በወርሃ ረጀብ የመጀመሪያው መሥራት ያለብህ ነገር፤ ወንጀል መፈፀምን ማቆም ነው‼
የረጀብ ወር ወንጀል በወርሃ ረመዿን ኑርህን ያጠፋዋል። የኢማን ጥፍጥናህን ይቀንሰዋል። ገና ከወዲሁ ነፍስያህን ከወንጀል በማቀብ ለረመዿን አዘጋጃት። ሶላት ኢቃም ከተባለ በኋላ እየተሰገደ እየሮጠ ሂዶ የሚደርስ ሰውና ቀድሞ ሂዶ ቀብሊያ ሱንናዎችን ሰግዶ፣ በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባለውን ዱዓእ አድርጎ፣ ኢቃም ሲባል ረጋ ብሎ ተነስቶ የሚሰግዱ ሰዎች እኩል የመረጋጋት መንፈስ እንደናይኖራቸው ሁሉ፤ ገና ከረጀብ ጀምሮ ነፍሱን ከወንጀል አቅቧት፣ ኸይር ሥራ እያለማመዳት ለረመዿን ያዘጋጀና ልክ «ረመዿን ነገ ነው!» የተባለ ምሽት ጀምሮ የሚዘጋጅ ሰው እኩል ውጤታማነት ላይኖራቸው ይችላል። ነፍሱን ቀድሞ ስላላለማመዳት አንዳንድ ጊዜ ተንሸራቶ በረመዿንም ወንጀል ሊፈፅም ይችላል። አላህ ይጠብቀንና!
ዛሬ ረጀብ 01, 1446 H.C. ነው። ረመዿን ድፍን 2 ወራት ይቀሩታል።
በረጀብ ወር የሚፈፀም የተለዬ ሶላት፣ ጾም ወይም ልዩ ዒባዳህ የለም። ረጀብ ነፍስ ይበልጥ ከማይበደልባቸው አላህ እርም ካደረጋቸው 4 የአመቱ የተከበሩ ወራት መካከል አንዱ ስለሆነ፤ በዚህ ወር በፍፁም ወንጀል ላይ ልትወድቅ አይገባም
ሸይጧን ሲወሰውስህ፤ አዑዙ ቢላህ ብለህ ራስህን ካለህበት ቦታ ተንቀሳቅሰህ ቀይር። አላህ ያግዘን‼