❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን ለከበሩ #በቅዱስ_ጳውሎስ ትምህርት ላመኑ #ለቅዱሳን_አውሳንዮስ_ፊልሞ፣ ለድንግል #ቅድስት_ሉቅያ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለከበረ #ሐዲስ_አባ_እንጦኒ ይህም ረውሕ ለሚባለው ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ከግብጽ አገር ከእስሙናይን አውራጃ ለሆነ ዐሥራ ስምንቱ ዓመት ቆሞ ሳይቀመጥ ለጸለየ #ለአባ_አቡፋ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር #ከዲያቆን_ቶና ከአገረ ቊስ #ሚናስ_ከጋዛ_ይልማድዮስ በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ #ከደማይልናልና_ከርጊኖስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የከበሩ_ቅዱሳን_አውሳንዮስ_ፊልሞና_ሉቅያ፦ እሊህ ቅዱሳንም በአፍራቅያ አገር ሳለ በከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ያመኑ ናቸው ከሀድያንም ዝሑራ በሚባል ኮከብ ስም ለሚጠሩት ለአርታዳሚ ጣዖት በዓልን በአደረጉ ጊዜ አይተው በስሕተታቸው ሊዘብቱ እሊህ ቅዱሳን ተስብስበው ወደ ጣዖቱ ቤት ገቡ ሰዎችም ለጣዖቱ ሲሠዉና ከፍ ከፍ ሲያደርጉት በአዩአቸው ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እሳትነት ልባቸው ነደደ ከጣዖቱም ቤት ወጥተው ወደ ክርስቶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሔደው የክብር ባለቤት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብሩንና ልዕልናውን አብዝተው አመሰገኑ። ከዚያ ካሉት አንድ ሰው በሰማቸው ጊዜ በጣዖታቸው ላይ እንደ ዘበቱ የተናገሩትን ልብ ብሎ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀላቸው መኰንኑም በፈረስ ተቀምጦ ሔደ ከወታደሮቹም ጋር ቤተ ክርስቲያኒቱን ከበባት ከምእመናንም ሰዎች የሸሹ አሉ።
❤ እሊህም ሦስቱን ቅዱሳን ያዛቸው የብረት ዘንጎችን በእሳት አግለው ቅዱሳኑ ጐኖች ውስጥ አደረጉት ከዚህም በኋላ የከበረ አውሳንዮስን ወደ ጒድጓድ ወረወሩትና ነፍሱን እስከ ሰጠ ድረስ በድንጊያ ወገሩት። የከበረ ፊልሞናንና የከበረች ሉቅያን ግን ብዙ ጊዜ በጸና ሥቃይ ያሠቃዩአቸው ጀመር ነፍሳቸውንም ይወስድ ዘንድ እግዚአብሔርን ለመኑት እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ነፍሳቸውን የካቲት25 ወሰደ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እንሆ የምስክርነታቸውና የሃይማኖቻቸው መታሰቢያ ተጽፎአል። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዲስ_አባ_እንጦኒ (ረውሕ)፦ ይህም ከከበሩ ዐረቦች ወገን የቆሮስ ሰው የሆነ ብዙ ገንዘብ ያለው ነው በሰማዕታት አለቃ በቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም አጠገብ በወንዝ ዳርቻ የሚኖር ነው። ይህም ጐልማሳ አብያተ ክርስቲያናትን የሚቃወም ሁኖ ቅዱስ ቊርባንን በመስረቅ ኅብስቱን ይበላዋል የከበረ ደሙንም ከጽዋው ውስጥ ይጠጣል የመሠዊያውንም ልብስ ገፎ በእሳት ያቃጥለዋል በክርስቲያን ሃይማኖትም ላይ ይዘብታል። መኖሪያው ቤቱ በከፍታ ቦታ ላይ ስለ ሆነ ካህናት ሲያገለግሉ ይታዩት ነበር።
❤ በአንዲትም ዕለት በቅዳሴ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ተከፍቶ አየ በፈረስም ተቀምጦ መጣ የቅዱስ ቴዎድሮስንም ሥዕል ተመልክቶ በፍላፃዎች ወጋው። አንዲቱም ፍላፃ ተመልሳ መሐል እጁን ነደፈችው በጭንቅም ከእጁ ላይ መዘዛት ይህንንም ለማንም አልነገረም። በሌላዪቱም ዕለት በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ሳለ መሥዋዕትን ተሸክመው ወደ መቅደስ ሲገቡ ካህናትን አያቸው በጻሕሉም ውስጥ ነጭ በግ ተኝቶ ከበላዩ ነጭ ርግብ ሲጋርደው በቅዳሴውም ፍጻሜ ያ በግ በየመለያያው የተከፋፈለ ሆኖ ካህናቱም ከተከፋፈለው ሥጋውን ሲቀበሉ ደሙንም ከጽዋው ውስጥ ሲቀበሉ አየ እጅግም አደነቀ። በልቡም የክርስቲያን ሃይማኖት እጅግ ድንቅ ነው በእውነትም የከበረ ክቡር ነው አለ። ዳግመኛም ያ በግ ተመልሶ እንደ ቀድሞው ኑሮው ሕያው ሁኖ አየ ከዚያም በኋላ ከመቀመጫው ወርዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ሔዶ ያየውን ሁሉ ለካህናቱ ነገራቸው እርሱም ሰምተው ስለዚህ ድንቅ ሥራ ደስ አላቸው።
❤ በዚችም ሌሊት ተግቶ ሲጸልይ ሊቅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ተገለጠለት እርሱም በፈረሱ ላይ ተቀምጦ ነበር እንዲህም አለው "እንሆ በእኔ ላይ ሥዕሌን እስከ ወጋህ ድርስ ክፉ ሠራህ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሥጋ ላይም ዘበትክ አሁንም ከክህደትህ ተመልሰህ በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን" አለው ይህንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ። በማግሥቱም በፈረሱ ላይ ሁኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱም ገብቶ ከእርሱ የሆነውን ሁሉ ነገረው ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው እርሱንም "በሕዝብ፡ፊት እዳላጠምቅህ እፈራለሁ ነገር ግን ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሒድ ጌታችን ክርስቶስ የሚያጠምቅህን ይሰጥሃል" አለው። እርሱም ሰምቶ ወደ ዮርዳኖስ ሔደ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ የሌሊቱም እኩሌታ ሲሆን የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ነጭ ሐር ግምጃ ለብሳ ተገለጠችለት ከእርሷም ጋር በንጹሕ ልብስ የተሸለመች ሴት ነበረች በእጅዋም ይዛ አነሣችውና "አትዘን እኔ ካንተ ጋር እኖራለሁና" አለችው። ሲነጋም ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በሔደ ጊዜ ሁለት ገዳማውያን መነኰሳትን አገኛቸው እነርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቁት። ስሙንም እንጦንስ ብለው ሰየሙት የምንኵስና ልብስ አስኬማንም አልብሰው በሰላም አሰናበቱት ወደ ደማስቆም ሔደ ወደ ቤቱ ገባ።
❤ ባልንጀሮቹና ወገኖቹም በአዩት ጊዜ "የለበስከው ምንድን ነው አሉት" እርሱም "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አላቸው በዚያንም ጊዜ ይዘው በሜዳ ውስጥ እየጐተቱ ወደ መኰንኑ እስኪያደርሱት ይደበድቡት ነበር። መኰንኑም ወደ እስር ቤት እንዲጨምሩት አዘዘ በታላቅ ሥቃይም ዐሥራ ሰባት ሌሊት በዚያ ኖረ እንሆ በላዩ ብርሃን ወረደ እንዲህም የሚል ቃል ሰማ "እንጦንዮስ ሆይ አክሊል ተዘጋጅቶልሃልና አትፍራ" ብርሃንን የለበሱ ሁለት አረጋውያንም መጥተው በራሱ ላይ የብርሃን አክሊል አኖሩ በነጋ ጊዜም ወደ አደባባይ ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በሌሊትም በላዩ ብርሃን ወረደ ጠባቆችም አይተው ከዕንጨት ላይ አውረዱት በጤግሮስ አቅራብያ ቀበሩት ከመቃብሩም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዲስ በአባ እንጦንስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_አቡፋና፦ ይህም አባት ከቶ ብርሃን በሌለበት ዋሻ ውስጥ የሚኖር ሁኖ በየሁለት ቀን ይጾማል የሚበላውም የሚጠጣውም በመለኪያ ተለክቶ ነው በሌሊትም በመዓልትም አምስት መቶ ጊዜ ይጸልያል። በአንደዲትም ዕለት ወንድሞች ሊጐበኙት ወደርሱ መጡ እንጀራንም አጣ ሦስት እንጀራንም በአገኘ ጊዜ ለሃያ ሰዎች አቀረበላቸው እነርሱም በልተው ጠገቡ ተአምራትም እያደረገ በሽተኞችንም እየፈወሰ ኖረ።
❤ ከዚያም በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ "አቡፋና ሆይ ዐሥራ ስምንት ቀረህ" የከበረ አቡፋናም" ዐሥራ ስምንት ዕለታት እንደሆኑ አስቦ እሊህ ዕለቶች እስቲፈጸሙ ቆመ ከዚያም በኋላ ሱባዔዎች ናቸው ብሎ ይህንንም በመቆም ፈጸመ እንደ፡ገና ወሮች ይሆናሉ ቢሆኑስ ብሎ ይህንም በመቆም ሳያጓድል አደረሰ። ዳግመኛም እንዲህ የሚል ቃል ወደርሱ መጣ "አቡፋና ሆይ ዐሥራ ስምንት ዓመት ናትና ጽና በርታ" አለው በዚያንም ጊዜ ፈጽሞ ጸና።
https://t.me/Gedelat