†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰባ ዘጠኝ ]
🕊
[ ሁለት አኃው አብረው ለመኖር ለጠየቁት የመለሰው ! ]
🕊
❝ አንድ አረጋዊ ከአንድ እኁ ጋር ሆነው አባ መቃርዮስን እንደ ጎበኙት ተነገረ፡፡ እነርሱም ፦ “አባታችን ሆይ ፣ እንደ አንድ ሰው ሆነን አብረን መኖር እንፈልጋለን” አሉት:: እርሱም አረጋዊውን እንዲህ አለው ፦ “መጀመሪያ እንደ እረኛ ሁን፡፡ ክፉ ትል ተሸካሚ [አስተላላፊ] የሆነች ወፍ በበጎች መካከል ትሎችን ብትዘራባቸው ትሎቹን እስከሚገድላቸው ድረስ ለታመመችው በግ መድኃኒት ይሰጣታል:: አንድ በግ ተላላፊ የሆነ በሽታ የሚዘራ ከሆነ ግን በሽታውን እስከሚያስወግደው ድረስ መድኃኒት ይጠቀማል፡፡”
አረጋዊውም ፦ “የዚህን አባባል ትርጉም ንገረኝ" አለው:: አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ “ትል የሚዘራው ወፍ እንደ ዲያብሎስ ነው ፣ በጉ ደግሞ ከአንተ ጋር እንደሚኖረው ወንድም ያለ ነው። ትሎቹ ደግሞ በነፍስ የሚኖሩና በልብ የሚራቡ የአጋንንት ፍትወታትና ክፉ ምኞቶች ናቸው። ትሎች በሰውነት ቁስል ላይ እንደሚኖሩት ማለት ነው። በሽታውን የሚያስወግደው መድኃኒት ደግሞ በመንፈስ ማደግ ፣ ትኅርምትና መድኃኒት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት
ነው።
ነፍስን የሚያነጹዋት ነገሮች እነዚህ ናቸው ፤ አጋንንት በእኛ ላይ ከሚያሰማሯቸው ክፉ ጠላቶቻችን ከሆኑት ከእኩያት ፍትወታትና ከክፋቶች ሁሉ የሚያጠሯት እነዚህ ናቸው::”
ያን እኁም እንዲህ ብሎ ተናገረው ፦ “ልጄ ሆይ ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ መሥዋዕትና መባዕ አድርጎ እስኪያቀርበው ድረስ አባቱን እንደ ታዘዘው እንደ ይስሐቅ ሁን ፤ እርሱ ለአባቱ በመታዘዙ በቤተ ክርስቲያን መዝገብ ውስጥ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ተጽፏልና፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖