የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ
ራስን ከሌላው ሰው ጋር ማነጻጸር ቀንደኛው የደስታና የሰላም ሌባ ነው፡፡ የዚህ ራስን ከሌላው ሰው ጋር የማነጻጸር አራጋቢ ደግሞ ማሕበራ ሚዲያ ነው፡፡
ማሕበራዊ ሚዲያ ያደረገብን ነገር ቢኖር ይህ ነው፡፡ ሰዎች ያላቸውን ጉድለት በመሸሸግ እኛ እንድናየው የሚፈልጉትን የተቀባባ ሁኔታ ብቻ ነጥለው ያቀርቡልናል፡፡ እነሱ በሚዲያ ነጥለው ያቀረቡትን “የተሻለ” ነገራቸውን ካየን በኋላ መለስ ብለን ስለራሳችን ከምናውቀው “ዝቅተኛው” ማንነት ጋር ማነጻጸር እንጀምራለን፡፡ በውጤቱም የእኛ ሕይወት ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረ ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ይህ አጉልና የተዛባ እሳቤ፣ የምንፈልገው ነገር ምን እንሆነ እከማናውቀው ድረስ እንድንቅበጠበጥና ደስታ-ቢስ እንድንሆን ያደርናል፡፡
ፍቅረኛ ብናገኝ አንረጋጋ፣ ገንዘብ ብናገኝ አንረካ፣ ብንለብስ ያማረብን አይመስለን . . . የሌለውንና የማይደረስበትን እንደፈለግን እንኖራለን፡፡
ምናልባት ስሜት ቀስቃሽ (Sensational) ከሆኑት ማሕበራዊ ገጾች አጉል ተጽእኖ ረገብ ብንልና የራሳችንን የሕይወት ግብ፣ አቅጣጫና ከፍታ ከራሳችን ራእይ አንጻር ብናወጣው ቅጥ ያጣው የውስጥ ስሜታችን ይረጋጋ ይሆናል፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence