ሀዘንም ስለርሱ ያዝናል። ዓይንም ቋጠሮውን ፈቶ ያነባል። ደግመህ ደጋግመህ ብታለቅስም የእዝነት ነውና ይገባዋል። ስለኢስላም ዕንቅልፉን ሰውቷል። ስለ ከፍታ ዘመናችን እያለመ ሌቱን በቂያመለይል ያነጋል። እገሊት ተርባ ይሆን እስኪ ይህን ብር ስጧት ይላል። በአላህ መንገድ የተሰው ሰዎችን ቤተሰቦች አይዘነጋም። በባስ እየተጓዘ ስለነርሱ ምቾት ይጨነቃል።
ሰውነቱ ከሲታ፣ እዚህ ግባ የማይባል ስጋ ያልተላበሰ ቀጭን ረጅም። በቀን ትንሽ እንጂ የማይመገብ እንዲሁ ደገፍ ብሎ በጀርባው የሚጋደም። የሶማሊያ መንደሮች ጠንቅቀው ያውቁታል። ዛፎቹ በሚገባ ያስታውሱታል። እርሱ ግን መታወቅን አይፈልግም በኢኽላስ መስራትን ተክኖበታል።
ዕለቱ ሐሙስ እርሱም ፆመኛ ነበር። ከመስጂድ ወደ ታሰረበት ክፍል አመመኝ ብሎ አቀና። ፆመኛ ሆኖ አላህን ተገናኘ። መልካም ስራውን ተቀብሎ ኩልል ካለው የጀነተል ፊርደውስ ጅረት ያስጎንጨው ዘንድ አላህን እማፀነዋለሁ።
➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho