የስህተትን መንፈስ መለየት
2ኛ ዮሐ 1:7-13
ቤተክርስቲያን በየዘመኑ የገጠማትና ሲፋለማት የኖረው ፣ አሁንም የሚገዳደራት አንድ ነገር ቢኖር የስህተት ትምህርት ነው ። ጌታ በዚህ ጉዳይ አስጠንቅቆአል “ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ " ማቴ 7:15 ከዋርያትም መካከል ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች ሲያስጠነቅቅ " ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ " ሐዋ 20:29,30 ዮሐንስ ራሱም " ወዳጆች ሆይ ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና " 1ዮሐ 4:1 ብሎአል ። ጴጥሮስም በ2ኛ ጴጥ 2:1 ላይ እንዲሁ ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ ተናግሮአል ። ስለ ሐሰት ትምህርት መረዳት የሚገባን ዋና ነገር ቢኖር አእማድ በሆኑ አስተምህሮቶች ላይ ልዩነት አለመኖሩን ነው እንጂ ከዚያ ውጪ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቶች ላይ እያንዳንዱ አገልጋይ ልዩነት አይኖረውም ማለት አይደለም ነገር ግን የትኛውም ልዩነት ይኑር የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ የምንማር ከሆንን በየትኛውም ወጥመድ አንያዝም ። ስለዚህ ዮሐንስ በዚህ ክፍል ስለ ስህተት አስተምህሮ ይህንን ይላል :-
1. አሳቹ እየሰራ ነው
" ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል ። እንዲህ ያለ ማንኛውም ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ... በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና ከትምህርቱ የሚወጣ ሁሉ አምላክ የለውም ፤ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ግን አብም ወልድም አለው" 2ኛ ዮሐ 1:7,9
የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አሁን እየሰራ ነው ። ይህ መንፈስ የትኩረት አቅጣጫው ሰወች ስለ ክርስቶስ የተዛባ መረዳት ይኖራቸው ዘንድ ነው ምክንያቱም የድነታችን መሰረቱ የተገነባው ክርስቶስን በተረዳንበት ልክ ላይ መሆኑን ሰይጣን ስለሚያውቅ ነው ። በዮሐንስ ዘመን የነበረው የተሳሳተ አስተምህሮ ክርስቶስ በስጋ አልተገለጠም የሚል ሲሆን በየዘመናቱ እንዲሁም ዛሬ በክርስቶስ ላይ የሚነሱ የስህተት ትምህርቶች ብዙ ናቸው ። ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ብቸኛው መንገድ ሆኖ እያለ በእርሱ ላይ የሚጨመሩ ብዙ ግሳንግሶች ዛሬም አእላፋትን በውጭ እያስቀራቸው ይገኛል ። እንዲህ ዓይነቱ አስተማሪ እንደ ዮሐንስ አገላለጥ አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው ። በክርስቶስ ላይ ከሚነሱ ስህተቶች መካከል በስጋ መገለጡን መካድ ፣ ኢየሱስን ሰው ብቻ አድርጎ መለኮትነቱን መካድ ፣ ብቸኛ አዳኝና አማላጅ መሆኑን መካድ ፣ የአብን የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ጨፍልቆ ኢየሱስ ብቻ በማለት የስላሴን ህልውና መካድ ፣ ክርስቶስ በመስቀል አልሞተም ብሎ ሞቱን መካድ ወዘተ ... ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ። ማንም ክርስቶስ ከተሸፈነበት አብም የለውም ምክንያቱም አብ ራሱ ያለ ወልድ ሊታወቅ አይችልምና ነው ጌታ ሲናገር " ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል ፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም ፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም፡” አለ " ሉቃ 10:22
2. አለመተባበር
" ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ፣ ይህንንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ፤ ሰላምም አትበሉት ፤ የሚቀበለው ሰው ፣ የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና " 2ኛ ዮሐ 1:10,11
የክርስቶስን ጤናማ ትምህርት ይዞ ከማናገኝበት ከየትኛውም ሰው መራቅ ፣ ትምህርቶቹንም አለመስማት እጅግ ተገቢ ጉዳይ ነው ። በቀድሞዋ ቤተክርስቲያን የስብሰባ ስፍራቸው ቤት ለቤት ስለ ነበር ይህንን ቀክፍተት በመጠቀም ክፉው እየሾለከ ይገባ ነበር ። ዛሬም በየቤታችንም ሆነ በየመድረኮቻችን የአስተምህሮ አቋሙን ሳናውቅ በሩን መክፈት ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ። ነገር ግን ሰወችን በአስተምህሮታቸው እንጂ በህይወት ድካማቸው መግፋት የለብንም ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ሲናገር " በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት ፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ " ሮሜ 14:1 እንዲሁም በገላትያ " ወንድሞች ሆይ ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት ... " ገላ 6:1 መባሉን መዘንጋት አይገባም ።
3. ለአገልጋዮች ቦታ በመስጠት
" የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ፤ ይሁን እንጂ በወረቀትና በቀለም እንዲሆን አልፈልግም ፤ ዳሩ ግን ደስታችን ፍጹም ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት ላነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ " 2ኛ ዮሐ 1:12
ሐዋርያው በኤፌሶን አካባቢ ወደ ነበሩት አብያተክርስቲያናት እንዳገለገለ ታሪክ ይናገራል ። ዮሐንስ እጅግ በሰፊው በልቡ ያለውን ይጽፍላቸው ዘንድ አልወደደም ይልቁንም ፊት ለፊት በመገናኘት በክርስቶስ ያገኙትን ደስታ አብሮ ለማጣጣምና በሰፊው ለማስተማር ይፈልጋል ። እንዲሁም እኛ በክርስቶስ ያገኘነውን ደስታ ለመካፈል ያሉንን አገልጋዮች ለመቀበልና ከእነሱም ለመማር የተከፈተ ልብ ልናገኝ ይገባል ። በዚህም መንገድ ከብዙ የተፋለሱ አስተምህሮቶች እንድንጠበቅ ይረዳናል ።
ምንጭ ወዊ ምንተሰኖት