Репост из: ገድለ ቅዱሳን
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን #ለሐዋርያውና_ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ፖሊካርፐስ ለዕረፍቱ በዓል፣ ለክቡር #ለቅዱስ_ፋሲለደስ ልጅ ለከበረ #ለቅዱስ_አውሳብዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከምስራቃዊ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ አገልጋይ #ከቅዱስ_አውስግንዮስ ከምስክርነቱ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያውና_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ፖሊካርፐስ፦ ይኽም ቅዱስ ሐዋርያና ሰማዕት የሆነው ፖሊካርፐስ ከ70 ዓ.ም እስከ 156 ዓ.ም የነበረ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራእዩ ከመሰከረላቸው ከ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ ይኸውም የሰርምኔስ ዻዻስ የነበረ ነው፡፡ ይኽም ቅዱስ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ቃል በቃል የተማረና ደቀ መዝሙሩ የነበረ ነው፡፡ አቡነ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ የቅዱስ ፖሊካርፐስ ባልንጀራው ነበር፡፡ ቅዱስ ፖሊካርፐስ ከ46 ዓመታት በላይ በፍጹም ትጋት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎ አረማውያን በ86 ዓመቱ በአደባባይ በእሳት አቃጥለው በሰማዕትነት አርፏል፡፡
❤ የቅዱስ ፖሊካርፐስ የሰማዕትነቱ ዜና የተገኘው የራሱ የሆነችው የሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን ሰማዕትነቱን በአካል በተከታተሉ ወንድሞች አማካኝነት ጽፋ ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ከበተነችው መልእክት ነው። በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት የሰማዕትነታቸው ሁኔታ፣ ሳይፈሩ ሰውነታቸውን ለሰይፍ ለስለት እንዴት እንደሰጡ፣ ስለ ክርስቶስ ለመመስከር እንዴት ይጨክኑ እንደነበር በሙሉ ዜና ገድላቸው እየተጻፈ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ይሰራጭነበር። እንደ አግናጥዮስ ሁሉ በሮም ፖሊካርፐስ ሰማዕት በሆነበት ጊዜም በሰምርኔስ ከተማ የሕዝብ በዓል ተደርጎ ነበር:: እንደልማዳቸው በዓሉ በሚከበርበት በእስታድየማቸው የአራዊት ትርኢት ነበር። አሬኒከስ የተባለ አንድ ክርስቲያንም "የአሕዛብ ጣዖታትን ካላመለክህ ለአራዊት እንሰጥሃለን" ብለውት አሻፈረኝ ብሎ በመፅናቱ በዚያ በአራዊት ተበልቶ ሰማዕት ሆነ። በዚህ ጊዜም ሕዝቡ "ክርስቲያኖች እንዲህ እንዲፀኑ የሚያስተምራቸው ዋነኛው ፖሊካርፐስ ነው እርሱ ተይዞ ይምጣ" እያሉ ጮሁ።
❤ ቅዱስ ፖሊካርፐስ የሞት ፍርድ ሲፈረድበት ፀንቶ በከተማዋ ቢቆይም ምእመናን እንዲሸሽ እያለቀሱ ስለለመኑት ባጠገብ ወዳለች መንደር ሸሸ። በዚያ ሳለ ሰማዕት እንደሚሆን በራእይ ተረድቶ እንደሚሞት ለወንድሞችና እህቶች ነገራቸው። ወዲያው በጥቆማ ተይዞ ወደ ሰምርኔስ ከተማ እያንገላቱ ወስደው ሕዝብ በተሰበሰበበት በበዓሉ አደባባይ አቆሙት። እርሱም ክርስቶስ በሕዝብ አደባባይ ቆሞ የተቀበለውን መከራ እያሰበ የመከራው ተካፋይ ስላደረገው በፍጹም ደስታ መከራውን ይቀበል ነበር። በሕዝቡ ፊት አቁሞ የሚያናዝዘው ሹም ክርስቶስን እንዲክድ ብዙ ማግባቢያዎችንና ማስፈራሪያዎችን ቢያቀርብለትም ያለፍርሃት ፀንቶ ክርስቲያንነቱን ስለመሰከረ በእሳት እንዲቃጠል ተፈረደበት። ወታደሮቹ እሳቱ ውስጥ ከገባ
በኋላ የሚያመልጠን መስሏቸው ለማጠር ሲዘጋጁ አይቶ "ወደ እሳቱ እንድገባ ያበረታኝ ጌታዬ በእሳቱ ውስጥም ፀንቼ እንድቆይ ያስችለኛል" አላቸው።
❤ ወታደሮቹ እጅና እግሩን አስረው ወደ እሳቱ ሲያቀርቡት አይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ በማለት የመጨረሻ ጸሎት አደረገ፦ "አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር የተወደደው ልጅህ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ በልጅህ አንተን እንድናውቅ ሆነናል። የመላእክትና የኀይላት እንዲሁም የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ አንተ ነህ፤ ፍጥረታትም ሁሉ የሚኖሩት ባንተ ነው በመንፈስ። ቅዱስ አጋዥነት ለዘላለማዊ ሕይወት ትንሣኤ ያለፍርሃት ከክርስቶስ መከራ ተካፋይ ከሆኑት ከሰማዕታት ወገን እንድቆጠር ስላደረግኸኝ እና በዚህች ቀንና ሰዓት በሚገባ ስላስተማርኸኝ አመሰግንሃለሁ። እንደ እነርሱ ዛሬ በፊትህ ተቀብያለሁና እንደ መልካምና የተወደደ መሥዋዕት አድርገህ ተቀበልልኝ። አንተ አስቀድመህ እንዳሳየኸኝ እና እንዳዘጋጀኸኝ አንተ እውነተኛና ታማኝ አምላክ ነህና ስለሁሉ ነገር አመሰግንሃለሁ፣ አከብርሃለሁ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። ከሰማያዊው ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት ከተወደደው ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን!።"
❤ የጸሎቱ ይዘት ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ከምታስተምረው ምሥጢረ ሥላሴ ጋር አንድ አይነት ሲሆን ይህንኑም የመሰለ ጸሎት አላት። በዚህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጥንታዊና ከምንጮቹ ከሐዋርያት የተረከበችው ለመሆኑ ታላቅ ማስረጃ ነው። ቅዱሱ ጸሎቱን ሲጨርስ በእሳቱ ውስጥ ወረወሩት። በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ተአምር የሚሠራ እግዚአብሔር ለምእመናን መጽናኛ የሚሆን ድንቅ ተአምርን አደረገ። እሳቱ የቅዱሱን ሰውነት ዙሪያውን እንደግድግዳ ከቦ የማያቃጥለው ሆነ። ሕዝቡም እሳቱ እንዳላቃጠለው ባዩ ጊዜ "በጦር ተወግቶ ይሙት" እያሉ ጮሁ፤ ወታደሮቹም በጦር ወጉትና በዚህ ሰማዕትነቱን ፈጸመ። ክርስቲያኖች እንዳያመልኩት በሚል የከበረ ሥጋውን አቃጠሉ፤ በዚህ ጊዜ ደስ የሚያሰኝ የእጣንና የሽቶ መአዛ ሸተተ። ክርስቲያኖችም ተረፈ አፅሙን በክብር ወሰደው ቀበሩት ቤተ ክርስቲያንም በስሙ ሠሩለት። ከቅዱስ ፖሊካርፐስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከት ያሳትፈን በጸሎቱ ይማረን!።
✝ ✝ ✝
❤ #የቅዱስ_ፋሲለደስ_ልጅ_ቅዱስ_አውሳብዮስ፦ ይህም የከበረ ፋሲለደስ ለአንጾኪያ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ነው። ለመንግሥት ልጅችም አባታቸው ነው እርሱም ከፋርስ ሰዎች ጋር ጦርነት ውስጥ እያለ ዲዮቅልጥያኖስ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክርስቶስን ክዶ ጣዖትን እንዳመለከ ሰማ። እጅግ አዝኖ ወደ ልጁ ወደ አውሳብዮስ ልኮ ይህን ነገረው የከበሩ የቤተ መንግሥት ሰዎች ዘመዶቹን ዳግመኛ ጠራቸው እነርሱም የንጉሥ ልጅ ዮስጦስ፣ አባዲር፣ ገላውዴዎስና ቴዎድሮስ ከእርሳቸውም ጋር ያሉትን ጠርቶ ስለ ከሀዲው ንጉሥ ነገራቸው። ሁሉም እጅግ አዘኑ ዳግመኛም እንዲህ አላቸው "እኔ ደሜን አፈሳለሁ" ሁሉም በዚህ በጎ ምክር ተስማምተው እርስ በርሳቸው ተማማሉ። ጠላቶቻቸውንም ድል አድርገው ወደ አገራቸው በተመለሱ ጊዜ ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋር ወጥቶ በደስታ ተቀበሏቸው።
❤ ከዚህም በኋላ የቅዱስ ፊቅጦር አባት ህርማኖስ ለቅዱሳኑ ጣዖትን እንዲአቀርብላቸውና እንዲሰግዱለት ንጉሡን መከረው ንጉሡም ህርማኖስ እንደ መከረው አደረገ። በዚያንም ጊዜ ቅዱሳንን ጠርቶ እንዲህ አላቸው "እኔ እጅግ እንደምወዳችሁ እናንተ ታውቃላችሁ አሁንም ለአጵሎን ሰግዳችሁ ልቤን ደስ ታሰኙ ዘንድ ከእናንተ እሻለሁ"። ቅዱሳንም ሰምተው እጅግ ተቆጡ አውሳብዮስም ንጉሡን ሊገድለው ሰይፋን መዘዘ ንጉሡም ሸሽቶ ተሸሸገ ከንጉሥም ባለሟሎች ብዙዎችን ሥራዊቱንም ጭምር ገደለ የከበረ ፋሲለደስም ባይከለክላቸው ከንጉሥ ቤት ምንም ሰው ባልቀራቸው ነበር።