በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ባህሪህን ይወስናል
ባህሪይህን ተመልከተውና በራስህ ላይ ያለህን አመለካከት በግለጽ ይጠቁምሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ስትሆን የምትገልጠው ባህሪይ በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ ብቻህን ስትሆን፣ ስለራስህ ስታስብ፣ ራስህን በመስታወት ስትመለከተው ስለራስህ የምታስበውን ትክክለኛውን ሃሳብ አግኘውና ከሰዎች ጋር ስትሆን የምታንጸባርቀውን የባህሪህን ፍቺ ይነግርሃል፡፡
ለምሳሌ፣ ጤናማ የሆነ በራስ መተማመን አመለካከት ያለው ሰው የሚገልጠው ባህሪይና የዝቅተኝነት ስሜት ያለው የሚገልጠው ባህሪይ አንድ አይደለም፡፡
እንደተገፋና እንደተናቀ፣ ዝቅተኛ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ማንም ሳይነካው ሰውን የሚነካና የሚተናኮስ ባህሪይ ያዳብራል፡፡ ማንም ገፋው አልገፋው ምንም ለውጥ እንደማያመጣበት የሚያስብ የተረጋጋና አላማው ላይ የሚያተኩር ባህሪይ ይታይበታል፡፡
ለምንም ነገር ያለመመጠን ስሜት ያለበት ሰው የፍርሃትና የአይን አፋርነት ባህሪ ይወርሰዋል፡፡ የሚመጥን ማንነትና አመለካከት እንዳለው የሚያስብ ሰው ደፋርነትና ተግባቢነት ይኖረዋል፡፡
ሰዎች አይፈልጉኝም የሚል ስሜት ያለበት ሰው ለሁሉም ሰውና ለሁሉም ነገር እሺ ባይነት ያጠቃዋል፡፡ ተፈለገም አልተፈለገም ተረጋግቶ የሚኖር ሰው ያመነበትንና ያላመነበትን በመለየት ሃሳቡን መግለጽ ችግር የለበትም፡፡
ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንደማይበቃ የሚያስብ ሰው አታላይና አጭበርባሪ ባህሪይን ያዳብራል፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ራሱን አሰልጥኖ መወዳደር እንደሚችል የሚያምን ሰው ደግሞ ቀጥተኛና እውነተኛ ይሆናል፡፡
በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ጤናማ ሲሆን ማሕበራዊ ግንኙነትህም እንደዚያው ጤናማ ይሆናል፡፡
ስለዚህ ማሕበራዊ ሕይወትህ እንዲስተካከል ከፈለክ በቅድሚያ በራስህ ላይ ያለህን ምልከታ አስተካክለው፡፡
ዶክተር ኢዮብ ማሞ
የስብዕና ልህቀት