የፈሪ ፍቅር .. . . .
በተኮላተፈ ፥ ስርዝ ድልዝ ድምፆች፣
ሲለማመድ ከርሞ ፥ ካንደበቱ ገፆች።
ደፈር ብሎ ልቤ ፥ ላይነግራት መውደዱን፣
ቃላት ያማርጣል ፥ እያሰባት ውዱን።
ተስፋ አፈር በላው ፥ ተስባብሯል መቅኔው፣
ፍራት ሰንጥቆታል ፥ ውስጡ ሲሸሽ ወኔው።
እንኳን አንገት አቅፎ ፥ እቤቷ ሊሸኛት፣
ከንፈር እየሳመ ፥ ባ'ንድ አልጋ ሊተኛት።
ስንት ጊዜ ጥሮ ፥ ወግ ደርሶት ሊያገኛት
የቁም ቅዠት ሆኖ ፥ ቀረ እንደተመኛት።
ባ'አንድ ቀን ለሊት ፥ ያየዋት በደና፣
ህልሜ ነበረች ፥ ገሀድ ያለች መና።
ልብ የሌለው ወዶ ፥ ለመግለፅ ሲዳፈር፣
መሽኮርመሙ ቀርቶ ፥ ቀና ሲል አይናፋር።
አንደበት ሲገራ ፥ ልቧን አርጎ ፈራጅ፣
ቀን እየቆጠረ ፥ እራሱን ሲያዘጋጅ ።
ከዛሬ ነገ ቀጥሮ ፥ ሊነግራት እያለ፣
አንዱ ጠልፎ ጥሏት ፥ ይዟት ኮበለለ።
ውሀ በላው ቅስሙን ፥ ሀሞቱ እረገፈ፣
በእምባ ተጨማልቆ ፥ በፀፀት አለፈ።
ሀዘን አጠላበት ፥ ብሶት ቤቱን ሰራ፣
ነፍሱ ነዶ ጋየ ፥ እብደት ስሙን ጠራ።
እናም እንዲህ አለ. . . .
ለጎኔ ማክዳ ፥ የዘላለም ቅምሻ፣
ስመኛት ዘመኔን ፥ ለህይወቴ ማምሻ።
ፍርሃት ልቤን አስሮ ፥ ጊዜ እየጠየቀኝ፣
ህልሜን አሰርቆ ፥ ባዶ እጁን ጠበቀኝ።
ገጣሚ፦ keyso✍
@getembate
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
በተኮላተፈ ፥ ስርዝ ድልዝ ድምፆች፣
ሲለማመድ ከርሞ ፥ ካንደበቱ ገፆች።
ደፈር ብሎ ልቤ ፥ ላይነግራት መውደዱን፣
ቃላት ያማርጣል ፥ እያሰባት ውዱን።
ተስፋ አፈር በላው ፥ ተስባብሯል መቅኔው፣
ፍራት ሰንጥቆታል ፥ ውስጡ ሲሸሽ ወኔው።
እንኳን አንገት አቅፎ ፥ እቤቷ ሊሸኛት፣
ከንፈር እየሳመ ፥ ባ'ንድ አልጋ ሊተኛት።
ስንት ጊዜ ጥሮ ፥ ወግ ደርሶት ሊያገኛት
የቁም ቅዠት ሆኖ ፥ ቀረ እንደተመኛት።
ባ'አንድ ቀን ለሊት ፥ ያየዋት በደና፣
ህልሜ ነበረች ፥ ገሀድ ያለች መና።
ልብ የሌለው ወዶ ፥ ለመግለፅ ሲዳፈር፣
መሽኮርመሙ ቀርቶ ፥ ቀና ሲል አይናፋር።
አንደበት ሲገራ ፥ ልቧን አርጎ ፈራጅ፣
ቀን እየቆጠረ ፥ እራሱን ሲያዘጋጅ ።
ከዛሬ ነገ ቀጥሮ ፥ ሊነግራት እያለ፣
አንዱ ጠልፎ ጥሏት ፥ ይዟት ኮበለለ።
ውሀ በላው ቅስሙን ፥ ሀሞቱ እረገፈ፣
በእምባ ተጨማልቆ ፥ በፀፀት አለፈ።
ሀዘን አጠላበት ፥ ብሶት ቤቱን ሰራ፣
ነፍሱ ነዶ ጋየ ፥ እብደት ስሙን ጠራ።
እናም እንዲህ አለ. . . .
ለጎኔ ማክዳ ፥ የዘላለም ቅምሻ፣
ስመኛት ዘመኔን ፥ ለህይወቴ ማምሻ።
ፍርሃት ልቤን አስሮ ፥ ጊዜ እየጠየቀኝ፣
ህልሜን አሰርቆ ፥ ባዶ እጁን ጠበቀኝ።
ገጣሚ፦ keyso✍
@getembate
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA