አል-ወኪል..
የኀያሉ ጌታህ የአላህ የግል ባሕርዩ ስም ነው፡፡
መጠጊያ፣ መሸሸጊያ ማለት ነው፡፡ መመኪያ ማለት ነው..
የሰው ልጅ ሆይ!
ነገሩ ሁሉ ጭንቅ ሆነ፡፡ መሸሻ፣ መሸሸጊያ ጠፋ፡፡ ጎበዝ ነገሥታት ሁሉ እንደ የሸረሪት ድር ሳሱ፡፡
ሁሉም ነገር ቀጥጥጥ የሚል መሰለ፡፡
በእግር፣ በመኪና፣ በመርከብ፣ በባቡር፣ በአውሮፕላን መንቀሳቀስ ሊቀር ነው የሚል ኀይለኛ ስጋት ተደቀነ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አሁንስ ደካማ መሆንህ፣ ክንድህ የዛለ መሆኑ ተሰማህ ወይ??
ዕውቀትህ፣ ገንዘብህ፣ ችሎታህ፣ ጥበብህ፣ ሳይንስህ፣ ቴክኖሎጂህ ከአንተ ተሰውሮ ከወዴት ሄደብህ??
ባዶነት እየተሰማህ ነው?
አዱኒያ በአጠቃላይ ከእነ ምናምኗ ሸክም ሆነችብህን?
በአየር ላይ እንደሚንሳፈፍ "እፉዬ ገላ" ሕይወት ወዲህና ወዲያ አካለበችህ ወይ??
ክንፉ እንደተመታ አሞራ ሕይወት አንገዳገደችህ ወይ??
ለልጆችህ፣ ለገንዘብህ፣ ለሀብትህ፣ ለንብረትህ፣ ለሕይወትህ፣ ለጤናህ...ሰጋህ ወይ? ለእነዚህ የሚሆን ዋስ ጠበቃ አስፈለገህ ወይ??
..በል እንግዲህ ፊትህን በብርሃን የተሞላ ወደ ሆነው "አል-ወኪል" ወደ ተሰኘው ኀያል ስም አዙረው፡፡
ጠፍተህ አትጠፋም፡፡ ወድቀህ አትወድቅም፡፡
በዐዲስ መልክ ከዚህ ኀያል ስም ጋር መተዋወቅ ጀምር፡፡ ..ጥልቅ በሆነው ትርጉሙ ውስጥ ሰጥመህ ግባበት፡፡
ነፍስያህን ከድክመት፣ ከጭንቀት፣ ከብቸኝነት በዚህ፡ኀያል ስም አማካኝነት ገላግላት፡፡
አል-ወኪል..መጠጊያ፣ መሸሻ፣ መመኪያ!!
ምርጥ መጠጊያ የሆነው ኀያሉ አላህ በቂያችን ነው!!
-ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል-
" رب المشرق والمغرب لا اله الا هو فاتخذه وكيلا "
© Abubekeralemu Muhe
✧ https://t.me/ALJUEDDAAWA