ገድለ ቅዱሳን


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


@Gedelat
ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡
በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤

           ❤ #ጥር ፳፬ (24) ቀን።

❤ እንኳን #ከእስክድርያ_አገር_ከታላላቆቿ_ወገን ለሆነች በዓቷን በማጽናት #ለ22_ዓመታት ዘግታ ለኖረችውና የላመ የጣፈጠ ቀምሳ ለማታውቀው፤ ለከበረች ተጋዳ #ቅድስት_ማርያ_ለዕረፍቷ በዐሏ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከተመሰገነ #ቀሲስ_አብሳዲ ከመታሰቢያው፣ ከግብጽ አገር ከጥሐ አውራጃ ስፍጥ ከምትባል መንደር ከሆነ ከከበረ #ከታላቅ_አባት_ከቢፋ በሰማዕትነት ከዐረፈና #ከሐውዚን_ጻድቃን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                            ✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለጻድቃን እለ #በሐውዜን"። ትርጉም #በሐውዜን ያሉ ለኾኑ #ጻድቃ_ ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።

                           ✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_ማርያ፦ ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ከታላላቆቿ ወገን የሆነች ነች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ክርስቲያኖች ናቸው በአደገችም ጊዜ ሊአጋቧት አሰቡ እርሷ ግን ይህን ጋብቻ አልወደደችም እናትና አባቷም በሞቱ ጊዜ የተዉላትን ገንዘብ ሁሉንም ለድኆች ሰጥታ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ከአሉ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባች የምንኵስና ልብስንም ለብሳ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለች ድል እስካደረገችውም ድረስ እንቅልፍን ዐሥራ ሁለት ዓመት ስትታገለው ኖረች ከቶ አትተኛም ነበር እንደዚያ ገዳም ሕግ በእሊህ በዐሥራ ሁለት ዓመታት ሁልጊዜ እስከማታ ትጾም ነበር።

❤ ከዚህም በኋላ የከበረ አስኬማን ለበሰች ያን ጊዜ ከጥጥ ባዝቶ የተሠራውን ልብስ ከላይዋ አውልቃ ማቅ ለበሰች ትችል እንደሆነ ወይም አትችል እንደሆነ ራሷን ትፈትን ዘንድ ለመዝጋት ትፈቅድላት ዘንድ እመምኔቷን ለመነቻት እርሷም ፈቀደችላት በዚያንም ጊዜ በዓቷን ዘጋች ምግቧን የምትቀበልበት ትንሽ መስኮት ቀደደች ሥጋውንና ደሙን በዚያው ትቀበላለች በዚያችም በዓት ውስጥ ሃያ ሁለት ዓመት ዘግታ ኖረች።

❤ በዚህ ሁሉ ዘመን ቁማ ትጸልያለች በመኝታ ጊዜም ጥቂት ትተኛለች የቀረውንም ሌሊት እስቲነጋ ቁማ ስትጸልይ ታድራለች። በየሁለት ቀን የምትጾም ሆነች የምትመገበውም በውኃ የራሰ ለምለም እንጀራ ነበር በከበረችም በአርባ ጾም እንጀራ አትበላም በየሦስት ቀን እየጾመች በውኃ የራሰ ሽምብራ ትመገባለች እንጂ።

❤ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን የከበረ የጥምቀት በዓልም በሆነ ጊዜ ከተባረከው ውኃ ያመጡላት ዘንድ ለምና አመጡላት ፊቷንና እጆቿን ታጥባ ሥጋውንና ደሙን ተቀበለች ከተባረከውም ውኃ ጠጣች ከዚህም በኋላ ታመመች እስከ ሃያ አንድ ቀንም በመኝታዋ ላይ ተኛች ዳግመኛ በዚች ቀን በጥር በሃያ አንድ ሥጋውንና ደሙን ተቀበለች።

❤ ከዚህም በኋላ እመ ምኔቷን አስጠራቻት እግሮቿንም እንታቀርብላት ብዙ ልመናን ለመነቻትና ስታቀርብላት ሳመቻቸው ፊቷንም አሸችባቸው "ወደ ክብር ባለቤት ጌታዬ ክርስቶስ ላቀረቡኝ እግሮችሽ እገዛለሁ" አለች ዳግመኛም ደናግሉን ሁሉ አስጠርታ ተሳለመቻቸውና ከሦስት ቀን በኋላ እንዲጐበኟት ለመነቻቸው ይኸውም ጥር ሃያ አራት ቀን ነው በመጡም ጊዜ ሙታ አገኟት ገንዘውም ከደናግል አስከሬን ጋር አኖሩዋት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ማርያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ጥር 24 ስንክሳር።

                            ✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለማርያም ዘአጥብዓት ትፍዲ። ለነዳያን ምጽዋተ ንዋየ አቡሃ ወላዲ። ወወጠነት ገድለ በአጽርዖ ንዋም ዓዲ። እምአምኆ ዛቲ ዕለት እንበለ ሕቀ እጐንዲ። ሰላም እብል ለቀሲስ አብሳዲ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥር_24።

                             ✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 1-17።

                              ✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ። ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ። በእንተ ዳዊት ገብርከ"። መዝ 131፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 2፥1-9፣ 1ኛ 3፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 4፥29-ፍ.ም።  የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 18፥1-9። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የስብረተ አፅማቸው በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።


@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL




❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

           ❤ #ጥር ፳፬ (24) ቀን።

❤ እንኳን #ከደቡባዊ_ግብጽ ከታችኛው ምድር አውራጃ ከንሒሳ ከተማ ለሆነ #ለቅዱስ_ለአባ_ኖብ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለልደት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን።                             

                           ✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_አባ_ኖብ፦ይህም ቅዱስ ከደቡባዊ ግብጽ ከታችኛው ምድር አውራጃ ከንሒሳ ከተማ ነው።
ወላጆቹ ቅዱሳን ንጹሐንና የሚራሩ ነበሩ። ይህንንም ቅዱስ ኖብን በወለዱት ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት እስኪሆነው ፈሪሀ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጉት። ቤተ ክርስቲያንን የመጻሕፍትን ቃል መስማትንና መማርን የሚወድ ሆነ።

❤ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የክርስቲያን ወገኖችን ዲዮቅልጥያኖስ በአሠቃያቸው ጊዜ ይህ ቅዱስ ደሙን ስለ ጌታችን ሊአፈስ አሰበ ያን ጊዜም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ ቄሱንም ምእመናንን እንዲህ እያለ ሲያስተምራቸውና ሲያበረታቸው "ጣዖታትን ከምታመልኩ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስለ ክርስቶስ ነፍሳችሁን ለሞት አሳልፋችሁ ብትሰጡ ለእናንተ መልካም ነው" ሲላቸው ሰማው። ይህም ቅዱስ እያዘነና እየተከዘ ወደ ቤቱ ተመለሰ አባቱም የተወለትን ወርቁንና ብሩን ልብሶችን ሁሉ ተመልክቶ እንዲህ አለ ሁሉ ነገር የዚህ ዓለም ፍላጎቱም ሁሉ እንደ ሚያልፍ እነሆ ተጽፏል። ከዚህም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ።

❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ገምኑዲ ሔደ በእግሩም ሲጓዝ በባሕሩ ዳርቻ ሉስዮስ የሚባለውን መኰንን አገኘው በፊቱም ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ። መኰንኑም ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት በእርሱ ላይም የሚደርሰውን ሁሉ ነግሮት አጽናናው።

❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ሰሜን አገር ሲጓዝ የከበረ ኖብን ከእርሱ ጋራ በመርከብ ወሰደው በመርከቡም ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው መኰንኑም ሊበላና ሊጠጣ ተቀመጠ በመኰንኑም እጅ የነበረው ጽዋ ወዲያውኑ እንደ ደንጊያ ሆነ የወታደሮቹም ዐይኖቻቸው ታወሩ የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ወርዶ አባ ኖብን ፈትቶ ከተሰቀለበት አወረደው በአፍንጫውና በአፉ የወረደውንም ደሙን አሻሸለት።

❤ ከዚህ በኋላም መልካም ነፋስ ነፍሶ መርከቢቱ ተጓዘች። ወደ አትሪብ ከተማም ደረሱ ወታደሮችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ትጥቃቸውን ፈተው በመኰንኑ ፊት ጣሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመኑ ሰማዕታትም ሆነው ራሳቸውን ቆረጡአቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። መኰንኑም በአትሪብ ከተማ ቅዱስ አባ ኖብን ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው በብረት ዐልጋ ላይም አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ በጸለየ ጊዜም እግዚአብሔር ከእሳት አዳነው።

❤ ከዚህም በኋላ በመጋዝ መገዙት ሕዋሳቱንም ቆራረጡ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ አዳነው ያለ ጉዳትም በጤና አስነሣው። ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ወሰዱት በዚያም ብዙ አሠቃዩት በላዩም እባቦችን ሰደዱ ግን አልቀረቡትም ከእባቦችም አንዱ ሒዶ በመኰንኑ አንገት ተጠመጠመ ያስጥሉትም ዘንድ ሟርተኞቹን አዘዛቸው ግን አልተቻላቸውም ከዚህም በኋላ ያድነው ዘንድ ቅዱስ አባ ኖብን ለመነው ቅዱሱም ከይሲውን ትቶት ከአንገቱ እንዲወርድ አዘዘው።

❤ መኰንኑም ሁለተኛ በእሳት እንዲአቃጥሉት ሟርተኞችንና ሥራየኞችን አዘዛቸው እሳቱም ምንም አልነካውም። አቅፋሐስ ከሚባል አገርም ዮልዮስ መጣ ከእርሱም እንደ ተረዳ ገድሉን ጻፈ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።

❤ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾለት አጽናናው እንዲህ ብሎም ቃል ኪዳን ሰጠው "ሥጋህ በሚኖርበት ቦታ ከእርሱ ታላቅ ፈውስ ይሆናል እንዲሁም በመከራው ጊዜ ስምህን በመጥራት ከእግዚአብሔር ርዳታ ለሚሻ ሁሉ ድኅነት ይደረግለታል። መታሰቢያህንም ለሚያደርግ ሁሉ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማም ለሚያጠጣ፣ ለቤተ ክርስቲያንም በስምህ መባ ለሚሰጠው፣ የገድልህንም መጽሐፍ ለሚጽፍ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ"።

❤ ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡ ተጋድሎውንም ፈጸመ ሥጋውንም ቅዱስ ዮልዮሰ አንሥቶ ከሁለት አገልጋዮቹ ጋራ ንሒሳ ወደ ሚባል አገሩ ላከው። የመከራውም ወራት በተፈጸመ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩለት በውስጣቸውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ አባ ኖብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፦ የሐምሌ 24 ስንክሳር።

                                
@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?idh=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL




❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤

                ❤ #ጥር ፳፬ (24) ቀን።

❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለፀሐይ ዘኢትዮጵያ #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት በቁመትና በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግሩ አገዳ ለተሰበረበት (#ለስብረተ_አፅማቸው) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ እንደ ነዳይ ሆነው ለምነው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት ለሚታወቁት #ለአቡነ_እጨጌ_መርሐ_ክርስቶስ (ዘሸዋ) ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።

                           ✝️ ✝️ ✝️
❤ #የአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ስብረተ_አፅም፦ "...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም። ሌሊትና ቀንም እግዚአብሔርን አመሰገነ። ዓለምንም እንደ ትቢያና እንደ ጉድፍ ቆጠረው ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ሆነ ልቡናውም ዘወትር ወደ ዓየር የተመሰጠ ነበር። እንዲህ ባለም ገድል ብዙ ዘመን (22ዓመታት) ኖረ። ቁመትንም ካበዛ ወዲህ አንዲቱ የእግሩ አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግሩ ሰባት ዓመት ቆመ። ከነዚህም አራቱን ዓመት ውሃው አልጠጣም"። ምንጭ፦ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ 53፥8-11።

                          ✝️ ✝️ ✝️
❤ #እጨጌ_መርሐ_ክርስቶስ (ዘሸዋ)፡- ትውልዳቸው አገራቸው ሸዋ ሚዳ ሲሆን ለገዳማት ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በተለይም በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ገድል አላቸው፡፡ ይኸውም እንደ ነዳይ ሆነው ለምነው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት ይታወቃሉ፡፡ ከባለ ሀብቶች ለምነው ያገኙትን ለድሆች ይመጸውቱትና በቀረው ቤተ ክርስቲያን ይሠሩበታል፡፡ አስደናቂ ገድላቸውና ዐፅማቸው በደብረ ሊባኖስ ይገኛል፡፡ በትግራይም ትልቅ ገዳም አላቸው። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
   

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL






💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷   "  መንፈሳዊ የድካም ዓይነቶች ! "

[    💖   አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ   💖    ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ድካሜንና መከራዬን እይ ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።

ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል። ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ ፤ አንተን ታምኛለሁና አልፈር። አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ። ❞

[   መዝ.፳፭፥፲፰  ]


🕊                       💖                     🕊




                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

          [      ክፍል  ሰባ ዘጠኝ      ]

                         🕊  

[  ሁለት አኃው አብረው ለመኖር ለጠየቁት የመለሰው ! ]

🕊

❝ አንድ አረጋዊ ከአንድ እኁ ጋር ሆነው አባ መቃርዮስን እንደ ጎበኙት ተነገረ፡፡ እነርሱም ፦ “አባታችን ሆይ ፣ እንደ አንድ ሰው ሆነን አብረን መኖር እንፈልጋለን” አሉት:: እርሱም አረጋዊውን እንዲህ አለው ፦ “መጀመሪያ እንደ እረኛ ሁን፡፡ ክፉ ትል ተሸካሚ [አስተላላፊ] የሆነች ወፍ በበጎች መካከል ትሎችን ብትዘራባቸው ትሎቹን እስከሚገድላቸው ድረስ ለታመመችው በግ መድኃኒት ይሰጣታል:: አንድ በግ ተላላፊ የሆነ በሽታ የሚዘራ ከሆነ ግን በሽታውን እስከሚያስወግደው ድረስ መድኃኒት ይጠቀማል፡፡”

አረጋዊውም ፦ “የዚህን አባባል ትርጉም ንገረኝ" አለው:: አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ “ትል የሚዘራው ወፍ እንደ ዲያብሎስ ነው ፣ በጉ ደግሞ ከአንተ ጋር እንደሚኖረው ወንድም ያለ ነው። ትሎቹ ደግሞ በነፍስ የሚኖሩና በልብ የሚራቡ የአጋንንት ፍትወታትና ክፉ ምኞቶች ናቸው። ትሎች በሰውነት ቁስል ላይ እንደሚኖሩት ማለት ነው። በሽታውን የሚያስወግደው መድኃኒት ደግሞ በመንፈስ ማደግ ፣ ትኅርምትና መድኃኒት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት
ነው።

ነፍስን የሚያነጹዋት ነገሮች እነዚህ ናቸው ፤ አጋንንት በእኛ ላይ ከሚያሰማሯቸው ክፉ ጠላቶቻችን ከሆኑት ከእኩያት ፍትወታትና ከክፋቶች ሁሉ የሚያጠሯት እነዚህ ናቸው::”

ያን እኁም እንዲህ ብሎ ተናገረው ፦ “ልጄ ሆይ ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ መሥዋዕትና መባዕ አድርጎ እስኪያቀርበው ድረስ አባቱን እንደ ታዘዘው እንደ ይስሐቅ ሁን ፤ እርሱ ለአባቱ በመታዘዙ በቤተ ክርስቲያን መዝገብ ውስጥ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ተጽፏልና፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


💖                      🕊                      💖




🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

       [    ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ !    ]

🕊                        💖                       🕊

በሰማይ ያሉትን ኃይላትን ፤ መላእክትን ትቶ ወደ እኛ መጥቶ ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ ብዙ ቸርነትን አደረገልን ፤ ሞትን አጠፋው የዲያብሎስን ሥልጣን ሻረ ፤ ከጽኑ አገዛዙም አዳነን ፤ በፍጹም ክብርም አከበረን።

ሰው የሆነም ዘመድ ሊሆነን ብቻ ፡ አይደለም ፤ ፈጽሞ ይቅር አለን ኃጢአታችንን ለማስተስረይ ፤ ከአብ ጋር ለማስታረቅ ሊቀ ካህናትም ይሆነን ዘንድ ወደደ እንጂ ፤ ስለዚህም ሰዎችን ሊመስላቸው ይገባል ባለው ነገሩ ላይ ጨምሮ በሁሉ አዛኝ የሕዝቡንም ኃጢአት ለማስተስረይ በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ አስታራቂ ይሆናቸው ዘንድ ነው አለ። [ ዕብ.፪፥፲፯ ]

ባሕርያችንን ስለተዋሐደ ሰው የመሆኑን ነገር ያስተምረን ዘንድ ይኸን ተናገረ ሰው ለመሆን ያበቃው ፤ ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ብቻ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት የለውም ፤ ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአት ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው ? ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው ? መሥዋዕት ለመሆን የነሣው ሥጋው ብቻ ነው እንጂ። ❞

[    ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖






🕊

[  † እንኳን ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ : እና ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †   ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  † ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ †  🕊

† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነው::

በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ዽዽስናን ሹሞ ፪ መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::

ከሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ በረከትን እንሳተፍ ዘንድ ጊዜ ካለን ቅዱስ ዻውሎስ ለልጁ ጢሞቴዎስ ከላካቸው መልዕክቶች ጥቂት እናንብብ::

🕊    †   ቴዎዶስዮስ   †    🕊

† በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ሰማዕታትም: ጻድቃንም: ሊቃውንትም: ነገሥታትም ተጠርተውበታልና:: ዛሬ የምናከብረውም ቴዎዶስዮስ ዘየዓቢ [ ታላቁ ] የሚባል ሲሆን ይህን የምንለው ከትንሹ ቴዎዶስዮስ [ የልጅ ልጁ ነው ] ለመለየት ነው::

ታላቁ ቴዎዶስዮስ በሮም የነገሠው በ፫፻፸ [370] ዓ/ም አካባቢ ሲሆን ከነ ቤተሰቡ ክርስቲያን ነበር:: እነዚህ ነገሮቹ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን እንዲታሰብ አድርጐታል :-

፩. በዓለም ታሪክ ክርስትና በሮም ግዛት ሁሉ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን አውጇል::
፪. የቤተክርስቲያንን ትልቁን 2ኛ ጉባኤ ቁስጥንጥንያን በ፫ መቶ ፹፩ [381 (373) ዓ/ም አሰናድቷል::
፫. ከበጐነቱ የተነሳ የተቀደሱ ልጆችን አፍርቷል:: ሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ: ቅዱስ አኖሬዎስ: ቅዱስ አርቃዴዎስ እና ቅድሰት ታኦድራ ልጆቹ ሲሆኑ አቡነ ኪሮስ ትንሽ ወንድሙ ናቸው::

ጻድቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በ፫፻፺ [ 390 ] ዓ/ም አካባቢ ዐርፏል::

† አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[   † ጥር ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ጢሞቴዎስ [ ሐዋርያና ሰማዕት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር ]
፪. ቅዱስ ጌርሎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
፬. ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ [ ዘቁስጥንጥንያ ]

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል
፬. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭. አባ ሳሙኤል
፮. አባ ስምዖን
፯. አባ ገብርኤል

" መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ዻውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ::
ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን
. . ."

[፩ጢሞ.፩፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖






👉 #የይድረስልኝ_አስቸኳይ_ጥሪ_ #ስለ_ፈጣሪያችን_አዕጋዝተ_ዓለም_ቅድስት_ሥላሴ። ቤተ ክርስቲያኑ ምንጣፍ ተነጥፎለት፣ መጋረጃ ተጋዶና ንዋየ ቅድሳቱ ተማልቶ እንዲመረቅ ሁላችንም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ። #ሼር_ሼር_ሼር በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ። እስከ #የካቲት_7_ቀን_2017 ዓ.ም እንድረስላቸው።

👉 ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታዮች እንዴት ሰነበታችሁ መቼም አታሳፍሩኝ #3345_ሰዎች_ቢያንስ_100_ብር ብንረዳ ምንጣፉን ሙሉ ለሙሉ እናነጥፈዋለን #በሰሜን_ሸዋ_ሀገረ_ስብከት_በአንጾክያ_ወረደ_ቤተ_ክህነት_ስር_ለሚገኘው_ለወበሻ_ቅድስት_ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ህንፃው ሥራ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ከሞላ ጎደል እያለቀ ስለሆነ #የካቲት_8_እና_9_ቀን_2017 ዓ.ም ይመረቃል  ዓ.ም ነገ ግን የውስጥ ምንጣፍ እና መጋረጃ፣ ነዋየ ቅድሳት ስለሚጎድል በሀገር ውስጥም ባሕር ማዶ ያላችሁ ምዕመናንና ምዕመናት ምንጣፋኑና ንዋየ ቅድሳቱ በግዛት የበኩላችሁ አስተዋጾ እድናደርግ በፈጥኖ ደርሹ በወበሻ ቅድስት ሥላሴ ስም እንማጸናለን።

👉 በግልም ሆነ በማኅበር ምንጣፍን፣ መጋረጃውና ንዋየ ቅድሳቱን ገዝቶ ማበርከት ይቻላል።


1, ለቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ ምንጣፍና መጋረጃ።
የቤተ ክርስቲያኑ #ምንጣፍ_ስፍቱ_230 ካሬ ነው። #የአንዱ_ካሬ_ዋጋ_1500*230= 345,000 ብር ነው።

የተለያዩ ንዋየ ቅድሳት ናቸው፦
2 የአንድ ሰሞነኝ ልብሰ ተክህኖ  18,000 ብር።
3, የታቦት ማክበርያ መጎናጸፍያና ቀጸላ 9,000 ብር።
4, የሥጋ ወደሙ ማክበርያ ጻሕልና ጽዋ 8,000 ብር።
5, የሥጋ ወደሙ ማውረጃ አጎበር 4000 ብር።
6, ወርቅ ቅብ ጽንሐሕ አንድ ትልቅ 8,500 ብር አንድ ትንሽ 600 ብር።
7,የግሪክ እጣን 1 ኪሎ 3000 ብር።
8, መቋሚያ ቢያንስ የብረት 12*330= 3960 ብር።
9, ጸናጽል የእንጨት መያዣ ቢያንስ 12*300= 3600 ብር።
10, ሽቶ።
11, ማኅፈድ።

👉 የቤተ የንግድ ባንክ አካውንት፦ #1000279032555። የወበሻ ቅድስት ሥላሴ ህንፃ አሰሪ።

👉 ለበለጠ መረጃ፦ 09 11 41 48 52 09 13 66 98 87፣ 09 46 44 04 05፣ 09 85 32 50 78።

👉 በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ ያላችን ለመርዳት የምትፈልጉ ምዕመናን በዚሁ ቁጥር #0911414852 #በኢሞ_በዋትሳፕ_በቴሌግራም(#@Teamhokidusan)  ማውራት ትችላላችሁ ከበረከቱም የምትሳተፉ ያስገባችሁበት እስክሪን ሹትና ስመ ክርስትናችሁ ላኩልን አባቶች በጸሎት እዲያስባችሁ።



Показано 20 последних публикаций.