.የተሳቀ እንባ
#ክፍል_²
(ፉአድ ሙና)
.
.
.
ኢስማኢል ከመኪናው ወርዶ አጎንብሶ ወደ ውስጥ ሲመለከት ኤርሚ እና ቤቲ መኪናው ውስጥ መቆየት እንደሚፈልጉና ከሀዩ ጋር መኪናውን እንዲለቁላቸው ጠየቋቸው። ሀያት የመኪናውን በር ከፍታ ወረደች። ያደረገችው ቋቋ ጫማ ነው። ልቧ ከወትሮው በተለየ ይመታል። የኢስማኢል ወንዳወንድነት ገና እንዳየችው ቀልቧን አጥፍቶታል። እየተራመዱ ወደ ሬስቶራንቱ ሲገቡ ጫማዋ ደንቀፍቀፍ አደረጋት። እስማኢል ሊደግፋት በሚመስል መልኩ እጇን ያዛት። የባሰ የልቧ ምት ተዘበራረቀባት። አተነፋፈሷ ተስተጓጎለ። እጇን መያዙን ያልወደደች ለመምሰል ኮስተር ለማለት ሞከረች። ከንቱ ሙከራ ፣ በልቧ የተፎረሸ ቀሽም ሙከራ። ሬስቶራንቱ ውስጥ ገብተው ወደ ፎቁ ወጥተው ተቀመጡ። ትንሽ እንደቆዩ አስተናጋጅ መጣ። መታዘዝ ባይፈልጉም ለመቀመጥ ሲሉ ሁለቱም ጁስ አዘዙ። የመጀመሪያ ቀን እንደመገናኘታቸው ብዙ ጠለቅ ያለ ወሬ አያወሩም። ስለ ትምህርቷ ፣ ስለ ስራው ብቻ ፤ ወሬው ከዚህ አይዘልም። እስማኢል ከሀያ ሁለት ዓመት አይዘልም። እሷ ደግሞ ገና አስራስምንት አመት አልሞላትም።
"ዎክ ብናደርግስ እዚህ ከምንቀመጥ?" አለ ኢስማኢል።
ትንሽ ተግደረደረችና "እሺ" አለች።
ከመቀመጫቸው ተነስተው ከሬስቶራንቱ ግቢ ወጡ። መኪናው ውስጥ ኤርሚና ቤቲ በስሜት ግለት ታፍነው የስሜታቸውን እሳት በመዳፎቻቸውና በከንሮቻቸው እየተነፈሱት ነው።
ኢስማኢልና ሀያት አስፓልቱን ተሻገሩ። አካባቢው ላይ በክፍት ብረት የታጠረ ግቢ አለ። የሜድሮክ ግቢ ነው። የአጥሩ ዙሪያ የድንጋይ መቀመጫ አለ። ኢስማኢል ተመቻችቶ ተቀመጠ። ቀና ብሎ ሲመለከታት እሷም ተቀመጠች። እንደምንም ራሱን አደፋፍሮ ክንዱን ከአንገቷ ላይ አሳረፈ። አቀፋት። አካባቢው ላይ ሰው አይበዛም። አንዳንድ ሰዎች በመንገዱ ላይ ሲራመዱ ይታያል። ሀያት እና ኢስማኢል አንድ ድንጋይ ላይ ለሁለት ተቀምጠዋል። በመካከላቸው ምንም አይነት ክፍተት የለም። ደግሞ ኢስማኢል ክንዱን ዘርግቶ አቅፏታል። ከሩቅ ለሚያያቸው የቆዩ ፍቅረኞች እንጂ ዛሬ የተገናኙ ፤ ከዚህ ቀደም የማይተዋወቁ አይነት ሰዎች አይመስሉም።
የሀያት ልብ ሰላሙን አጥቷል። ከኢስማኢል ደረት የሚፈልቀው የሽቶው ጠረን ፣ ልቧ የቀለጠለት ወንዳወንድ የሰውነት ቅርጹ ፣ የሚያምረው የፊቱ ገፅታ ፣ ምናልባትም ኤክስኪዩቲቭ መኪናውም ትንሽ ገፅታውን ሳያጎላው አይቀርም ፤ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው እጅ አሰጥተዋታል። አሁንም እንዳቀፋት ናት ፤ እየተንሾካሾኩ ፣ ብዙም ውበት በሌለው ድምጿ ፣ በጎረነነ ድምፁ እየተግባቡ። ሀያት እራሷን መቆጣጠር ከበዳት። ብዙዎቹ ሴቶች በፍፁም ደፍረው የማያደርጉትን ነገር ለማድረግ አሰበች። ልትጎርሰው ፣ ከንፈሩ ላይ ልትለጠፍ። "ደግሞ ቢንቀኝስ?" ብላ ተጨነቀች። "የለመደች ባለጌ ናት ብሎ ቢያስበኝስ?" ብላ ተብሰለሰለች። ግን የኢስማኢል ወንዳወንድነት ፣ የልቧ እጅ መስጠት ፣ ስሜቷን የመግታት አቅም አለመኖር ተደራረቡና ሀፍረቷን ገፈፉት። ካቀፋት ክንዱ ወደ ቀኝ ዞረች። እጇን ወደ አንገቱ ወስዳ ከፊቷ አቀረበችው። ከንፈሩን ጎረሰችው። ኢስማኢል አንገቷ ላይ የነበረው እጁ ወደ ታች ወርዶ ወገቧን ይዟል። "እሷ ከጀመረችልኝማ ምን ገዶኝ" የሚል ይመስላል። በደንብ ይስማታል ፣ በደንብ ትስመዋለች።
መንገዱ ላይ ውር ውር የሚሉት ሰዎች ከአስፓልቱ ዳር ተቀምጠው የሚሳሳሙትን እነኢስማኢልን ከመጤፍ አልቆጠሯቸውም። ተዉ ያላቸው የለም። የገላመጣቸው እንኳ አልነበረም። ሰዉ "ጊዜያቸው ነው" እያለ ትቷቸው ይነጉዳል። አሁን አንዱን መንገደኛ አስቁመን አስፓልቱ ጥግ ላይ የሚሳሳሙትን እነኢስማኤልን እያሳየን "ከተገናኙ ሁለት ሰዓት እንኳ በቅጡ አልሞላቸውም።" ብንለው ያምነናል? አይመስሉማ! አይመስሉም። ግን ስሜታቸው ስለ ምክንያታዊነት እና ስለ ድርጊታቸው ውጤት ለማሰብ ጊዜ አልሰጣቸውም። ብቻ ይሳሳማሉ።
.
ተሳስመው ሲረግቡ ፣ እግሮቻቸው መሀል እንደረጠቡ ፣ ቅድም በመካከላቸው የነበረው ሀፍረት ተገፎ ፣ እየተሳሳቁ እጅ ለእጅ ተያይዘው እየተላፉ ሬስቶራንቱ በር ላይ ወደ ቆመው የኢስማኢል መኪና ሄዱ። ቤቲ እና ኤርሚያስ የከንፈር ጨዋታቸውን ጨርሰው ነበር። ኢስማኢል እና ሀያት ወደ መኪናው ገብተው ቅድም በተቀመጡበት መልኩ ተቀመጡ። ሀዩ ጋቢና እንደተቀመጠች ወደ ኋላ ዞራ ቤቲን አየቻትና ሳቀች።
ቤቲ ሳቀችና "ኧረ ሀዩ ሊፒስቲኩስ? ተመቻቻቹ አይደል?"
ሀያት እና ኢስማኢል ተያይተው ተሳሳቁ። ኢስማኢል መኪናውን አስነስቶ መንዳት ጀመረ። ሰዓቱ ወደ አንድ ሰዓት ለመሆን እየተቃረበ ነው። መኪናቸው ካርል አደባባይ ጋ ሲደርስ በመከላከያ የጀርባ አጥር እየታከከ ውስጥ ለውስጥ ሄዶ ሞቢል ጋር ወጣ። ሀሳባቸው ቤቲ ሰፈሯ አለምባንክ ስለሆነ እስከ ጦርሀይሎች ሊሸኟት ነው። ጦርሀይሎች ሲደርሱ ቤቲን አሰናብተው ሀያትን ሰፈሯ ለማድረስ ወደ ተክለሀይማኖት ነዱት። ኤርሚያስ ከኋላ ተቀምጦ በመኪናው ቴፕ ከተከፈተው ዘፈን ጋር አብሮ ጭንቅላቱን በስልት ያነቃንቃል። ተክለሀይማኖት ሲደርሱ ኢስማኢል ስልክ ቁጥሯን ተቀበላት። የሱንም ሰጣት። ልትወርድ ስትል ኤርሚያስ እየሳቀ "ይኸው አይኔን ጨፍኜያለሁ አላያችሁም" አለ።
ኢስማኢል ከንፈሯን ስሞ ተሰናበታት።
.
ሀያት ከመኪናው ወርዳ ወደ ሰፈሯ የሚያስገባውን መንገድ እየተራመደች ከቦርሳዋ ውስጥ ቻፒስቲክ አውጥታ ከንፈሯን ተቀባች። ስትወጣ በነበረበት ሁኔታ እናቷ እንድታያት በማሰብ ራሷን ስትወጣ በነበረችበት ሁኔታ ላይ ለመመለስ ሞከረች። ሁሉም ነገር ተዓምር ሆኖባታል። "እንዴት ባብድለት ነው?" ትላለች ራሷን እየታዘበች። ከሰዓታት በፊት ያደረገችው ሁሉ እየገረማት።
ቤት ስትገባ እናቷ ስመው ተቀበሏት። ታናሽ እህቷን አቅፋ ጣቷን እያጮኸች እያጫወተች ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች። ሀያት ለእናቷ የአይኗ ስስት ናት። ለሷ ዛሬም እንቦቀቅላ ናት። ለሷ ምንም የማታውቅ ጨዋ ናት። ልጃቸው ከንፈሯ ዛሬ ሁለት ሰዓት እንኳ አብራው ባልቆየችው ሰው እንደተሳመ ቢነገራት ምናልባት ምድር ላይ በህይወት መኖሯን አምርራ በጠላች ነበር። እናት ናት፣ እናት ፣ ለልጇ ትልቅ ወግ ማዕረግ የምትመኝ እናት።
.
ሀያት መኝታ ክፍሏ ተቀምጣ ኢስማኢል ጋር ስለመደወል አሰበች። እንደ ጅል ለብቻዋ እየሳቀች ስልኳን አየችው።
.
𝔭𝔞𝔯𝔱 = ³ ይቀጥላል...
.
https://t.me/HANIF_TUBE01
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
╭─────────────
╰──➤ ✎ ❤️🩹𝕙𝕒𝕟𝕚𝕗