስትዘል ስትፈነድቅ ከጣራ በላይ ስትስቅ ማየት ነው ምፈልገው አልኩት ።
እሺ ሰላም አንዳንዴ በቃ አይሆንም አይደረግም ብለሽ ያመንሽው ነገር ድንገት ሆኖ ስታገኚው ቆይ ባንዴ እሺ ብለሽ ትቀበያለሽ ሰላም እኔኮ አደለም ሚስት ማግባት አደለም የልጅ አባት መሆን ይቅርና ሴትን ልጅ ቀርቤ የማውራት ፍላጎትም ሀሳብም ያልነበረኝ ሰው ነኝ እእ ድንገት ቤት የምትጠብቀኝ ሚስት አባዬ ብለው ሚጠሩኝ ልጆችን ሳገኝ ምን እንደሚሰማኝ ገምቺ እስኪ እእእ ......
እሺ በቃ ልክ ነህ አሁን ና ወደክፍላችን እንግባ ባባ ብቻውን ነው የተኛው ብዬ ይዤው ገባሁ በነጋታውም ወደቢሮ ሳይገባ ቤት ዋለ ከራሱጋ አልነበረም ማለት ይቻላል ከደስታው በላይ ያስጨነቀው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው ።
ብቻ ልዑሌ እርግዝናዬን ከነገርኩት ቀን ጀምሮ ቶሎ ሆድ ሚብሰው ነገር አለ ።
የትኛውም ነገር ላይ ስለ ልጅ ስናወራ እንባ ይቀድመዋል አንዳንዴ በእጁ የያዘውን እቃ እንደ አዲስ ይፈልጋል::
ይኼኛው እርግዝናዬ እንደመጀመሪያው አደለም በጣም ከባድ ነው የበላሁት ነገር ሆዴ ውስጥ አይቀመጥም እንደዛ ምወደው ቡና ገና ሲሸተኝ ያቅለሸልሸኛል በፍቅር እወዳቸው የነበሩትን ምግቦች አንዳቸውንም አልጠቀምም ::
በቃ ሰውነቴ በየቀኑ ቅይይር ይላል ::
እናቴጋ ከሄድን ስለቆየን እሁድ ቀን እናቴም ጠፋችሁ እያለችኝ ስለነበር ሄድን እንደተለመደው እዛ ስንጫወት ቤቱን ስናደምቀው ዋልን በየመሀሉ እያመመኝ ወደውጪ እየወጣሁ ነበር ማታ አካባቢ ወደቤታችን ለመሄድ ተነሳን እናቴ በሩን አስወጥታን ተመልሳ ገባች።
መሲ ባባን አቅፋ እኔና ልዑሌ ደሞ እጅ ለእጅ ተያይዘን እያወራን እየተሳሳቅን መኪናውጋ ደረስን ልዑሌ እኔንም መሲንም በሩን ከፍቶ ካስገባን ቡሀላ እኔ ስልኬን እረስቼው ስለወጣሁ ተመልሶ ሄደ ::
መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን ከመሲጋ ስለሰፈራችን እየነገርኳት ማክቤል በፍጥነት እየተራመደ ከፊት ለፊታችን ትንሽ እራቅ ብሎ አስፋልት ሲሻገር አየሁት አስፋልቱን ተሻግሮ ቆሞ ሚጠብቀው መኪና ነበር አይኔን ማመን አስኪያቅተኝ ድረስ እሱ አልመስልሽ አለኝ።
ማክቤል በህይወቱ የጨርቅ ሱሪ እና ሱፍ ሚባል ነገር አይወድም ነበር ።
ዛሬ ግን አለባበሱ ቢሮ የሚውል በጣም ትልቅ ድርጅት አስተዳዳሪ ነገር ነው ሚመስለው ፂሙን ፀጉሩን ተስተካክሎ አማላይ ሆኗል አረማመዱ ሁላ ልክ ቢዚ እንደሆነ የስራ ሰው ነበር ሳየው ወሬዬን አቋርጬ አፈን ከፍቼ እያስተዋልኩት ወደመኪናው ውስጥ ገብቶ በፍጥነት መኪናው ከዛ አካባቢ ተሰወረ ።
እውነት ለመናገር ገረመኝ እንዲ በዚህ ፍጥነት መቀየሩ ጥያቄ ሆነብኝ ።
ልዑሌ አትዝረክረኪ እሺ እቃሽን የትም እያጋደምሽ እኔን አታልፊኝ ብሎ እየሳቀ ስልኬን ሰጠኝ ተቀበልኩትና ወዲያው ለማክቤል አምሮብሀል እንዲህ ተለውጠህ በማዬቴ ደስ ብሎኛል ኩል ሆነሀል አልኩት ።
ምንም አልመለሰልኝም ከልዑሌጋ እያወራን እየሄድን አስሬ ስልኬን አያለሁ መልስ የለም ።
ወደቤታችን ከደረስን ቡሀላ ልብሳችንን ቀያይረን ባባም ቀን ሙሉ አንዴ እናቴ አንዴ እህት ሲቀባበሉት ደክሞት ስለነበር እንቅልፍ ተኝቶልን ስለነበር እኛም አረፍ አልን::
ማታ 2 ሰአት አካባቢ text ገባልኝ ማክቤል ነበረ አመሰግናለሁ🙏 ብቻ ነበር ያለኝ ።
እውነት ለመናገር ልጁን ካሳየሁት ቡሀላ ከበፊቱ የበለጠ እኔን ማስቸገር ልጄን ልየው እያለ መጨቅጨቅ እንጂ እንዲህ ድራሽ አባቱ መጥፋት ነበረበት እንዴ ቆይ ምን አስቦ ነው ከረሴጋ እያወራሁ እንቅልፍ ጣለኝ ::
ሌሊት ላይ ባባ ተነስቶ እያለቀሰ ነበር አባብዬ አስተኛሁት እኔ ግን ተመልሶ መተኛት ከበደኝ ።
🔻ክፍል ሰላሳ ሁለት ነገ ማታ 3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💗የፍቅር ማእበል💗