ሙስሊሟ ተማሪ በአክሱም ትምህርት ቤቶች ሂጃብ ለብሳ እንዳትማር የከለከለው በዋነኛነት የትግራይ ክልል መንግስት ሲቀጥል የፌዴራሉ አካል ሙሉ ፍላጎት ስለሆነ ብቻና ብቻ ነው። ተጠያቂዎቹም የችግሩም ባለቤቶችም የትግራይና የፌዴራል መንግሥታት ብቻና ብቻ ናቸው።
ለምን እውነቱን ሸፍኖ ሌላን መውቀስና ማስመሰል አስፈለገ? ቢፈለግ እኮ የክልሉ መንግስት በአንድ ቀን በአንድ መንግስታዊ ትዕዛዝ ብቻ አይደለም ሂጃብን መስጂድ እና የመቀበሪያ ቦታን እንኳን የአክሱም ሙስሊሞች እንዲያገኝ ማድረግ ይችላል።
ታዲያ እውነቱ በዋነኝነት የትግራይ ክልል መንግስት እንዲሁም ሲቀጥል የፌዴራሉ አካል ፍላጎት መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ለምን በጥቂት የአክሱም የሰፈር ፅንፈኞችና ዱርዬዎች ላይ ጥያቄ ማንሳት አስፈለገን? ለምንስ ዛሬስ እዚያው የማስመሰል ጥያቄዎች ላይ ቆምን? ለዚያ ነው ማለት ነው ከፌዴራል እስከ ክልሎች ሁሉም መጅሊስ በሚባል ደረጃ መግለጫ ያወጣበትን ሁሉም ሙስሊም የጮኸበትን አንድ ችግር የማይሆን ተራ ጉዳይን ሰምቶ መልስ የሚሰጥ መንግስታዊ አካል የጠፋው? መልሳቹ በፍጹም አይደለም የሚል እንደሚሆን ግልፅ ነው ። ታዲያ ከዚህ በላይ መንግስታቶች በሙሉ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ያላቸውን ንቀት እና ሙስሊሙ አሁን ያለበት ተጨባጭ እውነት ለማየት ምን ማስረጃ ይቅረብ? ስለዚህ የማስመሰል ጥያቄዎችን አቁመን ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመንቀል የችግሩን ምክንያት ትቶ ሌላ ቦታ መኳተናችንን ካልቆምን ቀጣዩ ጊዜ እጅግ የከፋ ነው።