# የስኳር በሽታ እና የአይን ጤና: ማወቅ ያለብዎት
የስኳር በሽታ በአይን ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከፍተኛ የደም ስኳር መጠን በአይን ውስጥ ያሉትን ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ይጎዳል፣ ይህም ወደ ሬቲና መጎዳት እና እይታ ማጣት ሊያመራ ይችላል።
የስኳር ሬቲና በሽታ (Diabetic retinopathy) ሁለት ዋና ዋና አይነቶች አሉ:
1. የደም ስር ያላበቀለ (Non prolifrative diabetic retinopahty): በዚህ ሁኔታ በሬቲና ውስጥ ያሉ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ይዳከማሉ እና ደም ይፈስሳል።
2. የደም ስር ያበቀለ (prolifrative diabetic retinopahty): በዚህ ሁኔታ አዳዲስ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ያድጋሉ እና እይታን ሊያሳጡ ይችላሉ።
የስኳር ሬቲና በሽታ ምልክቶች:
• የእይታ ብዥታ
• ቀለማትን ለመለየት መቸገር
• የእይታ መቀነስና ማጣት
መፍትሄዎች:
• የደም ስኳር መጠን መቆጣጠር: ከሀኪም ጋር በመነጋገር አመጋገብን ማስተካከል፣ መድሀኒትን በተገቢው ሰዓትና ተገቢውን መጠን መውስድ እና ቋሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ።
• የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር
• ሲጃራ ማጤስ ማቆም
• የአይን ሀኪም መጎብኘት: የስኳር በሽታ ካለቦት ምንም አይነት የእይታ ችግር ባይኖርቦትም እንኳ የአይን ሀኪም ጋር በየጊዜው መሄድ አለቦት።
የስኳር ሬቲና በሽታን መከላከልና እይታዎን መጠበቅ ይችላሉ። ከሀኪምዎ ጋር በመተባበር እና አስፈላጊ ከሆነ በአይን ሀኪም በኩል የተገቢውን ህክምና በማግኘት የአይን ጤናዎን ማስጠበቅ ይችላሉ።
#HealthHubET #የስኳርበሽታ #የአይንጤና #DiabeticRetinopathy
@HHETatI