የጅምላ ኢጎ
✍️ኤካህርት ቶሌ
ኢጎ በግላዊ ማንነቱ አለመርካቱን ለማመልከት ከሚያደርጋቸው ሙከራዎች አንዱ ከቡድን ጋር አንድ በመሆን የማንነት ስሜቱን ማስፋፋት እና ማጠናከር ነው። እነዚህ ቡድኖች ሃገር፣ብሄር፣ የፓለቲካ ፓርቲ፣ ማህበራት፣ ተቋማት፣ ሴክተሮት፣ ክለብ፣ አደገኛ ቦዘኔዎች ፣ የእግር ኳስ ቡድኖች እና ሌሎችም ሊሆኑ ይችላሉ።
አንዳንድ ጊዜ የሆነ ሠው እኔነቱን ትቶ ለጅምላው መልካም ነገር ሲል ምንም ዓይነት የግል ጥቅም፣ ችሮታ ወይም ክብር ሳይፈልግ፣ ህይወቱን እስከመሰዋት ድረስ ሲሰራ ግላዊ ኢጎው የከሰመ ሊመስል ይችላል። የቡድኑ ያህል ዋጋ ቢከፍሉም፣ደስተኝነት ሙሉነት ይሰማቸዋል። ከኢጎ ባሻገር የሄዱ መስለው ይታያሉ። ነገር ግን ከኢጎ ነፃ ወጥተው ሳይሆን ኢጎ ከግላዊ ወደ ጅምላዊ ተሸጋግሮ ነው።
የጅምላ ኢጎ ልክ እንደ ግል ኢጎ ግጭትንና ጠላትን የመፈለግ፣ በተሳሳቱ ሌሎች ላይ ትክክል መሆንን መፈለግ እና የመሳሰሉት ተመሳሳይ ባህሪያት አሉት። ፈጠነም ዘገየም፣ ቡድኑ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱ አይቀርም፤ ምክንያቱም ግጭትንና የራሱን ክልል ለመወሰን ብሎም ማንነቱን ለማግኘት ተቃውሞን ሳያውቅ ይፈልግ ነበር።አባሎቹም ማንኛውም ከኢጎ ተነሳሽነት የሚፈጠረውን ተግባር ጋር ተከትሎ የሚመጣውን ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ። በዚህም ጊዜ የነበሩበት ቡድን ጠንካራ የጥፋት ተልዕኮ እንደነበረው ሊነቁና ሊገነዘቡ ይችላሉ።
የነበርክበት እና እራስህንም ያዛመድክበት ብሎም ስትሰራለት የነበረው ቡድን፣ በርግጥ የጥፋት መሆኑን በድንገት ስትረዳ በመጀመሪያ የሚያም ይሆናል፡በዚያ ጊዜ አንዳንዶች የበለጠ ክፉና መራር ይሆናሉ። ይህም ማለት የቀድሞው ሃሳብ፣ውዥንብር እና የወደቀ መሆኑን ሲረዱ ወዲያውኑ የሌላ አይነት ዕምነት ስርዓት ይቀበላሉ ማለት ነው። የኢጎአቸውን ሞት ከመቀበል ይልቅ፣ ከዚያ በማምለጥ በሌላ አዲስ ኢጎ ዳግም ይወለዳሉ።
የጅምላ ኢጎ ጅምላውን ከፈጠሩት ግለሰቦች ኢጎ በላይ ማስተዋል የለሽ ነው። ለምሳሌ ሰልፈኞች (ጊዜያዊ የጅምላ ኢጎ ስብስቦች) ግለሰቦቹ ከሰልፈኞቹ ውጪ ቢሆኑ ኖሮ የማይፈፅሙትን አይነት ከፍተኛ ጥፋት የመፈፀም አቅም አላቸው። በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ኖሮ ዕብደት ተደርጎ የሚወሰድን ተግባር፣ አገሮች ግን በተደጋጋሚ ሲፈፅሙት ይታያል።
የሰዎች፣ የብሄሮችና የሐይማኖት ተቋማት የጅምላ ኢጎ ፣ “እኛ ቅዱሶች፣ ሌሎች እርኩሶች” የሚል ጠንካራ የፓሪኖያ ችግር አለበት። የስፔናውያን ስቃይ፣ አፈንጋጮችንና “ጠንቋዮች”ን ማንገላታት እንዲሁም ማቃጠልና፣ እስከ ኣንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድረስ የደረሰው የሐገራት ግንኙነት፣ አጠቃላይ የኮሚዩኒዝም ታሪክ፣የመስቀል ጦርነት ፣ጀሀድ፣ ቀዝቃዛው ጦርነት፣ በ1990ዎቹ በአሜሪካ የነበረው ማካርቲዝም፣ እስካሁን የዘለቀው የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፣ ሁሉም በሰው ልጆች ውስጥ በእጅጉ አሰቃቂ እና በፅንፈኛ ጅምላዊ የኢጎ በሽታ የተሞሉ የታሪክ ክፍሎች ናቸው።
ግለሰቦች፣ ቡድኖች አገሮች እስተዋይ ባልሆኑ ቁጥር፣ይሄ ኢጎአዊ በሽታ ወደ አካላዊ ጥቃት መሸጋገሩ አይቀሬ ነው። አካላዊ ጥቃት ኋላቀርነት ይሁን እንጂ
አሁንም ድረስ የተንሰራፋ ተግባር ነው። ምክንያቱም ኢጎ የእራሱን አሸናፊነት መጠበቅ፣ እራሱን ትክክል ሌሎች ስህተት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲል ይጠቀምበታል። ማስተዋል የለሽ በሆኑ ሠዎች መካከል ትንንሽ ክርክሮች ወደ አካላዊ ጥቃት በቀላሉ ያመራሉ። ክርክር ምንድን ነው? ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሠዎች የየራሳቸውን ምልከታ ይገልፃሉ፤ እነዛም ምልከታዎች ይለያያሉ። እያንዳንዱ ሠው ምልከታው ከፈጠረለት ሃሳብ ጋር አንድ ከመሆኑ የተነሳ፣ ሃሳቦቹ ጠንክረው የማንነትና የሃሳብ ስሜት ላይ የዋሉ አዕምሮአዊ እቋም ይሆናሉ። በሌላ አባባል ማንነትና ሃሳብ ይቀላቀላሉ። ይህ ከሆነ ደግሞ ለአመለካከቴ ስከራከር ወይም ስቆም ፣ ልክ እራሴን እንደምከላከል ይሰማኛል፤ እተውናለሁም። ሳላስተውለው ልክ ለህልወናዬ እንደምዋጋ እሆናለሁ፤
ስሜቶቼም የዚህን ማስተዋል የለሽ እምነት ያንፀባርቃሉ። እበሳጫለሁ፣ እናደዳለሁ፣እከላከላለሁ ወይም ኃይለኛ እሆናለሁ። እንዳልጠፋ በሚል ስጋት፣ ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል
ማሸነፍ አለብኝ።ውዥንብሩ ያ ነው። ኢጎ እራሱ የማትመለከተው አዕምሮ በመሆኑ ምክንያት አዕምሮም ሆነ ሀሳባዊ አቋሙ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አያውቅም።
@zephilosophy