የጠፋው ሀብት
°°°°°°°°°°°°°
አንድ ታላቅ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ልቤን ነካው ‹‹እውቀት ከሙስሊሞች የጠፋች ሀብት ናት የትም ቢያገኛት ባለቤቱ እሱ ነው›› ይላል፡፡ ወዲያው እነዛ እውቀትን ለመፈለግ ሲሉ ሆዳቸውን በድንጋይ አስረው ቤታቸውን ሽጠውና ሀገራቸውን ጥለው የሄዱት ቀደምት የኢስላም ምርጥ ትውልዶች ትዝ አሉኝ፡፡...
እውቀት ለማግኘት የነበራቸው ጉጉትና ጥረት አሁን ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት ከእውቀት ከራቀው ትውልድ ጋር ሆድና ጀርባ መሆናችን አስገረመኝ ለዚህም ነበር ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሁሌም ‹‹የሚጠቅመኝን እውቀት ሳላገኝ የሚያልፈኝ ቀን ለእኔ በረካ የለውም›› ይሉ የነበሩት፡፡ አቡደርዳዕ (ረ.ዐ) በበኩሉ ስለ አንድ እውነታ ማወቅ ለሊቱን ሙሉ እየሰገዱ ከማደር ይበልጣል የተማረ ሰውና ተማሪዎቹ እጅግ በተከበረ ተግባር ውስጥ ናቸው፡፡ ሌሎች ግን ያለክብር የቀለሉ ናቸው፡፡ ይሉናል፡፡
...
ኢስላም እውቀትን መፈለግ ግዴታ ከማድረጉ በተጨማሪ እውቀትን ፈልጎ ለሚጓዝ ሰው አላህ የጀነትን መንገድ እንደሚያገራለት፣ መላኢኮች በተግባሩ በመደሰት ክንፋቸውን ዝቅ እንደሚያደርጉለት፣ ለወንጀሉ እስቲግፋር እንደሚጠይቁለትና የአደም ልጅ ከሚሠራው ሥራ ሁሉ በላጩ እውቀትን መፈለግ እንደሆነ ነብዩ በተለያዩ ሀዲሳቸው ይነግሩናል፡፡ አላህን የምንፈራውና የምንታዘዘው ባለን እውቀት ልክ ነው፡፡ እውቀት መሪ ሲሆን ተግባር ደግሞ ተከታዩ ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ይህን የጠፋብንን የነብዩን ብቸኛ ውርስ ፈልገን በማግኘት ወደ ተግባር ልንለውጠው ይገባል፡፡
‹‹የዚህን ዓለም ድሎት የፈለገ ሰው እውቀትን ይፈልግ። የመጪውን አለም ድሎት የፈለገ ሰው እውቀትን ይፈልግ። የሁለቱንም ዓለም ድሎት የፈለገ ሰው እውቀትን ይፈልግ።›› ኢማም አሽ-ሻፊዒይ
‹‹ከቻልክ አዋቂ ሁን ካልቻልክ ተማሪ ሁን ይህንንም ካልቻልክ አድማጭ ሁን አራተኛ ግን አትሁን ትጠፋለህና›› ዑመር ኢብኑ አብዱልአዚዝ››
አላህ ይርዳን;;አላህ እውቀት ፈላጊዎች ያድርገን አውቀንም የምንሰራበት አላህ ያርገን፡፡ አሚሚሚሚሚን.
https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg