ኢትዮጵያ ከስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናነች ያለችውን ጥረት ኔዘርላንድ እንደምትደግፍ አስታወቀች
ኢትዮጵያ ከስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናነች ያለችውን ጥረት ኔዘርላንድ እንደምትደግፍ የአገሪቱ የፍትህና ደህነነት ሚኒስቴር የአለማቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ሮብ ቫን ባህሆቨን ገልፀዋል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በዋና ዳይሬክተሩ የተመራን የኔዘርላንድ ፍትህና ደህንነት ሚኒስቴር ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ
በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ተግባር በሚመለከትና በቀጣይ ከኔዘርላንድ ጋር በዘርፉ ያለን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለልዑኩ ገለፃ አድርገዋል።ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ በሪፎርም ሂደት ላይ መሆኑን እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ለልዑኩ አስረድተዋል፡፡
ሮብ ቫን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾችን በሚመለከት እያከናወነች ያለችውን ስራ እንደሚያደንቁ ገለፀው አገራቸው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ሁለቱ አካላት በተለይም በአቅም ግንባታ ዘርፍ ላይ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ በጋራ ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዬች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
--
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia