የስብዕና ልህቀት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ የሚያደርጉ 10 መንገዶች
#Share (ላገባም ላላገባም የሚሰራ ነው።)
__
የፍቅር ተፈጥሮአዊ አካሄድ አልጋ በአልጋ እ
ንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የፍቅር ግንኙነቱ ሲጀመር የነበረው ፍቅር በሂደት እየቀነሰ የነበረው እንዳልነበረ ሊሆን ሁሉ ይችላል፡፡ በመሰረቱ ካልታረመ፣ ካልተኮተኮተ፣ በጥቅሉ አስፈላጊው እንክብካቤ ካልተደረገለት ዝም ብሎ ማበቡን እና መልካም ፍሬ ማፍራቱን የሚቀጥል ምንም ነገር የለም፡፡ ያልተሰራበት ግንኙነት እጣ ፈንታው ደስታ አልባ መሆን ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባሉ፣ ለብዙዎች ምሳሌ ሆነው የሚቀርቡ የፍቅር ግንኙነቶች እንኳን ፍፃሜያቸው የማታ ማታ መራራቅ አልፎ ተርፎም መለያየት ሊሆን ይችላል፡፡ ትልቁ የፍቅር ሕይወት ፈተና ሲጀመር የነበረው ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ ማድረግ ነው፡፡

ምንም እንኳን ፍቅርን ለመመስረት ሁለት ሰዎች አስፈላጊ ቢሆኑም እንዲፀና እና ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ለማድረግ ግን አንድ ሰውም በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ኃላፊነቱን ግን አስቀድሞ መውሰድ ይጠይቃል፡፡ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ነው የሚያድረው፡፡ ክፍቱን የተተወ ቤት ውስጥ ብዙ ነገር ገብቶ ይወጣል፤ ብዙ ነገር እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ያለመጠባበቅ የቻልነውን ያህል ለማድረግ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ውጤቱ ላይ ትኩረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ዋናው ነገር ከእሷ ወይንም ደግሞ ከእሱ መምጣቱ ሳይሆን ዞሮ ዘሮ የሁለቱ የፍቅር ግንኙነት ጣፋጭ እና ፅኑ መሆኑ ነው፡፡ ፍቅራችሁ የሚፀናበት ይበልጥ የፈካ እና የደመቀ፣ ዘመናትን የተሻገረ መሆን የሚችለው ያለመጠባበቅ ኃላፊነት ወስዳችሁ መስራት ያለባችሁን መስራት ስትችሉ ነው፡፡ ምንም ተባለ ምንም አንድ ሰው ሁልጊዜም ኃላፊነቱን መወጣት መጀመር አለበት፡፡ በራሱ ሊንቀሳቀስ እና ሊለወጥ የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ የትዳር ግንኙነት ሲሆን ደግሞ ለማደስ ጥረት ካልተደረገ ወደ መፍረሱም ሊያቀና ይችላል፡፡

ቀጥሎ የትዳር ህጎች ከሚል መጽሐፍ ውስጥ ያገኘናቸውን 10 ፍቅር እንዳማረበት እንዲዘልቅ ያደርጋሉ የሚባሉ ህጎችን አለፍ አለፍ ብለን እናስቃኛችሁ፡፡ እነዚህ ተግባራት ላገቡ ብቻ ሳይሆን ላላገቡና በፍቅር ግንኙነት ላሉም የሚጠቅሙ ተግባራት ናቸው ፡፡

1✍ስሜትን የሚያነቃቁ ነገሮችን ማድረግ

መቼም አብሮ ሲኖር የሚያጋጭ፣ የሚያቀያይም፣ ቅሬታ የሚፈጥር ወዘተ ብዙ ነገር ይኖራል፡፡ ስሜት ይህንን ተከትሎ ይቀዘቅዛል፡፡ ፍቅር ስሜትም ነው በአንድ ጎኑ፡፡ በመሆኑም ስሜትን የሚያነቃቃ ደስታ የሚፈጥር ነገር ማድረግ የአድናቆት አስተያየት መስጠት ለአብነት ያህል አስፈላጊ ነው፡፡ ስራዬ ብላችሁ ማድነቅን ተለማመዱ፡፡ “ትላንት ማታ ጓደኛዬ ቤት በጣም ተጫዋች ሆነህ ነበር ያመሸኸው፤ ደስ ብሎኛል”፣ “አምሮብሻል” ወዘተ ዓይነት አድናቆት ሊሆን ይችላል፡፡ ከትችታችን ይልቅ አድናቆታችን በጣም መብለጥ ይኖርበታል፡፡

2✍ትችትን መቀነስና አድናቆት መጨመር

በአንፃሩ ትችት ትዳር ሲመሰረት አካባቢ አስፈላጊ ነው ይላሉ ብዙ ሰዎች፡፡ ጊዜ በነጎደ ቁጥር ግን ሰዎች ለትችት አለርጂክ መሆን ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ትችትን መቀነስ አንድ አንድ ነገሮችን አይቶ እንዳላዩ ማለፍም ያስፈልጋል፡፡ መነገር አለበት የምንለው ነገር ካለም ከሁለት እና ሶስት አረፍተ ነገር ባልበለጠ እርዝማኔ መገልፅ ይመከራል፡፡ እርግጥ ነው ለትዳርና ፍቅር መጽናት አስፈላጊ የሆኑ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ከሆኑ፤ ግንኝነቱን በማይጎዳ መልኩ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው፤ ምክኒያቱም አለባብሰው ቢያርሱ በአፈር ይመለሱ እንዳይሆን፡፡ ስለዚህ ትችቱ ለፍቅር ግንኝነቱ ሲባል እንጂ እጸጽን ነቅሶ ለማውጣትና የእራስን ትክክለኝነት ለማጉላት መሆን የለበትም፡፡ ትችት በምንሰጥበት ጊዜ ከጥሩ ጀምረን መሀል ላይ ትችታችንን ገልጸን ከዛም በአድናቆት ወይም በበጎ ነገር መደምደም ይመከራል (ሳንድዊች እስታይል እንደሚባለው)፡፡

3✍አዳማጭ ሁኑ

ማደመጥ ለፍቅረኛችን ወይንም ለትዳር አጋራችን የምንሰጠው ትልቁ ስጦታ ነው፡፡ ትርጉም መስጠታችሁን፣ ተሳሳተ የምትሉትን መረጃ ማስተካከላችሁን ጥላችሁ በሙሉ ልባችሁ ማዳመጥ ጠቃሚ ነው፡፡

4✍ራሳችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ

ለራሳችሁ፣ ጓደኞቻችሁ፣ ቤተሰባችሁ ወዘተ ከትዳራችሁ በተጨማሪ ጊዜ መስጠት ጥሩ ነው፡፡ የግላችሁ ጊዜ ማሳለፊያ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ በራሳችሁ እና በራሳችሁ ጉዳይ ላይ ምንም ትኩረት የማታደርጉ ይልቁንም ሙሉ ትኩረታችሁ የትዳር አጋራችሁ ላይ ከሆነ ተቺዎች ወይንም ደግሞ ጭንቀታሞች ትሆናላችሁ፡፡ እያንዳንዷን እዚህ ግባም የማትባል ጉዳይ እያነሳችሁ ስትጥሉ አሰልቺ እና አፋኝ ዓይነት ግንኙነት እንዲኖራችሁ ታደርጋላችሁ፡፡

5✍ይቅርታ ጠይቁ

ምንም እንኳን ለተፈጠረው ችግር የእናንተ እጅ ድርሻ ትንሽ እንደሆነ ብታስቡም “እኔ ይኼ ችግር እንዲፈጠር ለተጫወትኩት ሚና ይቅርታ ይደረግልኝ” ማለትን ተለማመዱ፡፡

6✍ይቅርታ ካልተጠየኩኝ ሞቼ እገኛለሁ አትበሉ

አንድ አንድ ጊዜ ይቅርታ ሳይጠይቁ ሰዎች መተዋቸውን፣ ለውጥ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሊገልፁ ይችላሉ፡፡ይቅርታ ካልተጠየኩ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ግን አላስፈላጊ ተደራራቢ ችግር ይፈጥራል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ተፈላጊው ለውጥ መምጣቱ ነው፡፡

7✍ዘወትር ፈላጊዎች አትሁኑ

በስሜት የራቀ የሚመስል ሰው ጫና ሲደረግበት ይበልጥ ይርቃል፡፡ መተንፈሻ አየር መስጠት፣ ራስ ላይ ትኩረት ማድረግ በአንፃሩ የራቀንም ያቀርባል፡፡ የት ወጣች የት ገባች ውጤታማ አይደለም፡፡

8✍ሀሳባችሁን አጭር እና ለስላስ በሆነ መንገድ ግለፁ

ደጅ ደጁን የሚል ሰው አንድ አንድ ጊዜ ህመም የሚፍጥረበትን የቃላት ልውውጥ ሽሽት ውስጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሀሳብን አጠር አድርጎ፣ በተለሳለሰ መንገድ መግለፅ ጥሩ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ድምፅንም ጭምር ዝቅ አድርጎ መናገር ተገቢ ነው፡፡ ከጣራ በላይ ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገር ቁጣ ይመስላል፤ ከሆነም በዛ መልኩ መግለፁ አስፈላጊ አይደለም፤ ከመፍትሄነት ይልቅ የባሰ ችግር ፈጣሪነቱ ይጎላል፡፡

9✍ሁሉን መስዋዕት አታድርጉ

ተለዋወጭ ሰው መሆን አስፈላጊ ባይሆንም ሁሉንም ነገር ለእርስ በእርስ ግንኙነቱ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን አይመከርም፡፡ ጫና እየተደረገባችሁ ሁሉንም እምነታችሁን፣ ምርጫችሁን እና መንገዳችሁን ገደል አትክተቱ፡፡

10✍በመጠኑም ቢሆን ሁለታችሁም የግልጊዜ ይኑራችሁ

ሰዎች በባህሪያቸው የሚሳቡት ከእርስ በእርስ ግንኙነቱ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ የሚወዳቸው የራሱ ነገሮች ወዳሉት ሰው ነው፡፡ የመጽሐፍት ክበብ፣ በጎ ፍቃድ፣ ዋና ወዘተ ሊሆን ይችላል ባላችሁ ትርፍ ጊዜያችሁ መሞከሩ ይመከራል፡፡ ለብቻችሁ የሚኖራችሁ ጊዜ በጋራ ለሚኖራችሁ ጥሩ ቆይታ አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡ሁሌ አብሮ መሆን መዛዛግና መሰለቻቸት ሊፈጥር ይችላል ፡፡

በነጋሽ አበበ

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence


“I believe in the sun
even when it is not shining
and I believe in love,
even when there’s no one there.
And I believe in God,
even when he is silent.
I believe through any trial,
there is always a way
But sometimes in this suffering
and hopeless despair
My heart cries for shelter,
to know someone’s there
But a voice rises within me, saying hold on
my child, I’ll give you strength,
I’ll give you hope. Just stay a little while.
I believe in the sun
even when it is not shining
And I believe in love
even when there’s no one there
But I believe in God
even when he is silent
I believe through any trial
there is always a way.
May there someday be sunshine
May there someday be happiness
May there someday be love
May there someday be peace….”
– Unknown Author

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence


How to find inner peace


አደጋን ተጋፈጥ

ከብዙ ሰዎች የበለጠ ውድቀት ይገጥመኛል፡፡ በንግድ ሥራዬ ውድቀት ግጥሞኛል፡፡ በማህበራዊ ግንኙነት ውድቀት ገጥሞኛል፡፡ በሕይወቴ ብዙ ጊዜ ውድቀት ይገጥመኛል፡፡ ይህ ለምን እንደተከሰተ በመገረም አስባለሁ፡፡ በውድቀቴ እማረር ነበር፡፡ አሁን ግን ገብቶኛል፡፡ ውድቀት ከታላቅ ደረጃ ለመድረስ የሚከፈል ዋጋ ነው፡፡ ውድቀት የታላቅ ስኬት መሠረታዊ ግብአት ነው፡፡ አዲስ ነገር በመፍጠር ጠቢብ የሆነው ዴቪድ ኬሊ ይህን ብሏል፡- «ቶሎ ውደቅና ፈጥነህ ተነሥ››.. ከምቾት ቀጠናህ ሳትወጣና በተጠና መልኩ አደጋን ካልተጋፈጥህ ልታሸንፍ አትችልም፡፡

ብዙዎቻችን የምንኖረው የደህንነት ስሜት በሚፈጥርልን በሚታወቅ «ወደብ› ላይ ሆነን ነው። ለሃያ ዓመታት አንድ ዓይነት ምግብ ስንመገብ ኖረናል፣ ለሀያ ዓመታት በአንድ ሥፍራ ተወስነን ኖረናል፤ ለሀያ ዓመታት በአንድ መንገድ ተመላልሰናል፣ ለሀያ ዓመታት አንድ ዓይነት አስተሳሰብ አንጸባርቀናል። በዚህ መልኩ አስደሳች ሕይወት ለመምራት አይቻልም፡፡ እስከዛሬ ስትሰራ የኖርከውን መሥራት ከቀጠልክ እስከዛሬ ስታገኝ የቆየኸውን ማግኘትህን ትቀጥላለህ፡፡ አይንስታይን እብደትን የገለጸው «ተመሳሳይ ነገር እየሰሩ የተለየ ውጤት መጠበቅ» በማለት ነው። እውነተኛ ሐሴትን ልትጎናጸፍ የምትችለው አደጋን ተጋፍጠህ ወደ ታላቁ ባሕር ቀዝፈህ ስትገባ እንጂ ከወደብ ላይ ተወስነህ ስትቆም እይደለም፡፡

ውድቀት ደረጃህን ከፍ የማድረግ ሂደት አካል ነው። በምድሪቱ ላይ የሚገኙ ግዙፍ ስኬታማ ተቋማት ስኬትማ ከመሆናቸው በፊት ብዙ ውድቀትን አስተናግደዋል፡፡ በጣም ስኬታማ ሰዎች ከተራ ሰዎች ይበልጥ ውድቀት
አስተናግደዋል።  ለእኔ፣ ውድቀት ለመሞከር ና ለመድፈር አለመቻል ነው። እውነተኛ አደጋ ያለው አደጋ አልባ ሕይወት በመምራት ነው፡፡ ማርክ ትዌይን ትዝብቱን እንዲህ ሲል አስፍሯል፡- ‹ከሀያ ዓመታት በኋላ ከሠራሃቸው ይልቅ ባልሰራሃቸው ነገሮች ትበሳጫለህ›› ስለዚህ፣ ከዛሬ ጀምር፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ


share : @Human_Intelligence


🔑Conditioned Mind

"It is not because things are difficult that we do not dare; it is because we do not dare that things are difficult." - Seneca
---
🔆በሕንድ መንደሮች ውስጥ ሲዘዋወር የቆየ አንድ እንግዳ ሰው ነዋሪዎቹ ዝሆኖቻቸውን የሚጠብቁበት መንገድ ግራ አጋብቶታል... እጅግ ግዙፍ የሚባሉ ዝሆኖች በቀላሉ ሊበጠሱ በሚችሉ ገመዶች ታስረው በጸጥታ የመቆማቸው ምስጢር እውነትም እንቆቅልሽ ነበር... 'እንዴት ሊሆን ይችላል?'...

⚜️ግራ መጋባቱ እየቀጠለ ሲሄድ ወደ አንድ የዝሆኖች አሰልጣኝ ዘንድ ቀርቦ 'ይህን እንዴት ማድረግ ቻላችሁ?... ዝሆኖች በምድር ላይ በጉልበታቸው ተስተካካይ የሌላቸው ፍጥረታት መሆናቸው ይታወቃል... በዚህ ሰላላ ገመድ ታስረው እንዲቆዩ ያደረጋቸው ምስጢር ምንድነው?...' ሲል ጠየቀ... 'ደህና...' አለ ዝሆኖችን የሚገራው ሰው... በእንግዳው ሰው ጥያቄ አንዳችም መገረም ሳያሳይ... 'በዚህ ገመድ መታሰር የሚጀምሩት ከደረጁ.. ጉልበት ካበጁ በኋላ አይደለም... ገና ግልገል ሳሉ ነው... በዚያ የማለዳ ዕድሜ አሁን የምታየው ገመድ እነርሱን አስሮ ለመቆየት በቂ ነበር... እየቆዩ ሲሄዱ ገመዱን የሚበጥስ አቅም ቢፈጥሩም በልጅነታቸው የታተመባቸው እምነት ግን ዛሬም ገመዱን መበጠስ እንደማይችሉ ይነግራቸዋል'...

🔆ሰውየው በጥበባቸው ተገረመ... ግዙፉን ዝሆን ለማሰር ግዙፍ ሰንሰለት አላስፈለጋቸውም... አስተሳሰባቸውን የሚያስር የማለዳ ልማድ በቂ ነበር... ነገሩ ሰንሰለት ካሰረው ልማድ ያሰረው ነው... 'ልማድ ከብረት ይጠነክራልና' ሼክስፒር እንዳለው...

🔆የኑረት ውበት በየደረሱበት መጠየቅ... የሰውነት ከፍታም በየመዳረሻው መርቀቅ ቢሆንም ከተነገረው ዘሎ 'ለምንና እንዴት' ለማይል አዕምሮ የነበረን ማስጠበቅ እንጂ 'አዲስ ነገር' ማፍለቅ አይሆንለትም... የኑረት ስኬትም ሆነ ውድቀት በእምነትህ ልክ ይገነባል... ቡድሃ "All that we are is the result of what we have thought. The mind is everything. What we think we become. " የሚለውን ቃል በትምህርቱ መጀመሪያ ላይ ያስቀመጠው ለዚሁ ነበር...

💫የምታምናቸውን ነገሮች ለምን እንዳመንካቸው ጠይቀህ ታውቃለህ?... የተቀበልካቸውን እሳቤዎች ልክነት በ'እንዴት' ዓይን መዝነህ ታውቃለህ?... የነገሩህን መጽሐፍትና ያስተማሩህን አንደበቶች መርምረህ ታውቃለህ?... እርግጠኛ ስለሆንክባቸው ጉዳዮች ቢያንስ ለራስህ በታማኝነት የምታቀርበው መልስ አለህ?... ወይስ እንደ ግዙፉ ዝሆን በሰላላ የአስተሳሰብ ወደሮ ታብተሃል?... መጠየቅስ አድክሞህ ይሆን?... Wynn Bullock የተባለ ሰው... "If you stop searching, you stop living, because then you're dwelling in the past. If you're not reaching forward to any growth or future, you might as well be dead." ብሎ ነበር... ሶቅራጥስ በበኩሉ "The unexamined life is not worth living" ብሏል...

✨ከማለዳ ውልደት እስከ ውድቅት ህልፈት የምትሳበው ኑረት ሁለንተናዋ በጠነከረ ልማድ የተቀየደ ነው... ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ የትወናዋን አካሄድ የሚወስንላት መራሔ ተውኔት ልማድ ወይም እምነት ይባላል... የምታምነውን ነው የምትሆነው... ግና.. የማለዳ እምነትህ ረፋድ ላይ... የረፋድ እሳቤህ ቀትር ላይ... የቀትር ግንዛቤህ በተሲዓት... የተሲዓት እውነትህ በምሽት ካልተመረመረ ከልማድ እስረኛነትህ ሳትፈታ ውድቅትህ ይመጣል... "The world is a prison and we are the prisoners.Dig a hole in the prison wall and let yourself out." ይልሃል ሩሚ...

🔑'ተለምዷል' የሚልህ ሰው ሲበዛ ጠርጥር... ቅኝት ነው... 'ምንም ማድረግ አይቻልም' ካለህ ተቃኝቷል በቃ... 'ያለ ነው'... 'ባሕል ነው'... 'አሰራር ነው'... 'እከሌ የሚባል ሰው ወይም መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል'... ወዘተረፈዎች የቅኝት መገለጫዎች ናቸው... እዚህ መንደር ውስጥ 'ለምን' ባይ የተገኘለት የእብደት ታፔላ ይለጠፍለታል...

🔆ዕድሜ ልኩን ጥርሱን ሳያጸዳ የኖረ ሰው ለተወሰኑ ቀናት ብሩሽ ተጠቅሞ በመተዉ የአፉን ሽታ ቢያስተውል ሊል የሚችለው አንድ ነገር 'የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል' ነው... ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት ሽታውን ተላምዶት ስለቆየ 'አፍህ ይሸታል' ቢሉት አይቀበልም ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳት ይጀምራል... ተለማምዶ እስኪዘነጋው ድረስ... ጠረን እንድትለይ የሚረዱህን 'ብሩሾች' ስንቴ 'ያሸታሉ' ብለህ ጣልክ?... ስንቴስ ወደ ቀደመ ሽታህ ተመለስክ?...

ኒቼ በተወልን ድንቅ መስመር የማያልቀውን እንጨርስ... "If you have a 'why' to live by, you can live with any 'how'."

የ'ለምን' እና 'እንዴት' ድፍረት ይስጠን!!
                 ሰላም...❤️

                             ✍ ደምስ ሰይፉ

@Human_Intelligence


የአንተ ክብረ-ወሰን ምንድን ነው?

ፈላስፋው አርተር ሾፐን-አወር ይህን ተናግሯል፡፡ ‹‹ብዙ ሰዎች የራሳቸውን የራእይ ገደብ የዓለም ወሰን አድርገው ይወስዳሉ፡፡ ጥቂቶች ግን እንዲያ አያስቡም፤ ከእነርሱ ጎራ ተሰለፍ፡፡» በጣም ጥልቅ ነጥብ ነው፡፡አሁን የምትኖረውን ሕይወት ባለህ አቅም ልክ እየኖርክ ነው?? ምናልባት ነገሮችን የምትመለከተው በፍርሐት፣ በገደብና በሀሰተኛ ግምት እይታ ይሆናል። የመስኮትህን መስታወት ወልውለህ ወደ ውጭ ስትመለከት አዲስ አማራጮችና እድሎች ይከሰታሉ፡፡

ዓለምን የምንመለከተው እንደሆነው ሳይሆን እኛ እንደሆንነው መሆኑን አስታውስ፡፡ ከአስርት ዓመታት በፊት ደስታ የራቀው ጠበቃ ሆኜ ሕይወቴን የምመራበት የተሻለ መንገድ እየፈለግሁ ሳለ ይህ ሐሳብ ሕይወቴን ለውጦታል፡፡
ከ1954 ዓ.ም. በፊት የአንድ ማይል ርቀትን ከአራት ደቂቃ በታች በሩጫ ሊሽፍን የሚል ሯጭ እንደማይኖር ይታመን ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ሮጀር ባኒስተር ይህን ክብረ ወሰን ከሰበረ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የእርሱን ክብረወሰን በርካታ አትሌቶች ለማሻሻል በቁ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ምን እንደሚቻል ለዓለም እርሱ አሳይቷልና፡፡ ከእርሱ በኋላ የሮጡ አትሌቶች አዲስ ማነፃፀሪያ ነጥብ አግኝተዋል። ያን እምነት ታጥቀውም ሰዎች የማይቻለውን ለማድረግ በቁ፡፡

የአንተ ክብረ-ወሰን ምንድን ነው? ለመሆን እንደማትችል ለማድረግ እንደማትችል፣ ልታገኝ እንደማትችል በማሰብ ስለራስህ የያዝከዉ የውሽት ግምት ምንድን ነው? አስተሳሰብህ እውነታህን ይፈጥራል፡፡ እምነቶችህ ድርጊቶችህን ስለሚመሩ ከአስተሳሰብህ ጋር በሚቃረን መልኩ ፈጽሞ ምንም ነገር አታደርግም፡፡

የሕይወትህ ደረጃ የአስተሳሰብህ ደረጃ ነፀብራቅ ነው። በሕይወትህ አንዳች ነገር ሊከሰት እንደማይችል ካሰብክ ያን ግብ እውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን የምትወስድበት አንዳችም መንገድ አይኖርም፡፡ የ«አይቻልም» አስተሳሰብህ ራሱን እውን ያደርጋል። በራስህ ላይ የምትፈጥረው ገደብ መድረስ ከሚገባህ የታላቅነት ደረጃ እንዳትደርስ ጠልፎ የሚጥልህ ሰንስለት ነው፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ

Share : @Human_Intelligence




ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም!!

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በቅን መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት!

የስብዕና ልህቀት


Репост из: Tesfaab Teshome
የፍልሚያችን ውጤት
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ጭቆናን ለማክሰም
ያለአንዳች መታከት፥ በብርቱ ብንተጋም
አርነት ለመውጣት
በፅኑ ተጋድለን ፥ጡንቻችን ቢዝልም

ከፍልሚያችን ማግስት፦
የተቀናጀነው፥ የመራብ ነፃነት
ማሳካት የቻልነው ፥የመታረዝን መብት
ሃብታችን የሆነው ፥የህመም ክምችት
የተማርነው ጥበብ፥ ሳይደክሙ መፎከት።

በመፋለም ብዛት፥ ቀድሞ የታነፀው፥ ስለፈራረሰ
ከልብ ምንጫችን ላይ፥ የሚፈልቀው ኹሉ ፥ስለደፈረሰ
ርቱዕ የነበረ ፥አንደበታችንም ፥ባ'ፍረት ተለጎመ
ከልባችን መዝገብ ፥ድል ማድረግ ተፍቆ፥ መሸነፍ ታተመ


@Tfanos


ጊዜህን በርካሽ ዋጋ አትሽጥ!!

"ሴኔካ አካላዊ ንብረቶቻችንን መጠበቅ ላይ ጥሩ የሆንነውን ያህል፣ አእምሯዊ ድንበሮቻችን ማስመር ላይ ግን ግድ የለሽ መሆናችንን . ያስታውሰናል። ማንም እንዳሻው ድንበራችንን አልፎ ሲገባ አንቃወመውም: ንብረት ተመልሶ ሊገኝ ይችላል፤ እንዲያውም ገና ብዙ የምድር ሃብቶች በሰው አልተነኩም። ጊዜ ግን? ጊዜ ፈጽሞ ሊተካ የማይችል ሀብታችን ነው፤ ተጨማሪ መግዛት አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው በተቻለ መጠን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረግ ብቻ ነው፡፡"

"በሕይወታችን ውስጥ ሌሎች ጣልቃ እንዲገቡ በቀላሉ እንፈቅዳለን፤ የከፋው ነገር ደግሞ በአብዛኛው ጊዜያችንን ሊያጠፉት ለሚችሉት ሰዎች መንገድ የምናመቻች መሆናችን ነው። ማንም ሰው ለአላፊ አግዳሚው ገንዘቡን አይሰጥም፤ ግን እያንዳንዳችን ለምን ያህል ሰዎች ሕይወታችንን ሰጥተናል!ለንብረትና ለገንዘብ እጃችን አይፈታም፣ ሁላችንም እጅግ ስስታሞች መሆን ለሚገባን ለሚባክን ጊዜ ግን የምናስበው እጅግ ትንሽ ነው።”
- ሴኔካ

"የሕይወታችንን ቀናት ልክ እንደ ገንዘባችን አንመለከተም? በትክክል ለምን ያህል ቀናት በሕይወት እንደምንቆይ ስለማናውቅ፣ አንድ ቀን የምንሞት የመሆኑን ሀቅ በቻልነው ሁሉ ላለማሰብ ስለምንሞክር፣ ጊዜያችንን በነጻነት ለማባከን ፍቃድ የተሰጠን ይመስለናል። እዚህ ላይ እኔ በምትኩ የማገኘው ምንድነው?” ብለን እምብዛም ሳንጠይቅ በዚያችው ባለችን ጊዜ ላይ ሰዎችና ክስተቶች ጊዜያችንን እንዲሰርቁን እንፈቅድላቸዋለን፡፡"


"እንዴት እንደምትጠቀምበት ካወቅክ፣
ሕይወት ረጅም ነው ነገሩ፣ ለመኖር ያለን ጊዜ አጭር ስለመሆኑ ሳይሆን ብዙውን ያባከንነው ስለመሆናችን ነው። በደንብ ከተጠቀምንበት ሕይወት በበቂ ሁኔታ ረጅም ነው ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት በበቂ ሁኔታ ተለክቶ የተሰጠ ነው። በድሎትና ችላ በማለት ውስጥ ካባከንነው፣ መልካም ፍጻሜ ለማግኘት ካልሰራን፣ በመጨረሻ ማለፉን እንኳን ከመረዳታትን በፊት አልፎ እናገኘዋለን። ስለዚህ የተቀበልነው ሕይወት አጭር አይደለም፤ አጭር ያደረግነው እኛ
ነን።”
-ሴኔካ

ስለዚህ ዛሬ ራስህን ስትጣደፍ ወይም “በቂ ጊዜ የለኝም፡፡” የሚሉትን ቃላት ስትናገር ብትሰማው፣ ቆም በልና ጥቂት ሰከንዶች ውሰድ፡፡ ይህ እውነት ነው? ወይስ ብዙ አላስፈላጊ ነገሮች በመስራት ተጠምደህ ነው? በእርግጥ ውጤታማ ነህ፣ ወይስ በሕይወትህ ውስጥ ብዙ የባከነ ነገር እንዳለ ትገምታለህ? በህይወታችን አብዛኛውን ጊዜ  የምናባክነው በማይጠቅሙን ሀሳቦች እና በማይረቡ ነገሮች ላይ ነው። እያንዳንዱን ደቂቃ የምንጠቀም ቢሆን ምን ያህል ጊዜ ሊተርፈን እንደሚችል አስቡ!!


"እንዲህም እላለሁ እንዲት ቀንም ቢሆን አልሰጥም - ማንም ቢሆን አንድ ቀኔን ሊመልስልኝ አይችልምና!!

እንዲህም እላለሁ እያንዳንዷ ሰከንድ የእኔ ናት በባለቤትነት እና በስልጣን አስተዳድራታለሁ:: አልፋኝ የምትሄድ ሽርፍራፉ ሰከንድ አትኖርም!!"

የእለት ፍልስፍና


የስብዕና ልህቀት
Share : @Human_Intelligence


Репост из: Tesfaab Teshome
የመሪ ያለህ !
(ተስፋኣብ ተሾመ)


ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ችግር እያለ ሕዝቡ ዝምታን መምረጡ ስንፍና አልያም ግድ የለሽነት የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። ይህ ስህተት ነው።

ሕዝብ እንዴት መተባበር እንዳለበት አያውቅም።

ፖለቲካ የሙሉ ጊዜ ስራቸው የሆኑ አካላት ካልመሩት በቀር ህዝብ መንግስታትን ለመጋፈጥ ቢሞክር ችግር ይከሰታል። ባንክና ታንክ ካለው አካል ጋር ሕዝብ ቢጋፈጥ የእሳት እራት ከመሆን አይተርፍም።

ይልቅ ፖለቲካ የሙሉ ጊዜ ስራቸው የሆነላቸው ሰዎች ቸልታ አሳሳቢ ነው። የፓርቲዎች ስንፍና የሚወቀስ ነው።

ሕዝብ መሪ ይፈልጋል።

ሚሊዮን ሰዎች እንዴት ይግባባሉ? ሚሊዮን መረጃዎች እንዴት ይተነተናሉ እንዴትስ ይተገበራሉ?፥ ህዝብ መረጃን እንዴት ይቀባበላል?፥ ግብ ላይ ለመድረስ የሚረዳው ስትራቴጂ ምንድነው?

ለጥያቄዎቹ መልስን ማበጀት የሚችለው መሪ ነው።

የፖለቲካ መሪ የጠፋው ለምንድነው?

የደርግ ዘመን እሳት ሙህራንን በላ፥ መምራት የሚችሉትን አኮላሸ። የኢህአዴግ ዘመን በተደራጀ መንገድ ድንቁ*ርናን አመረተ። ፖለቲካ እውቀት መሆኑ ቀርቶ ተራ ነገር ሆነ። ጥቂት አዋቂዎች የቀደሙትን የበላው እሳት እንዳይበላቸው "ፖለቲካን በሩቁ" አሉ።

መሪ የለንም። መተማመን የለም። የአንዱ መሪ ለሌላው ጠላ*ት ነው። የጋራ መሪም የጋራ አላማም የለም።

ለምንድነው መሪ አልባ የሆንነው? ሕዝባችን መሪ ለመውለድ መክነ ወይስ የተወለዱ መሪዎች ተጨናገፉ?


@Tfanos


ፍቅርና ጋብቻ

“ፍቅር ምንድን ነው?” ሲል ተማሪው ለመምህሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡ “ለጥያቄህ መልስ ለመስጠት በቅድሚያ በአንድ የስንዴ ማሳ ሂድና ትልቁን ስንዴ መርጠህ ይዘህ ናና መልሱን እነግርሃለሁ፡፡

ነገር ግን ልብ አድርግ የአሰራር ሕጉ የሚፈቅደው በስንዴው ማሳ አንድ ጊዜ ብቻ በማለፍ የስንዴውን ዛላ ይዘህ ትመለሰላህ እንጅ በማሳው ውስጥ መመላለስ አይቻልም አለው” መምህሩ፡፡

ተማሪው እንደተባለው ወደ ስንዴው ማሳ ገባና የመጀመሪያውን ሽና (መደዳ) ይዞ ሲጓዝ አንድ ትልቅ የስንዴ ዛላ አገኘ ነገር ግን ይሄን አድንቆ ሌላ ከዚህ የላቀ ትልቅ ይኖራል በማለት ፍለጋውን ቀጠለ እንዳሰበውም ከበፊቱ የተሻለ ትልቅ አገኘ፡፡

ምን አልባትም እስካሁን ካየሁት የበለጠው እየጠበቀኝ ይሆናል በማለት ፍለጋውን ቀጠለው፡፡

የስንዴውን ማሳ ከግማሽ በላይ ካደረሰ በኋላ ከዚህ በፊት ካገኛቸው የስንዴ ዛላዎች የበለጠ እንደማይኖር ተረዳና ቀደም ብሎ አግኝቶት በነበረውና ባመለጠው ትልቅ የስንዴ ዛላ እየተቆጨ ባዶ እጁን ወደ መምህሩ በተመለሰ ጊዜ “ፍቅር ማለት እሱ ነው፡፡

የተሻ ፍለጋው አልገታ ብሎህ ፍለጋውን ቀጠልክ ነገር ግን የተሻለውን እንዳጣህ ዘግይተህ ተገነዘብክ” አለው መምህሩ፡፡

“ታዲያ ጋብቻ ማለትስ ምንድን ነው?” ሲል ሁለተኛ ጥያቄውን አቀረበ

መምህሩም “አሁንም ጥያቄህን ለመመለስ ባንድ የማሽላ ማሳ ሂድና ትልቅ ነው ያልከውን ማሽላ ይዘህ ተመለስ፡፡

ታዲያ አሁንም እንደበፊቱ የአሰራር ሕጉ የሚፈቅድልህ አንድ ጊዜ ማለፍ እንጅ ተመልሶ መፈለግና ማንሳት አይቻልም” አለው፡፡

ተማሪው ወደ ማሽላው ማሳ በደረሰ ጊዜ ከበፊት ስህተቱ ተምሮ ስህተቱን ላለመድገም ከማሳው ግማሽ እንደደረሰ አንድ በቂ ነው ብሎ ያሰበውን መካከለኛ ማሽላ ይዞ ወደ መምህሩ ተመለሰ፡፡

መምህሩም “አሁን ጥሩውን ፈልገህና የተሻለ ነው ብለህ ያሰብከውንና ምርጡንም እንዳገኘህ አምነህ በእምነት ይዘህ መጠሀል ይህ ማለት ጋብቻ ነው” በማለት ጥያቄዎቹን መለሱለት፡፡


የስብዕና ልህቀት
Share; @Human_Intelligence


አእምሮአችን በሰው ልጅ የአፈጣጠር ታሪክ ውስጥ ልዩ የሆነ የእግዚአብሔር ስራ ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ብንፈትሽ የፀሀይን መጥለቅና መውጣት፣ የውቅያኖሶችን ስጥመት እና መሰል አስደናቂ የተፈጥሮ ምስጢራት ብንመረምር፤ እንደሰው አእምሮ ረቂቅ የሆነ ነገር ግን አናገኝም፡፡ አእምሮአችን በህይወታችን ጉዞ ሁሉ የሚከተለን ጠባቂያችን ግን ደግሞ ልንከተለው ያልፈለግነው ዋነኛ የእኛነታችን አሻራ ነው፡፡

አእምሮአችን ራሱን የቻለ ሰፊ ውቅያኖስ ቢሆንም እኛ ግን ከዚያ ሁሉ ማዕበል የምንጠቀመው የአንድ ማንኪያ ጠብታ ያህሉን ብቻ ነው። ምርጫችንም የምናደርገው የውቅያኖስ ያህል ስፋት ካለው አቅማችን ይልቅ በዚህችው ጠብታ ላይ ነው፡፡ በዚህ ኢምንት ጉዳይ ላይ መመርኮዝ ደግሞ አንድ መሠረታዊ እውነታ እንዲያመልጠን ያደርጋል። አብዛኛው ጊዜያችንና ገንዘባችን ሰውነታችን ለማስዋብ የሚጠፋ ነው፡፡ እዚህ ላይ የምናጠፋውን እሩብ ያህል ጊዜ አእምሮአችንን ለመሞረድ ብናጠፋ ግን ጥቅማችን ዘርፈ - ብዙ ይሆናል፡፡ በዚህ ዘመን በህይወት ያለ ሰው ሶቅራጥስን፣ ኮንፊሺየስን፣ ሼክስፒርን ወይም ቤትሆቨንን በአካል የሚያቃቸው አይገኝም፡፡ ነገር ግን የአእምሮአቸው ውጤት የሆነው ስራቸው በክፍለዘመናችን ሁሉ ገናና ሆኖ እየኖረ ነው፡፡

ቪጄ ኤስዋሪን

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence






በጨዋታ መሃል ፦

አለቺኝ ?

እንዴት ልበ ሙሉነት የተጠናወተኝ ሰው እንደሆንኩ ከራሴ ጋ እየተሻማው አወራሁ... አብራራሁ... ዘበዘብኩ

በእርጋታ ከሰማቺኝ በኃላ
አለቺኝ

አልኳት ደስ ባላለው ፊት እያየኃት



አሁንም ዝም አልኳት ።  ዝምታዬ ውስጥ ግን መደነቅ እና ድብርት  ነበረበት


"የተከፈለ ዋጋ " ስህተት
ያለፈውን መርሳት የሚገባን ለምንድ ነው?

ልናየው የጀመርነው ፊልም መጥፎ ነበርና ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሚስቴን ‹እንሂድ› አልኳት። እሷ ግን ‹‹በጭራሽ፣ 30 ዶላራችንንማ ዝም ብለን አንጥልም›› አለቺኝ፡፡ ‹‹ይህ ለመቆየት ምክንያት አይሆንም›› ብዬ ተቃወምኳት፡፡ ገንዘቡ አንድ ጊዜ ወጥቷል - ይህ የተከፈለ ዋጋ ስህተት የሚባል የአስተሳሰብ ስህተት ነው፡፡ ሎሚ የገመጠች ይመስል ፊቷን አኮሳተረችብኝ፡፡ ‹‹ከመቆየታችንና ካለመቆየታችን ጋር ሳይያያዝ 30 ዶላሩን አንድ ጊዜ ወጪ አድርገናል ፤ ስለዚህ ይህ ነገር ለውሳኔያችን መሰረት መሆን አይችልም›› ብዬ ሁኔታውን ለማብራራት ሞክርኩ፡፡ ጥረቴ አልተሳካም፣ ተመልሼ ተቀመጥኩ፡፡

በቀጣዩ ቀን በአንድ ስብሰባ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ የማስታወቂያ ዘመቻችን ላለፉት አራት ወራት እየተካሄደ ቢሆንም አንዱንም ግቡን እንኳን አላሳካም ነበር፡፡ እኔ ማስታወቂያው እንዲቀየር ፍላጎት ስለነበረኝ ይሄው እንዲፈፀም ሃሳብ አነሳሁ፡፡ የማስታወቂያ ክፍል ሃላፊያችን ግን አጥብቃ ተቃወመች፡፡ ‹‹ብዙ ገንዘብ አውጥተንበታል፤ አሁኑኑ ከተውነው የከፈልነው ገንዘብ መና ቀረ ማለት ነው›› የሚል ነበር መከራከሪያዋ - ሌላ የተከፈለ ዋጋ ስህተት ሰለባ፡፡

አንድ የሴት ጓደኛ ያለችው ወጣት በተረበሽ ግንኙነታቸው ውስጥ ለመቀጠል ብዙ ታገለ፡፡ የሴት ጓደኛው እየደጋገመች ከእሱ ውጪ ትማግጥበታለች፡፡ ይሄን ችግሩን ለእኔ የገለፀልኝ እንደዚህ ብሎ ነበር። ‹‹በዚህ ግንኙነት ውስጥ ብዙ ኃይል አባክኛለሁ፤ ብዙ ዋጋም ከፍያለሁ፡፡ አሁን ላይ ግንኙነቱን ማቋረጥ አልችልም፤ ልክ አይመስለኝም፡፡» - የተከፈለ ዋጋ ስህተት አይነተኛ ሰለባ፡፡

ይህ የተከፈለ ዋጋ ስህተት የበለጠ አደገኛ የሚሆነው ደግሞ ብዙ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበትና ፍቅር የከፈልንበት ነገር ላይ ሲሆን ነው፡፡ - ይዘነው ልንቀጥለው እየታገልንለት ያለው ጉዳይ የሞተ ነገር ቢሆን እንኳን እንዳንጨክንበት ያደርገናል፡፡ ነገሩ ምንም እንደማይጠቅመን እያወቅን ከነገሩ ጋር ጊዜያችንን እና ገንዘባችንን እናባክናለን።

በአንድ- ነገር ላይ ከፍተኛ ጥረት ካደረግክና ብዙ ጊዜያት ከከሰከስክበት ለውጤቱ የምትሰጠው ዋጋ የተጋነነ ይሆናል። የምትሰራቸውን ስራዎች ሁሉ በምክንያት  እንምትሰራቸው አስተውል። በአንድ ነገር ላይ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት ባባከንክ ቁጥር ወደ ኋላ እየተመለስክ ውጤቱን ተመልከት - ውጤቱን ብቻ። አምስት አመታትን ለፍተህ የተማርከው ትምህርት (ዲግር) ተግባራዊ እውቀት ካልሰጠህና ጥሩ የስራ እድል ካልፈጠረልህ  ተወው!! አምስት አመታትን ወስደህ ያዘጋጀው መጽሐፍ ጠያቂ ከሌለው መጽሐፉ ላይረባ እንደሚችል አስብ። አምስት አመት ሙሉ ለፍቅር የለመንካት ሴት ከዚያ በኋላ በጥቂት ወራት ውስጥ ተዋውቀሃት ካገባሃት ሴት ትበልጣለች? አስተውል አንድን ነገር ብዙ ደክመህበታል ማለት ነገሩ ጥሩ ነው ማለት አይደለም!!

ነጋዴዎቸና ኢንቨስተሮች በዚህ ስህተት ተጠቂዎች ይሆናሉ።  የከፈልነው ዋጋ እና ኢንቨስትመንት ከፍ ያለ በሆነ ቁጥር ከጉዳዩ ጋር ለመቀጠል ያለን ፍላጎትም ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡ብዙውን ጊዜ የንግድ ውሳኔዎቻቸውን በከፈሉት ዋጋ ላይ የሚንጠለጠል ያደርጉታል፡፡ ‹‹በዚህ ቢዝነስ ውስጥ ብዙ ገንዘብ ከስክሻለሁ ስለዚህ ስኬታማ ሊሆን ባይችልም አሁን ልተወው አልችልም›› ይላሉ፡፡  ይህ ኢ ምክንያታዊነት ባህሪ ወጥ በመሆን ፍላጎት የሚመራ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ወጥነት የታማኝነት (credibility) ማሳያም ይመስለናል። ሃሳብ መቀያየር እንደነውር ነው የሚታየው፡፡ በግማሽ የሄደ ፕሮጀክትን መተው መሸነፍን እንደማመን ይቆጠራል። ይህ ስህተት ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል፣ አንዳንድ ጊዜም የተሳሳተ ውሳኔ ላይ እንድንደርስ የሚያደርግ ነው። አሜሪካ የቬትናም ጦርነት ውስጥ መቀጠልን የመረጠችው በዚህ የተነሳ ነው። ‹‹ለዚህ ጦርነት ብዙ ዋጋ ከፍለናል፤ አሁን ማቆም ስህተት ነው የሚሆነው›› በሚል አረዳድ በመታጠር፡፡


በእርግጥ አንድ ነገር እስኪጠናቀቅ መስራትና መጨረስ ውስጥ ብዙ ጥሩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለተሳሳቱ ምክንያቶች አንድን ነገር ይዘህ እየቀጠልክ አለመሆንህን ግን እርግጠኛ ሁን፡፡ ለምሳሌ ተመልሰው ለማይገኙ (non recoverable) ወጪዎች ሲባል አንድን ነገር ይዞ መቀጠል አግባብ አይደለም፡፡ ምክንያታዊ ውሳኔ ሰጪነት እስከእለቱ ድረስ የወጡ ወጪዎችን እንድንረሳ ያስገድደናል፡፡ ምን ያህልም ግን ያፈስስክበት ነገር ቢሆን አሁን ላይ ውሳኔ ለመስጠት ከግምት ውስጥ ልታስገባቸው የሚገቡህ ነገሮች የወደፊት ወጪዎችና ጥቅሞችን ብቻ ናቸው።

✍️ሮልፍ ዶብሊ

የስብዕና ልህቀት
Share&Join
@Human_Intelligence


ውብ ታሪኮች-1
ድንቅ አጫጭር ትረካዎች በአንድ ላይ

ተራኪ-ግሩም ተበጀ

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence


ድፍረት ማለት ያለ ፍርሀት መኖርና እየደነፉ ማውራት ማለት ሳይሆን ፣ከሚገባው በላይ ብንፈራና ብንደነግጥም እንኳን ያሰብነውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለት ነው ።

በአስቸጋሪ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ተረጋግቶ መውጫ ቀዳዳ በመሻት  መውጣት የድፍረት አንድ አካል ነው

ድፍረት ማለት የፍርሀት አለመኖር ሳይሆን ፍርሀት ላይ የምንቀዳጀው ድል እንደሆነ ተማርኩ፤ ጀግና የሚባለው ፍርሀት የማይሰማው ሳይሆን ፍርሀትን መማረክ የቻለው ነው!

----ኔልሰን ማንዴላ


የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው። የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው። እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምንይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው። የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው።

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

Показано 20 последних публикаций.