የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኒቃብ ክልከላን በተመለከተ
የደቡብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በፃፈው ደብዳቤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኒቃብ ክልከላ ማድረጉንና ሴት ተማሪዎች ከትምህርት እና ከፈተና ፕሮግራም መስተጓጎላቸዉን በተመለከተ መፍትሄ እንዲሰጥበት ጠይቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ባደረጉት ዉይይት ከደህንነት ስጋትና ሀይማኖትን ከማንጸባረቅ ጋር ተያይዞ ኒቃብ መከልከላቸዉን በቃል የገለጹላቸዉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኒቃብ የሚለብሱ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት እና ከፈተና ፕሮግራም ተስተጓጉለዉ እንደሚገኙ ጠቅሷል።
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሚመለከታቸዉ የመንግስት ተቋማት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንዲያበጅለት ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን በማለት ደብዳቤውን አጠናቋል።