👉 ቀን ጥሎኝ ብታየኝ
¯¯¯¯¯¯---_
👌 አንዳንድ ንግግሮች ባለቤታቸው ቦታ ሳይሰጣቸው ይናገራቸውና ዱንያውንም አኼራውንም የሚያበላሹ ይሆናሉ። ከእንደነዚህ አይነት ንግግሮች ውስጥ ምን ታረገው ቀን ጥሎኝ አይተኸኝ የሚለው ሲሆን ሀብታም የነበረ ወይም በጀግንነቱ የሚታወቅ የነበረ ወይም ትልቅ ስልጣን የነበረውና በኋላ ሁኔታዎች የተቀየረበት ሰው የሚናገረው ይገኝበታል። እንደዚሁ አንዳንድ እህቶች በተለይ ዐረብ ሀገር ያሉ ስራ ፈተው ለብዙ ጊዜ በመቀመጥ ሲቸገሩና ሲከሱ ሲጎሳቆሉ ይህን ንግግር ይጠቀማሉ።
➩ በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የዚህን አይነት ንግግር መናገር ወንጀሉ በጣም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ከዐቂዳ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።
✅ በመጀመሪያ አንድ ሙስሊም የሚናገረውን ንግግር አስቦና የሚያመጣውን ጥቅምና ጉዳት አመዛዝኖ መናግር ነው ያለበት። የአላህ መልእክተኛ ሳያመዛዝን የሚናገር ሰው ንግግሩ የሚያመጣውን መዘዝ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
عَنْ أَبي هُرَيْرَةَ أَنَّهُ سَمِعَ النَّبيَّ – ﷺ – يَقُولُ : "إنَّ الْعَبْد لَيَتَكَلَّمُ بِالكَلِمةِ مَا يَتَبيَّنُ فيهَا يَزِلُّ بهَا إِلَى النَّارِ أبْعَدَ مِمَّا بيْنَ المشْرِقِ والمغْرِبِ".
📚 متفقٌ عليهِ
"አንድ ሰው አንዲትን ንግግር የሚያስከትለውን ሳያውቅ ይናገርና ከፀሀይ መውጫ እስከ ፀሀይ መግቢያ ርቀት ወዳለው እሳት ይወድቃል።"‼
🏝 ተመልከቱ እንደቀልድ በተናከርነው አንድ ንግግር የሚመጣው ውጤት። ቀን ጥሎኝ የሚለው ንግግር ደግሞ በጣም አደገኛና ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ነው። አንድ ሰው ይህን ንግግር ሲናገር ቀን መጣልና ማንሳት (ማበልፀግና ማደህየት) ይችላል የሚል እምነት ኖሮት ከሆነ ይከፍራል ከእስልምናም ይወጣል። ነገር ግን ይህ እምነት ሳይኖረው እንደቀልድ ከሆነ የተናገረው ትንሹ ሽርክ ነው። ይህ ማለት ከከባባድ ወንጀሎች ይመደባል። ምክንያቱም ቃሉ ቀን መጣል ይችላል የሚል መልእክት ስለያዘ።
🔦 በመሆኑም ሙስሊም የሆነ ሰው ከመናገሩ በፊት ስለሚናገረው ነገር ማወቅና ማመዛዘን ይኖርበታል። ከዚህ በተጨማሪ ቀኑን በመኮነን መልኩ ከሆነ ሌላ ጥፋት ነው። ምክንያቱም ቀን ምንም ነገር ማድረግ አይችልም። የአላህ ስራ የሚያርፍበት ብቻ ነው። ይህ ከሆነ የምንኮንነው አላህን ነው ማለት ነው። ቀን ይነጋል ይመሻል የሚያመሸውና የሚያነጋው አላህ ነው። ለዚህ ነው ዘመንን አትስደቡ የተባለው። ምክንያቱም ዘመን የአላህ ስራ ማረፊያ ከሆነና በቀኑ ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮች የሚያስከስታቸው እሱ ከሆነ የምንሰድበው አላህን ነው ማለት ነው!!! ይሄ ደግሞ ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ወንጀል ነው።
🔍 አንድ ሰው በየትኛውም ጊዜ ምንም ነገር ቢደርስበት ይህ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው የደረሰው ብሎ ማመን አለበት። ይህ በቀደር ማመን ይባላል። በቀደር ማመን ደግሞ የኢማናችን አስኳል ነው። በሌላ አባባል አሁንም ቀን ጥሎኝ የሚለው ንግግር ከቀደር ጋር ያጋጨናል ማለት ነው። ምክንያቱም በአላህ ውሳኔ ያመነ ሰው በማንም በምንም አያማርም። ይልቁንም አላህ ወስኖ ያሻውን ሰራ ነው የሚለው። በዚህም ወደ አላህ ይቃረባል የአላህንም ውዴታ ያገኛል። በቀን ማማረር ትርፉ ኪሳራ ነው።
👉 ሌላው መከራም ይሁን ችግር የሚያገኘን በሰራነው ወንጀል መሆኑን ማመን ይኖርብናል። የበሽታና የርዝቅ እጥረት መንስኤ የራሳችን ወንጀል ነው። በተለይ ዐረብ ሀገር ያላችሁ እህቶች መጀመሪያ ከሀገር ያለ መሕረም ስትወጡ ጀምሮ ወንጀል ላይ ወድቃችኋል። እዛ ሆናችሁ አላህን ፈርታችሁ ላለፈው ተፀፅታችሁ ወደ አላህ መቅረብ ይኖርባችኋል። በተለይ ኢጃዛ በምትወጡ ጊዜ አላህ ካዘነላት ውጪ አብዛኛዎች እህቶች ወንጀል ላይ ነው የሚዘፈቁት። ከአጅ ነብይ ወንድ ጋር አብረው ነው የሚሆኑት የዝሙትና የተለያዩ ወንጀል አይነቶች ይፈፀማሉ።
▷ አላህን ፈርተናል የሚሉ እህቶችም ቢሆን በራሳቸው ቤት መከራየት ስለማይችሉ አንድ ወንድ ከ20 – 30 ሴቶችን ይሰበስብና ያችንም እቺንም አገባሻለሁ እያለ እየበዘበዘ አላህን ካመፀ በኋላ እነርሱንም አይናችሁ ላፈር ይላል። በአብዛኛው እንደነዚህ አይነት ወንዶች የሚፈልጉዋቸውን እህቶች በተለያየ የኢጃዛ ጊዜ እንዲመጡ በማድረግ ነው የሚፈልጉትን የሚሰሩት። ያቺም ከኔ ጋር ነው ትላለች እቺም ከኔ ጋር ነው ትላለች እሱ ግን ከማናቸውም ጋር አይደለም ከገንዘባቸውና ከሸህዋው ጋር ነው። የዚህ ወንጀል መጨረሻ እህቶችን ቀን ጥሎኝ ነው ብለው ሌላ ወንጀል ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።
▰ ለማንኛውም አላህን ፈርተን ቀንን ከመተቸትና አላህን ከሚያስቆጣ ወንጀል እንውጣ።
https://t.me/bahruteka