መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~~~
የመውሊድ ደጋፊዎች ለዚህ ቢድዐ የሚያጣቅሱት ትልቁ ማስረጃ እነ እከሌ ደግፈውታል እያሉ ዑለማዎችን ማጣቀስ ነው። በርግጥ የኖሩበት ዘመን ድባብ ተፅእኖ አሳድሮባቸው ከመረጃ ያፈነገጠ ሃሳብ ቢያንፀባርቁ ይህ የሚደንቅ አይደለም። እንዲያውም ጉዳዩ ይለያይ እንጂ በእንዲህ አይነት ተፅእኖ ስር በመውደቅ እነሱ የመጀመሪያ አይደሉም። የሆነ ሆኖ አብዛኞቹ መውሊድን ፈቅደዋል የሚባሉት ዓሊሞች ዛሬ መውሊድ ላይ በሚታየው መልኩ አይደለም የፈቀዱት። ይሄውና አይታችሁ ታዘቡ፡-
1. አተዝመንቲ (682 ሂ.?)፡-
“የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” “መውሊድ …ፈፃሚው ደጋጎችን መሰብሰብ፣ በነብዩ ላይ ሶለዋት ማውረድ፣ ድሆችንና ምስኪኖችን ምግብ ማብላትን ካሰበ መልካም ቢድዐ ነው። በዚህ ልክና በዚህ ሸርጥ (መስፈርት) ከሆነ ይመነዳበታል። እንጂ ቂላቂሎችን መሰብሰብ፣ ዜማ ማዳመጥ፣ መደነስና ልብስ ማውለቅ … ካለበት አይወደድም። እንዲያውም ሊወገዝ የቀረበ ነው። መልካም ቀደምቶች ካልሰሩት ነገር ውስጥ መልካም የለም።” [አሲረቱ ሻምያህ፡ 1/441-442]
ሁለት ነገሮችን ያዙ፦
አንድ፦ የመውሊድ በዓል በመልካም ቀደምቶች ዘመን እንደማይታወቅ።
ሁለት ፦ በጥፋት የታጀበ መውሊድ እንደማይደግፉ። ዛሬ ደግሞ እሳቸው ካወገዙትም በላይ መውሊድ እጅግ በርካታ ሰቅጣጭ ጥፋቶችን ያጨቀ ሆኗል።
2. ኢብኑል ሓጅ (737 ሂ.)፦
“ትልልቅ ከሆኑ ዒባዳዎችና የዲን መገለጫዎች እንደሆነ በማመን ሰዎች ከፈጠሯቸው ቢድዐዎች የሚካተተው በረቢዐል አወል ላይ የሚሰሩት መውሊድ ነው። በርግጥም በርካታ ቢድዐዎችንና ክልክል ነገሮችን አጭቋል። ከዚህ ውስጥ ዘፈኖችን መጠቀማቸው ተጠቃሽ ነው። ከነሱ ጋር ከበሮ፣ ዋሽንትና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ይኖራሉ። በዚህም የዘፈን ድግስ አድርገውታል። አንተንም እኛንም አላህ ይዘንልንና ምን ያክል ንፁህ የሆነችዋን ሱና መፃረር እንዳለ፣ ምንኛ አስቀያሚ እንደሆነ፣ ምንኛ አስነዋሪ እንደሆነ፣ እንዴት ወደ ሐራም ነገሮች እንደሚጎትት ተመልከት። ንፁህ የሆነችዋን ሱና በተፃረሩ ጊዜ፣ መውሊድንም በፈፀሙ ጊዜ መውሊዱ ላይ ብቻ እንዳልተገደቡ አታይምን?! ይልቁንም የተወሱትን በርካታ ከንቱ ነገሮች ጨመሩበት። እድለኛ የታደለ ማለት ቁርኣንና ሱናን በመተግበርና ወደዚያ በሚያደርስ ነገርም ላይ እጆቹን ያሰረ ነው። እሷም ያለፉትን ቀደምቶች መከተል ነው፣ ሁሉንም አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸውና። ምክንያቱም እነሱ ከኛ የበለጠ ሱናን የሚያውቁ ናቸውና። ምክንያቱም ንግግርን ይበልጥ የሚያውቁ፣ ሁኔታንም ይበልጥ የሚረዱ ናቸውና። ልክ እንዲሁ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ በመልካም የተከተላቸውን መከተል ይገባል። ከዘመናችን ሰዎች ባህሎችና ዝቃጭ ባህሎችን ከሚፈፅሙ ሰዎች ይጠንቀቅ።
ዘፈን ከኖረ እነዚህ ጥፋቶች በመውሊድ ተግባር ላይ የተደራረቡ ናቸው። ከሱ የፀዳ ሆኖ ምግብ ብቻ ካዘጋጀ በዚህም መውሊድን ካሰበና ወንድሞችን ወደሱ ከጠራ፣ ቀደም ብለን ከጠቀስነው ሁሉ ነፃ ከሆነ በኒያው ብቻ ቢድዐ ይሆናል። ምክንያቱም ይሄ በዲን ላይ ጭማሬ ነውና። ካለፉ ቀደምቶች ስራም አይደለምና። እናም እነሱ ከነበሩበት ተፃራሪ የሆነ ኒያ ከመጨመር ይልቅ ቀደምቶችን መከተል በላጭ ነው። ኧረ እንዲያውም ግዴታ ነው። ምክንያቱም እነሱ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሱና በመከተል፣ እሳቸውንና ሱናቸውን በማላቅ ከሰው ሁሉ በላጮች ነበሩና። ለነሱ ወደዚህ በመሽቀዳደም በኩል የቀዳሚነት ማእረግ አላቸው። ከነሱ ከአንዳቸውም መውሊድን እንዳሰበ አልተላለፈም። እኛም ለነሱ ተከታዮች ነን። ስለሆነም የበቃቸው ይበቃናል።” [አልመድኸል፡ 2/204-312]
ስለ ጭፈራና ማጨብጨብ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡- “የሆነ ሰው በ 661 እንዲህ የሚል ጥያቄ አዘጋጅቶ ወደ አራቱም መዝሀብ ምሁራን ዘንድ አመራ፡- ‘ክቡራን የዲን መሪዎች የሆኑ ምሁራንና ሙስሊም ዑለማዎች አላህ እሱን ለመታዘዝ ያድላቸው፣ በውዴታውም ላይ ያግዛቸውና የሆኑ የሙስሊም ስብስቦች ወደሆነ ሃገር ሄዱና ወደ መስጂድ አመሩ። በውስጡም ማጨብጨብ፣ መዝፈንና አንዲሁም አንዳንዴ በእጃቸው አንዳንዴ በድቤዎችና በዋሺንቶች መጨፈር ያዙ። በሸሪዐ ይህን መስጂድ ውስጥ መፈፀም ይቻላልን? አላህ ምንዳችሁን ይክፈላችሁና ፈትዋ ስጡን ..’ የዚህን ጊዜ
* ሻፊዒያዎች፡- ‘እንዲህ አይነት መዝሙር መስማት የተጠላ ነው። ባጢል ነው የሚመስለው። ይህን የሚዘምር ሰው ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረውም። ወላሁ አዕለም’ አሉ።
* ማሊኪያዎች፡- ‘በመሪዎች ላይ እነዚህን ተውበት አድርገው ወደ አላህ እስከሚመለሱ ድረስ ሊከለክሏቸውና ከመስጂድ ሊያስወጧቸው ግዴታ አለባቸው። ወላሁ አዕለም’ አሉ።
* ሐንበሊያዎች፡- ‘ይህን የሚሰራ ሰው ከኋላው አይሰገድም። ምስክርነቱ ተቀባይነት የለውም። ዳኛ ከሆነ ፍርዱ ተቀባይነት የለውም። ኒካሕ ካሰረም ኒካሑ ውድቅ ነው። ወላሁ አዕለም’ አሉ።
* ሐነፍያዎች፡- ‘የተጨፈረባት ምንጣፍ እስከምትታጠብ ድረስ አይሰገድባትም። የተጨፈረባት መሬትም አፈሯ ተቆፍሮ እስከሚወገድ ድረስ አይሰገድባትም። ወላሁ አዕለም’ አሉ።” [አልመድኸል፡ 3/99]
3. አልወንሺሪሲ (834 ሂ.)፡-
“ሙስሊሞች ዘንድ የተከበረ ቢሆንም ነገር ግን በሱ ውስጥ አንዳንድ ቢድዐዎች እስከሚፈፀሙበት ያደረሱት ጉዳዮች አሉ። ይህም በብዛት በዘፈን መሳሪያዎች መገኘትና በሌሎችም ያልተፈቀዱ ፈጠራዎች ምክንያት ነው። እሳቸውን ﷺ ማላቅ ሊሆን የሚገባው ሱናቸውን በመከተልና ፈለጎቻቸውን በመፈፀም ነው። እንጂ መልካም ቀደምቶች ዘንድ ያልነበሩ ቢድዐዎችን በመፍጠር አይደለም።” [አልሚዕያሩል ሙዕሪብ፡ 1/357-358]
4. ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒ (852 ሂ.)፡-
የመውሊድ ደጋፊዎች የሚያጣቅሱት የኢብኑ ሐጀር ንግግር እንዲህ የሚል ነው፡- “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም። ይህም ከመሆኑ ጋር ግን መልካም ነገሮችንም አፍራሾችንም ይዟል። በዚህ ተግባር ላይ አፍራሾቹን ርቆ መልካሞቹ ላይ ያነጣጠረ መልካም ቢድዐ ይሆናል። ካልሆነ ግን አይቻልም።” ” [አልሓዊ፡ 1/228]
አስተውሉ!
* መውሊድ ከኢብኑ ሐጀር ዘንድ ቢድዐ እንጂ ሱና አይደለም።
* “በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች (ሶሐቦች፣ ታቢዒዮችና አትባዑ ታቢዒን) ከአንድም አልተላለፈም” ማለታቸው ደግሞ “ነብዩ ﷺ እና ሶሐቦቻቸው አክብረውታል” የሚሉ ቀጣፊዎችን ወሽመጣቸውን የሚቆርጥ ነው።
* መውሊድ ውስጥ ጥፋቶች እንደሚገኙ መግለፃቸው የዛሬ መውሊድ ጨፋሪዎች ዘንድ የማይገኝ ምስክርነት ነው።
* አፍራሽ ነገሮቹ ካልተራቁ መውሊዱ እንደማይፈቀድ መናገራቸው ደግሞ ከዛሬ መውሊድ አክባሪዎች ጋር ፈፅሞ እንደማይገጥሙ ማሳያ ነው።
እነዚህን ነጥቦች ያስተዋለ ሰው እንጥፍጣፊ ታክል ሚዛናዊነት ካለው ኢብኑ ሐጀርን ዛሬ ለሚፈፀመው መውሊድ ለማጣቀስ አይዳፈርም።
5. ሲዩጢ (911 ሂ.)፡-