በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መካከል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃን በተመለከተ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መካከል የጋራ ኃላፊነትን በጋራ አሰራርና እቅድ ለማከናወን የተስማሙት ሁለቱም ተቋማት የስምምነቱ ዋና ዓላማ ሁለቱም ተቋማት አግባባዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የቫይታል ስታቲስቲክስ ስርዓትን ለማጠናከር በጋራ የሚያከናውኗቸውን ተግባራትን በግልፅ በማስቀመጥ ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስርዓት የሚመነጩ መረጃዎች ለህግ፣ ለአስተዳደር እና ለስታቲስቲክስ ዓላማዎች በማዋል ዜጎችና መንግሥት ከስርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።
ስምምነቱን የፈረሙት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሁሉም አቀፍ የሪፎርም ስርዓት እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያን የሚመጥን ዘመናዊ፣ ጥራቱንና ደረጃው የጠበቀ ተደራሽ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርአትን መተግበር የሚያስችል ከህግ፣ ከአሰራር፣ ከአደረጃጀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ከማዘመን የሚስተዋሉ ችግሮች በመሰረታዊነት ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም በወሳኝ ኩነት ምዝገባና ማሳወቅ ስርአት ባለድርሻ የሆኑትን ተቋማት በተለይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት እና ጤና ሚኒስትር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለስምምነቱ ተግባራዊነት ሁለቱም ተቋማት በቁርጠኝነት እንደሚነሱና የሚጠበቀውን ውጤት እውን ከማድረግ እምነታቸውን የፀና መሆኑ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር በከር ሻሌ በበኩላቸው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከተጀመረ አስር አመት ቢያስቆጥርም በቅንጅታዊ አመራር ድክመት ምክንያት ኢትዮጵያ የምትፈልገውን የወሳኝ ኩነት ዳታ ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀው ስምምነቱ ተቋማቱን ያላቸው የጠበቀ የስራ ግንኙነት ከማጠናከርና አገሪቱ የምትፈልገው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃ ለማግኘት ዓይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/