ማክሰኞ 15/04/17
የሁለተኛ ዮሐንስ መልዕክት ( ክፍል 02 )
እውነትና የፍቅር ቁርኝት
2ኛ ዮሐ 1-3
ዮሐንስ ከጌታ ሐዋርያት መካከል የፍቅር ሐዋርያ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ወንጌሉን ሲጽፍም ኢየሱስ ይወደው የነበረ ደቀመዝሙር በሚል የብዕር ስም ስለራሱ ጽፎአል ። ዮሐንስ እውነት ፣ ፍቅር ፣ ብርሃን ወዘተ የሚሉ ቃላትን በብዙ ይጠቀማል ። ዮሐንስ በወንጌሉ ፣ በሶስቱ መልዕክቶቹና በራዕይ ውስጥ እውነት የሚለውን ቃል 122 ጊዜ ተጠቅሞአል ። ይህ የሚያሳየን ከምንም ነገር በፊት ቀዳሚውና ወሳኙ ጉዳይ እውነት መሆኑን ያሳየናል ። እውነትን ሳንይዝ እርስ በእርስ መዋደድ ፣ በአርነት መመላለስ ፣ በሁሉ አቅጣጫ ድል የሞላው ህይወት መኖር አይቻልም ። ባጠቃላይ እውነት ራሱ ክርስቶስ በመሆኑ እውነት በሌለበት መልካም ነገር የለም ። ዮሐንስ በዚህ በመልዕክቱ መግቢያ ላይ የእርስ በእርስ መዋደድ መሰረቱ እውነት እንደሆነ ፣ እውነት የሚገዛው የሰውን ልብ እንደሆነና መገኛውም ክርስቶስ መሆኑን በማሳየት መልዕክቱን ይጀምራል ።
1. በእውነት መዋደድ
" ሽማግሌው ፤ በእውነት ለምወዳት እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዷት ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆቿ " 2ኛ ዮሐ 1:1
እውነት የያዘ ፣ እውነትን የሚናገርና በእውነት የሚኖር ሰው እውነትን የሚወዱ ሁሉ ይወዱታል ። ነገር ግን ዛሬ ዛሬ እውነትን የያዘና በእውነት የሚሄድ ሰው ሳይሆን ተወዳጁ እውነትን የሚያመቻምች ፣ አስመሳይና ውሸታም ፣ እውነትን በአመጻ የሚከለክል ሰው ነው ተቀባይነትና ተከታይ ያለው ። ዮሐንስ የሚጽፍላት ይህች የቤተክርስቲያን መሪ የሆነች ሴት በእውነት ላይ በመቆሟ እንደሚወዳት እሱ ብቻ ሳይሆን እውነት የሚወዱ ሁሉ እንደሚወዱአት ስለ እርስዋ የሚያውቀውን ምስክርነት ይነግራታል ። ይህች ሴት ይህችን ቤተክርስቲያን ለመምራት ያስቻላትና ለዚህ ተግባር የተመረጠች ያደረጋትም እውነትን የያዘችና ለእውነት የቆመች በመሆንዋ ነው ። እውነትና ፍቅር አንዱ ከሌላው ጋር ተቃቅፈው የሚኖሩ ናቸው እውነት ባለበት ፍቅር አለ ፍቅር ባለበት እውነት አለ ጳውሎስ ሲናገር ፍቅር " ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም " 1ኛ ቆሮ 13:6 እንዲሁም በኤፌሶን መልዕክቱ ላይ " ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ " ኤፌ 4:15 ሁለቱ የተጣመሩ ናቸው ። የእርስ በእርስ ያለን ፍቅር እየጎለበተ ሊሄድ የሚችለው በእውቀትና በማስተዋል እያደግን በሄድን ቁጥር ብቻ ነው ስለዚህ ጳውሎስ እንዲህ ይጸልያል " ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ " ፊል 1:9
2. የእውነት መኖሪያ
" በውስጣችን ከሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ከሚሆን እውነት የተነሣ " 2ኛ ዮሐ 1:2
እውነት የሚኖረው በሰው ውስጥ ነው ። የሰው ልብ በእውነት ሲማረክ ፣ እውነት በውስጣችን ሲኖር የለውጥ ጅማሮ ያለው በዚህ ጊዜ ብቻ ነው ። አንድ ጊዜ እውነት በውስጣችን ከሰረጸች ማንም ሊያወጣት አይችልም ፣ እውነትን የሚወዱ ሁሉ እውነት የዘላለም ወዳጅ ናት ። ጌታ ኢየሱስ ማርያም ቃሉን ከመስማት ተነስታ እንድታግዛት እንዲያደርግ ማርታ ስትጠይቀው " ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት ፤ “ማርታ ፣ ማርታ ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ ፤ ትዋከቢአለሽም ፤ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው ፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች ፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም " ሉቃ 10:41,42 እውነት አንድ ጊዜ ውስጣችን ከገባ ማንም ሊወስደው አይችልም ። እውነት የእግዚአብሔር ቃል ነው ጌታ ሲናገር " በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው " ዮሐ 17:17 ቃሎቹ በኛ ካሉ ጸሎታችን እንኳ ውጤታማ ይሆናል " በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል " ዮሐ 15:7 ሰይጣን ተግቶ የሚሰራው እውነት በውስጣችን መኖሪያዋን እንዳታደርግ ነው " የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ ፥ ክፉው ይመጣል ፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል ... " ማቴ 13:19
3. የእውነትና የፍቅር ምንጭ
" ከእግዚአብሔር አብና የአብ ልጅ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ፣ ምሕረትና ሰላም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናል " 2ኛ ዮሐ 1:3
የእውነት መገኛው እግዚአብሔርን በክርስቶስ የሚያውቅና ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የተረዳና ይህ እውነት የተገለጠለት ሰው ብቻ ነው ። አማኝ የክርስቶስ ጸጋና ምህረት ሲገባው ህይወቱ በሰላም ከመትረፍረፉም በላይ እውነትንና ፍቅርን ገላጭ ይሆናል ። ክርስቶስን የተረዳ ሰው እውነትን ወይም ቃሉን በሚገባ የመረዳት ብቃት አለው ክርስቶስን ያለተረዳ ሰው እውነትን አያውቅም የእውነት መገኛዋና ትክክለኛ ስፍራዋ ክርስቶስን በማወቅ ውስጥ ነው ። ጌታ ኢየሱስ ፈሪሳውያን ለምን ቃሉን መስማት እንዳልቻሉ ሲናገር " ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው ? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው ። እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ ... " ዮሐ 8:43,44
ምንጭ ወዊ ምንተስኖት