የማንሰን የመሸሽ ህግ
"ሰዎች በአብዛኛው ስኬትን የሚፈሩት ውድቀትን በሚፈሩበት ተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡"
ማርክ ማንሶን
የማንሰን ህግ እንዲህ ይላል የሆነ ነገር ማንነትህን በበለጠ ስጋት ላይ በጣለው መጠን፣ በበለጠ ትሸሸዋለህ፡፡
ይህ ማለት ራስህን የምታይበትን መንገድ እንዳትለውጥ ስጋት ላይ የጣለ የሆነ ነገር በኖረ መጠን ራስህን ስኬታማ ወይም ስኬታማ ያልሆነ አድርጎ ለማየት ያለህን እምነት፣ እንዲሁም ራስህን በእሴቶችህ መሰረት የምትኖር አድርገህ የምታይ መሆኑን ለማሳየት በዚያ ነገር ዙሪያ የመገኘትህን ነገር የበለጠ ትሸሻለህ፡፡
በዚህ ዓለም ውስጥ እንዴት ተስማሚ እንደሆንክ ከማወቅ ጋር የሆነ ምቾት አብሮ ይመጣል፡፡ እና ያንን ምቾትህን የሚያነቃንቅ ነገር ሲመጣ፣ ሕይወትህን የተሻለ ሊያደርግ የሚችል እንኳን ቢሆን አስፈሪ ይሆንብሀል፡፡
የማንሰን ህግ በህይወታችን ውስጥ ላሉ ጥሩና መጥፎ ለሆኑ ነገሮች ሁሉ ይሰራል፡፡ ሚሊየን ዶላር ማግኘት ማንነትህን ስጋት ላይ ሊጥለው እንደሚችለው ሁሉ፣ ገንዘብህን ሙሉ በሙሉ ማጣትም ልክ የዚያኑ ያህል አስፈሪ ነው፡፡ ዝነኛ መሆን ልክ ስራህን የማጣት ያህል ማንነትህን ስጋት ላይ ይጥለዋል፡፡ ሰዎች በአብዛኛው ስኬትን የሚፈሩት ውድቀትን በሚፈሩበት ተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ ያም ነን ብለው የሚያምኑትን ማንነታቸውን እና ልማዳቸውን ስጋት ላይ ይጥላል፡፡
ሁልጊዜ የምታልመውን ያንን የፊልም ፅሁፍ መፃፍ የምትሸሸው ያንን ማድረግህ የኢንሹራንስ ሰራተኛ የመሆንህን ማንነት ወደ ጥያቄ የሚያመጣ ስለሆነ ነው፡፡ ባለቤትሽ መኝታ ላይ ምን እንዲሆንልሽ እንደምትፈልጊ መናገር የምትሸሺው ያ ጥያቄ ጨዋ ሚስት የመሆን ማንነትሽ ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ብለሽ ነው፡፡ ጓደኛህን ሁለተኛ ልታየው እንደማትፈልግ የማትነግረው ጓደኝነታችሁን ማቋረጥ ከአንተ ጥሩና ይቅር ባይ ማንነት ጋር ስለሚጋጭ ነው፡፡
እነዚህ ራሳችንን እንዴት እንደምናይና ስለ ራሳችን ምን እንደሚሰማን ያለንን ማንነት ይለውጣሉ ብለን ስለምንፈራ በተደጋጋሚ የምናልፋቸው ጥሩና በጣም አስፈላጊ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡
ለረጅም ጊዜ የአርት ስራዎችን ኦንላይን ላይ አስቀምጦ ፕሮፌሽናል አርቲስት ስለመሆን የሚያወራ አንድ ወዳጅ ነበረኝ፡፡ ለአመታት ስለዚህ ነገር ሲያወራ፣ ገንዘብ ሲያጠራቅም፣ ስራዎቹን የሚያሳይባቸው ጥቂት የተለያዩ ድረገፆች ሳይቀር ሰርቶ ነበር፡፡ነገር ግን ስራዎቹን አላወጣቸውም፡፡ ያንን ላለማድረጉ ሁልጊዜም የሚሰጠው ተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ የሰራው ስራ በበቂ ሁኔታ ጥሩ አይደለም፡፡ ወይም ሌላ የተሻለ ስዕል እየሳለ ነው፡፡ ወይም ለዚህ ጉዳይ በቂ ጊዜ ለመስጠት ገና አልተዘጋጀም፡፡አመታት አለፉ፡፡ የሚሰራውን ስራ ግን አሁንም አልተወም፡፡ ለምን? ምክንያቱም በስዕል ስራ ለመኖር ቢያልምም ማንም የማይወደው አርቲስት ከመሆን ይልቅ ማንም ስለ እርሱ ሰምቶ የማያውቅ አርቲስት ሆኖ መቅረት የበለጠ አስፈሪ ስለሆነ ነው፡፡ ቢያንስ ማንም ስለ እርሱ ሰምቶ የማያውቀው አርቲስት መሆኑ ተመችቶታል፡፡
መጨፈር የሚወድ ሁልጊዜ ለመጠጣትና ሴት ለማሳደድ የሚወጣ ሌላ ጓደኛ ነበረኝ፡ ለአመታት የሀብታም አኗኗር ከኖረ በኋላ ራሱን በጣም ብቸኛ፣ ሀዘንተኛና ጤና ያጣ ሆኖ አገኘው፡፡ ስለዚህ የዚህ የጭፈራ የአኗኗር ዘይቤውን መተው ፈለገ፡፡ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ በገባነውና ከእርሱ በተሻለ በተረጋጋነው በእኛ ቅናት አደረበት፡፡ ግን አልተለወጠም፡፡ ለአመታት ከባዶ ምሽት ወደ ባዶ ምሽት፣ ከጠርሙስ ወደ ጠርሙስ እያለ በዚህ አይነት ሕይወት ቀጠለ። ሁልጊዜ ሰበብ አያጣም፡፡ ሁልጊዜ መረጋጋት የማይችልበት ምክንያት ነበረው፡፡ያንን የአኗኗር ዘይቤ መተው ማንነቱን በእጅጉ ስጋት ላይ የሚጥል ነበር፡፡ መሆን የሚችለው ጭፈራ የሚወድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ ያንን መተው ና ትዳር መመስረት ስነልቦናዊ ክብርን የሚነካ ፤ነፃነትን የሚያሳጣ ና በራስ ላይ ግድያ እንደመፈፀም ነው፡፡
ሁላችንም የየራሳችን እሴቶች እና ልማዶች አሉን፡፡ እነዚህን እሴቶች እንጠብቃቸዋለን፡፡ በእነርሱ መሰረት እንኖራለን። እንከላከልላቸዋለን፡፡ እንንከባከባቸዋለን፡፡ ያንን ለማድረግ ብለን ባይሆንም እንኳን አእምሯችን የተሰራው እንደዚያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደተገለፀው አስቀድመን በምናውቀው ነገርና እርግጠኛ ነን ብለን በምናምንበት ጉዳይ ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ አድሏዊ ነን፡፡ እኔ ጥሩ ሰው ነኝ ብዬ የማምን ከሆነ ያንን እምነቴን ለመቃረን አቅም ያለው ሁኔታ ሲያጋጥመኝ ያንን ሁኔታ እሸሻለሁ፡፡በጣም ጎበዝ ምግብ አብሳይ እንደሆንኩ የማምን ከሆነ፣ ያንን ለራሴ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ደግሜ ደጋግሜ እፈልጋለሁ፡፡ ሁልጊዜ ማመኑ አስቀድሞ ይመጣል፡፡ ራሳችንን የምናይበትን እይታ ምን እንደሆንን ወይም እንዳልሆንን የምናምነውን እስክንለውጥ ድረስ ሽሽታችንንና ጭንቀታችንን ማሸነፍ አንችልም፡፡
ደራሲ ማርክ ማንሶን
https://t.me/+Rn0O-d8bj50OUCcP