🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ ! ]
🕊 💖 🕊
❝ በሰማይ ያሉትን ኃይላትን ፤ መላእክትን ትቶ ወደ እኛ መጥቶ ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ ብዙ ቸርነትን አደረገልን ፤ ሞትን አጠፋው የዲያብሎስን ሥልጣን ሻረ ፤ ከጽኑ አገዛዙም አዳነን ፤ በፍጹም ክብርም አከበረን።
ሰው የሆነም ዘመድ ሊሆነን ብቻ ፡ አይደለም ፤ ፈጽሞ ይቅር አለን ኃጢአታችንን ለማስተስረይ ፤ ከአብ ጋር ለማስታረቅ ሊቀ ካህናትም ይሆነን ዘንድ ወደደ እንጂ ፤ ስለዚህም ሰዎችን ሊመስላቸው ይገባል ባለው ነገሩ ላይ ጨምሮ በሁሉ አዛኝ የሕዝቡንም ኃጢአት ለማስተስረይ በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ አስታራቂ ይሆናቸው ዘንድ ነው አለ። [ ዕብ.፪፥፲፯ ]
ባሕርያችንን ስለተዋሐደ ሰው የመሆኑን ነገር ያስተምረን ዘንድ ይኸን ተናገረ ሰው ለመሆን ያበቃው ፤ ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ብቻ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት የለውም ፤ ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአት ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው ? ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው ? መሥዋዕት ለመሆን የነሣው ሥጋው ብቻ ነው እንጂ። ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖