ጣፋጭ ኩርኩም
~
ህንዳዊ ሃኪም ነው። ፂሙ ከደረቱ ደርሷል። አንድ ፂሙን የላጨ በቁርኣንና ሱና ላይ የጠለቀ እውቀት ያለው የአዝሀር ሊቅ ጋር ተገናኘ። ህንዳዊው ስለ ፂም ጠየቀው።
የአዝሀሩ ሊቅ፡ "ፂም ማሳደግ የፈፀመው የሚመነዳበት፣ የተወው የማይቀጣበት ሱና ነው" ብሎ መለሰለት።
ህንዳዊው ሃኪም፡ "እኔ ምንም እንደምትል አላውቅም። ግን የአላህ መልእክተኛ እንደኔ ናቸው? ወይስ እንዳንተ? " አለው።
አዝሀሪዩ ፡ "አይ እንዳንተ ናቸው" ብሎ መለሰ።
[ሸርሑል ሙሐረር፡ 114]
* አንዳንዱ በእውቀት ካንተ ቢያንስ እንኳ አሻራው እድሜ ልክህን የማይጠፋ ቁንጥጫ ይሰጥሃል።
እይታህ ቢለይ እንኳ ከፍ ያለውን መምረጥ ላይ አይንህን አትሽ።
{ أَتَسۡتَبۡدِلُونَ ٱلَّذِی هُوَ أَدۡنَىٰ بِٱلَّذِی هُوَ خَیۡرٌۚ }
"ያንን እርሱ ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ እርሱ በላጭ በሆነው ነገር መለወጥን ትፈልጋላችሁን?" [አልበቀረህ፡ 61]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor