ክፍል ሶስት
ሰማያቱን በሙሉ ወደ ታች ትተው ህዋውን ሲመጥቁ ከሲድረቱል ሙንተሀ ግኝተ-ግዛት ደረሱ። ስፍራው ውብ ነው። ረዥም ከእንቁ፣ ከሉል እና ከአልማዝ የተሰሩ መጋረጃዎች ይታያሉ ፤ በመካከላቸው አንድ ሚማርክ ጅረት ይፈሳል። ከጅረቱ ላይ ሚያንዣብበው አረንጓዴ ወፍ
ለስፍራው ውበቱን ጨምሯል፣ ነቢ ሰዐወ በትዕይንቱ ተደንቀው ሳለ ጂብሪል ኮሽ አላቸው፦«ይህ ጅረት ከውሰር የተሰኘው አላህ ያዘጋጀልህ መጠጥ ነው።» ጅረቱ ነቢን ሰ ዐ ወ ትኩረታቸውን ይልቅ ይስበው ጀመር።
ኢና አዕጠይናከ^ልከውሰር…
በትኩረት ሲመለከቱት ከጅረቱ መሀል የሚንሳፈፉት የሉል እና የእንቁ መጠጫ ኩባያዎቹ የሳቸውን ክብር ማላቅያ መሆኑን ተረዱ።
ወደ ጅረቱ ጠጋ ብለው ሊቀምሱት ሲመለከቱት ንፅሀቱ ከወተት ይነፃል፣ ጥፍጥናው ከማር ይልቃል ፣ ሽታው ሚስክን ያስረሳል። ነቢ ሰዐወ እጃቸውን ነክረው ቀምሰው አለፉ። ሲድረቱል ሙንተሀ ግዛቷ ሰፊ ነው። መላዕክት ድንበሯን አያልፉም ፣ መለኮታዊ ግርጆዎች
እዝያ ይጀምራሉ ፣ የምእናን ሩሖች ሲወጡ መዳረሻቸው ከሷ ግዛት ነው ፣ የጅብሪልም ድንበር እዝያው ነው።
ጉዞው ቀጥሏል…
ጅብሪል ዐሰ ከሲድረቱል ሙንተሀ ከፍታ የሚፈቀድለትን የመጨረሻ ድንበር ደርሶ ከመጀመርያው መለኮታዊ ግርጃ ደጅ ላይ ቆም አለ'ና፦«ሙሀመድ ሆይ! ሂድ ወደ ግርጆው
ዘልቀህ ግባ» ብሎ አዘዛቸው።
«በዚህ አይነት አስፈሪ ሁኔታ ላይ እንዴት ብቻህን ሂድ ትለኛለህ? ወዳጅ እንዲህ ያደርጋል እንዴ?» አሉ ነቢ ሰዐወ።
«መሀመድ ሆይ! ይህን ግርጆ ብሻገረው እቃጠላለሁ» ብሎ የጌታውን ብርሀን እንደማይቋቋመው ነገራቸው።
«ወደ አላህ የማደርስልህ ጉዳይ ካለህ ንገረኝ» አሉት።
«ነገ ሲራጥ ሲዘረጋ ኡመትህ እንዳይወድሙ ክንፌን ዘርግቼ እንዳሳልፋቸው አስፈቅድልኝ» …ብሎ ላካቸው።
የመጀመርያውን የተናጥል ጉዞ ሊያደርጉ ወደ ግርጆው ጠጋ ሲሉ ከወርቅ የተሰራ አልጋ የሀር
ፍራሽ ተነጥፎበት ከፊታቸው ተከሰተ።
ነቢ ሰዐወ ከአልጋው ላይ ሲወጡ ጅብሪል ከኋላ ተጣራ፦«ሙሐመድ!!! አላህ ያሞግስሀል።
ስማው ታዘዝም ንግግሩ እንዳያስደነግጥህ።»
ነቢን ሰ ዐ ወ ያንሳፈፈው አልጋ ድንገት ከአድማሰ-ብርሀኑ ውስጥ ነብይህን ጨለጣቸው።
የአላህን የክብር ግርጆዎች በቅፅበት ያቆራርጡም ጀመር።
እያንዳንዱ ተገላጭ ግርጆ ውፍረቱ 500 አመት ለጋላቢ ያስጋልባል። በዚህ ሁኔታ 70 ሺህ ግርጆች ለነቢ ሰ ዐ ወ ክብር ተገልፁ። ግርጆዎችን ሁሉ ተሻግረው ከፍ ሲሉ ምንም አይነት ፍጥረትም ሆነ መላኢካ የሌለበት
ስፍራ መሆኑን ተረዱ። ከማያውቁት አለም የብቸኝነት እና የፍርሀት ስሜት ይሰማቸው ጀመር።
ነቢ ሰዐወ ከፍ አሉ፣ ነቢ "የት" የሌለበት ስፍራ ላይ ያለ "የት" ተከሰቱ፣ ውድህ የልቅናን ዘውድ ከራሳቸው ደፉ ፣ የመለኮት ዙፋን ካካለለበት አፅናፍ ነቢ ሰ ዐ ወ ብቅ አሉ።
ድምፀ-መለኮቱ ተጣራ ከበላይ ውሰድ ብለንሀል ከዚህ ሁሉ ሲሳይ ከቅርበታችንም ሰንቅ ሚስጥርን ባንተስ አይደል እንዴ! ከውኑን ያበራን?
በአድማሱ ፀጥታ እና በስፍራው አስደማሚነት ነቢ ሰ ዐ ወ እየተገረሙ በነበረበት ቅፅበት በአቡ በክር ረዐ ድምፅ፦«እዝያው ቁም ጌታህ ፀሎት ላይ ነው» የሚል ድምፅ ሰሙ።
የአቡ በክር ድምፅ እዚህ ስፍራ ላይ መደመጡ እና በጌታ ስርአተ ፀሎት አፈፃፀም ግራ የተጋቡት ነቢ ሰዐወ ካሉበት ሁነው በማብሰልሰል ላይ ሳሉ...
«የፍጥረታት በላጭ ቅረብ፣ አህመድ ሆይ! ቅረብ፣ ሙሀመድ ሆይ! ቅረብ» የሚል ድምፅ ተሰማ፤ ነብይህም በተዘጋጀላቸው ረፍረፍ ወደ ታጩለት መርተባ ይቀርቡ ጀመር።
ነቢ ሰዐወ ለክብሩ አቀርቅረው፣ አላህ ለሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ መስጠት በተሳናቸው ቅፅበት እጀ-መለኮት(የዱል ቁድራ) ከትከሻቸው ላይ አረፈ።
የእጀ-መለኮቱ ቅዝቃዜ ከትከሻቸው ባረፈ ግዜም ፤ የቀደምትን እና የመፂአንን እውቀት አሰረፀባቸው።
የተለያዩ ዕውቀቶችን፣ ሚስጥረ-ዕውቀትን፣ ዕውቀተ-ምርጠትን፣ ለህዝብ ተደራሽ የሚሆኑ ዕውቀቶችን በሙሉ ከልባቸው ያሰርፅ ጀመር።
«ጌታዬ! በባይተዋርነት እና በፍርሀት ስዋልል የአቡ በክርን ድምፅ ሰማሁ ተገረምኩም ፤ ደጀ-ሰላምህንም በደረስኩ ግዜ ያንተን መፀለይ ሰማሁ፤ አንተ የተብቃቃህ ሁነህ ስለምን ትፀልያለህ?» ብለው ጠየቁት።
«እኔ ለማንም ከመፀለይ የተብቃቃሁ ነኝ፤ ፀሎቴም "ጥራት ይገባኝ፣ ጥራት ይገባኝ፣ እዝነቴ
ቁጣዬን ቀድማለች" እያልኩ ነው።
ወንድምህ ሙሳን ልናናግረው በፈለግን ግዜ ጓደኛው ስለሆነችው በትሩ አውግተነው አላመድነው። አንተንም ፍርሀትህን ልናስወግድ የጓደኛህን ድምፅ አስደመጥንህ» ብሎ መለሰላቸው።
«ሙሀመድ ሆይ! የጅብሪልን መልዕክት ረሳህ? » አላህ ጠየቃቸው?
«አላህ ሆይ! ታውቀዋለህ ብዬ ነው ዝም ማለቴ» ነቢ መለሱ።
«ሙሀመድ ሆይ! የጂብሪልን ጥያቄ ተቀብለናል። ግና እድሉ ለተጎዳኘህ እና ለወደዱህ ብቻ ነው እሚገጥማቸው» አላህ አለ።
«በነብያት ላይ ጀነት ሀራም ናት ፤ አንተ እስክትገባ ድረስ። በህዝቦችም ላይ ሀራም ናት ፤ ህዝቦችህ እስኪገቧት ድረስ» ክብርን አጎናፀፋቸው። እዝያ ስፍራ ላይ በኑር ተጨልጠው ለመዘርዘር ስፋት ያለው ክስተት ተስተናግዶ
በስተመጨረሻም ትልቁን ስጦታ ለነቢ አስረከባቸው።
ነቢም ሰዐወ የተሰጣቸውን የሰላት ስጦታ ለኡመቱ ሊየከፍሉ የዙፋኑን ግዛት ተሰናብተው 50 ሰላት ይዘው ወደ ታች ይወርዱ ጀመር። ጂብሪል ከድንበሩ ቁሞ የነቢን ሰዐወ መምጫ በመጠባበቅ ላይ ነው። እሳቸው ብቅ ሲሉ ይዟቸው ወደ ሰማያቱ ይወርድ ጀመር።
ጉዞ ወደ ታች...ሲድረቱል ሙንተሀ...ሰባተኛ ሰማይ...ስድስተኛ ሰማይ...እዚህኛው ሰማይ
ላይ ሙሳ አስቆማቸው።
«በምን ታዘዝክ?» ነቢን ጠየቃቸው።
«50 ሰላት ተደነገገልኝ» ነቢ ሰዐወ ለሙሳ ዐሰ መለሱለት።
«ኧረ አስቀንስ እንጂ! ህዝቦችህ አይችሉም። የኔ ህዝቦች እኮ ጠዋት 2 ረከዐ ማታ 2 ረከዐ ተደንግጎላቸው እንኳ አልተገበሩትም። ያንተዎቹ ደግሞ በምን አቅማቸው?» ብሎ ነቢን ሰዐወ ወደ መጡበት የአላህ ዙፋን መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 45 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 40ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 35 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 30 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 25 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 20 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 15 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 10 ይዘው መጡ...ሙሳ መለሳቸው።
5 ሰላት አስቀንሰው 5 ይዘው መጡ...ሙሳ አሁንም አስቀንሱ ብሎ መለሳቸው።
«ከደነገገልኝ 50 ሰላቶች ውስጥ 45 አስቀንሼ 5 ብቻ ቀርቷል ፤ ይህንንም ቀንስልኝ ማለት ይከብደኛል። ጌታዬን አፍረዋለሁ።» አሉ። ነቢ አይናፋር ነበሩ።
ያን ሌሊት በተደረገላቸው የጉብኝት ግብዣ የእናት የአባታቸውን ጉዳይ ሳይሆን የኡመቱን ጉዳይ ፈር አስይዘው ወደ ምድር ወረዱ።
አሚን በል!
ስለኛ በለፉት ቁጥር መልካም ምንዳቸውን ለነቢ አላህ ይከፈላቸው። ይከጅሏት ከነበረችው የልዕልና ምስጉን ስፍራ ላይ አላህ ከነ ሙሉ ክብራቸው ያቁማቸው። በዝናብ ጠብታ፣ በአሸዋው ብዛት ፣ በቅጠል በፍሬው የበዛ ሰላት እና ሰላም በሳቸው ላይ ከአዘል እስከ አበድ/ከዝንተ አለም እስከ ዘለ አለም ይውረድባቸው።
አሚን አትልም!!! አሚን
Sefwan Ahmedin
________________________________________
ሲረቱል ሀለቢያ የተሰኘውን ኪታብ በዋናነት የተጠቀምኩ ሲሆን ሌሎች ኪታቦችንም በስፋት
ተጠቅምያለሁ። 4 ስንኞችን ከወረባቦው ሸክ የመድሕ