#1 አሸናፊዎችም ተሸናፊዎችም ተመሳሳይ ግቦች አሏቸው።
ግቦችን ማስቀመጥ ስኬታማዎች በማድላት መድሎ (survivorship bias) በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቃ ነው። ትኩረት የምናደርገው አሸናፊ ሆነው በጨረሱት ወገኖች ላይ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ለውጤት ያበቃቸው የተለጠጠው እቅዳቸው እንደሆነ አድርገን እናስባለን። ተመሳሳይ ግቦችን አስቀምጠው ሩጫቸውን በተሸናፊነት የቋጩ ተወዳዳሪዎችን ግን አናይም፡፡
የትኛውም የኦሎምፒክ ተወዳዳሪ የወርቅ ሜዳሊያውን ማሸነፍ ግቡ ነው፡፡ የትኛውም ምሩቅም ስራ ማግኘትን ያልማል። ውጤታማ የሆኑም፤ ውጤታማ ያልሆኑም ሰዎች ተመሳሳይ ግቦችን የሚጋሩ ከሆነ በተሸናፊዎችና በአሸናፊዎች መካከል ለተፈጠረው የስኬታማነት ልዩነት ምክንያት ግቦችን ማስቀመጥ አይደለም ማለት ነው።
ስለሆነም ግቦች ሁልጊዜም ነበሩ። በኋላ ውጤት ያመጣው ለየት ያለው ነገር በቡድኑ ላይ በየቀኑ መሻሻልን ያመጡ የሂደቱ ሁኔታዎች ናቸው፡፡
#2 ግብን ማሳካት ቅጽበታዊ ለውጥ ብቻ ነው
የመኖሪያ ክፍልህ በጣም ስለቆሸሽ ልታፀዳው ግብ አስቀመጥክ እንበል፡፡ ጉልበትህን አሰባስበህ ወደ ሥራ ከገባህ ንፁህ ክፍል ይኖርሀል - በዚያች ቅጽበት፡፡ ይሁን እንጂ አስቀድሞም ቆሻሻ ክፍል እንዲኖርህ ወዳደረገው ባህሪህ የምትመለስ ከሆነ ክፍልህ እንደገና ይቆሽሻል፡፡ እንደገና ለማፅዳትም ሌላ ብርታት መፈለግ ይኖርብሃል፡፡ ሂደቱን ባለመቀየርህ ምክንያት በተለያየ ጊዜ ተመሳሳይ ውጤት ስታባርር ትኖራለህ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱን ሳያስወግዱ ምልክቶቹን ብቻ እንደማከም ነውና፡፡
ግብን ማሳካት ሕይወትን የሚቀይረው ለቅጽበታት ብቻ ነው፡፡ ይህ ስለ መሻሻል ያለ የስሜት ግብረ መልስ ነው፡፡ ውጤቶቻችንን ማሻሻል እንደምንፈልግ እናስባለን፡፡ ችግሮቻችን ግን ውጤቶቻችን አይደሉም፡፡ መቀየር ያለብን ሂደቱን እና ስርዓቱን ነው፡፡ ምክንያቱም ችግሩን የሚፈጥሩት እነዚህ ነገሮች ናቸው፡፡ በውጤት ደረጃ ችግሮችን ብትቀርፍ መቅረፍ የምትችለው በጊዜያዊነት ብቻ ነው፡፡ ቀጣይነት ያለው ጥሩ ለውጥ ለማምጣት ከፈለግክ ችግሮቹን በሂደት ደረጃ መፍታት አለብህ፡፡ ግብዓቶችን አስተካክል፤ ውጤቶች ራሳቸውን ያስተካክላሉ፡፡
@Human_Intelligence