ኦቦ ኃይለ ማርያም ገመዳ የማጫና ቱለማ ማህበር ፈጣሪ ነው።
ኦዳና ቁቤ በመጫና ቱለማ ማህበር አርማ እንዲሆን ያስገባ በኦሮሞ ባንዲራ እምብርት ላይ ኦዳ እንድቀመጥ ሃሳብ ያቀረብ የተማረ ንቁ ብሄርተኛ ነው።
ከድሃ ቤተሰብ የተወለደ የታሪክና ህግ አዋቂ ነበር። ትውልዱ ሰላሌ ጂዳ ነው። በጣሊያን ጊዜ ዘምቶ...ጣሊያንን ተዋግቶ፥ በጣሊያን ተማርኮ ሶማሊያ ተወስዶ ታስሮ ነበር። ኃይሌን በቅርበት የሚያውቁት ሲመሰክሩ በዚያ ትውልድ ዘመን በርሱ ደረጃ የሚገኝ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ነበረ ለማለት እንቸገራለን ይላሉ። እነ ኮሎኔል አለሙ ቂጤሳ ግን አድንቀውት አይጠግቡም ነበር፣ ጠላቶችም በንቃቱና በጀግንነቱ ያደንቁታል።..
ኃይለማርያም እንደሚያጠፉት ያውቅ ነበር። አፄ ኃይለስላሴም በሚገባ ያውቁታል።በጥብቅና ሙያው፣በይግባኝ ለደምበኞቹ ሞግቶ አያሌ ጊዜያት አፄ ኃይለስላሴ ፊት ቀርቧል። አፄው በተደጋጋሚ አይተውት ድንቅ ችሎታው አስገርሞዋቸው ነበር።
እጅግ ከመደነቃቸው የተነሳ የማን ልጅ እንደሆነ ለማወቅ የማንስ ልጅ ነህ ብለው ስጠይቁት ፣ " ጃንሆይ ኃይለማርያም የገመዳ እባላለሁ አላቸው። ጃንሆይ የሚያውቀት ባላባት መስሎዋቸው፣ "የኛው ገመዳ ልጅ ነሃ!" ሲሉት፣ የለም ጃንሆይ! እኔ እርሶ የማያውቁት የድሃው ገመዳ ልጅ ነኝ" አላቸው።፣ እርሳቸውም በኃይሌ አባባል እንደ ተገረሙም፣እንደ ደነገጡም ይነገራል።
ጀግናው የአንድነት አቀንቃኝ ኮሎኔል አለሙ ቂጤሳ ኃይለማርያም ቀርቦ ኦሮሞን አንድ የሚያደርግ ማህበር እንመስርት አለው። ኃይለማርያም እሺ ብሎ ቁቤና ኦዳና የማህበሩ መተዳደሪያ ደምብ እንድሆን አዘጋጅቶ አቀረበ። አስቀድሞ የሸዋ ቱለማ መረዳጃ ማህበርን መስርቶም ይንቀሳቀሰ ስለነበር የራሱንም ማህበር በአዲሱ ማህበር ጋር አዋሃዶ ህጋዊ ፈቃድም አግኝተው ስራ ጀመሩ። ኃይለ ማርያም ኦሮሞ ያልሆኑትን ኢትዮጵያዊያን "ወንድምህን እንደ ራስህ ውደድ..." በሚለው መርህ ይመለከት ነበር ። የመጫና ቱለማ ማህበር ፈጣሪ የመተዳደሪያ አርቃቂና ዋና ፀሐፊ ሆኖ በቢሮውን 24 ሰዓት ያገልግል ነበር።
በግፈኞች አይን ገብቶ ልያጠፉት ምክንያት አግኝተው በጀግና ላይ ሞት ፈረዱ። ብሔርተኞችን ለማጥፋት በአላቸው አላማ በተከታታይ ሻምበል ማሞ መዘምርና ጄነራል ታደሰ ብሩ ላይ ሞት ፈረዱ ። ሌሎችን በእስራት ቀጡ።! ጄነራል ዳዊት አብዲና ኦቦ ኃይለማርያም በግዞት ተሰቃዩ፣ ታመሙ፣ ህክምናም ተከለከሉ! እነ ኮሎኔል አለሙ ጎንደር ተወስደው ታሰሩ። ሰይፉ ተሰማ ጋሞጎፋ ተወስዶ፣እስር ቤት በስውር ተገደለ።
የኦሮሞ ዘር ናቸው የሚባሉ ራስ እምሩ የኃይለማርያም ስቃይን አይተው አዝነው አፄ ኃይለስላሴን ህክምና እንድፈቅዱለት ተማፀነ።... "እሺ እፈቅዳለሁ፣ ግን የመጫና ቱለማ ዋና ቀማሚ ኃይለማርያም መሆኑን አትርሳ" አለው።
ህክምናው በጣም ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ስለተፈቀደ የመዳን እድሉ የመነመነ ነው ። የነፍጠኞች ግፍና ጭካኔ ከፋሽስት ይበልጣል። ኃይለማርያም ታሞ እየተሰቃዬ በቃሬዛ ተሸክመው የፍርድ ቤት ችሎት እንዲከታተል አደረጉ ።
በመጨረሻም አፄው ፈቃደኛ ሆነው ህክምናው ሲፈቀድለት የመጫና ቱለማ አመራሮች ተደሰቱ ።፣.....ኃይለማሪያም በህክምና እንደማይድን ያውቅ ነበር።
ከእስር ቤት ወደ ሆስፒታል በቃሬዛ ስወሰድ ለተሰበሰቡ ወዳጆቹ የመጨረሻ መልዕክቱን አስተላለፈ።"ታክሜ፣ድኜ ዳግም አገኛችኋለሁ ብዬ ተስፋ አላደርግም። የኔ ነገር ፍፃሜው ላይ ደርሷል።ከእንግዲህ የኦሮሞ ነገር ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አይመለስም። የለኮስነው ሰላማዊ ትግል መሠረቱ አይነቃነቅም፣ወደ ኋላም አይመለስም። በአጭሩ የኦሮሞ ትግል አሁን በቂጥ ሆድ እንደገባ እባብ ነው። ከጎተቱት ይበጠስና መርዙ ውስጥ ይቀራል። ካልወጣ ሙሉ በሙሉ ወደ ውስጥ ይገባል።በምንም ተስፋ አትቁረጡ ፣በርቱ፣ እጅ የማይሰጥ ትውልድ አፍርተናል..." ብሎ ተሰናበታቸው።
የዚህ ጀግና ታሪክ የጻፈ የኦሮሞ ምሁር የድህረ ምረቃ ተማሪ ነው ።ጀግኖች ይሞታሉ። ግን አላማቸው ታሪካቸው ሥማቸው ለዘለአለም ይኖራል። የግፈኞች ታሪክ ለዘለአለም ተቀብሮ ይቀራል።
ኦሮሞ እዚህ የደረስው በሰው ልጆች ላይ ተደርጎ የማይታወቅ ግፎችን አልፎ ነው ።
🙏 Bulto Bena