ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ጥረት እንግሊዝ እንደምትደግፍ አስታወቀች።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በም/አምባሳደር ሉክ ቡሎክ የተመራ ልዑክ፣ ክሪስ ዊሊያምስ ስደት ተመላሾች ዳይሬክተር፣ ጀኒ ጆንስ ፓለቲካል ኮንስለር ፣ ጆን ፌርክላው አለምአቀፍ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ተግባር በሚመለከትና በቀጣይ ከእንግሊዝ ጋር በዘርፉ ያለን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
አክለውም ተቋሙ በሪፎርም ሂደት
ላይ መሆኑን እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ ኢትዮጵያ ወደ ኢ ፓስፓርት መግባቷን ተናግረዋል፡
ሉክ ቡሎክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾችን በሚመለከት እያከናወነች ያለችውን ስራ እንደሚያደንቁ እና አገራቸው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን በማረጋገጥ የተቋሙን ሰራተኞች ስልጠና ለመስጠትና ሌሎች ቴክኒካል ድጋፎችን ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
በመጨረሻም ተቋሙ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሰራ ያለውን ስራና ኢ ፓስፖርት
መጀመሩን አድንቀዋል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተቋሙ የሚሰጠው ስልጠና የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና የሚኖረው ስለሆነ ለሚደረግላቸው ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
--
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia