መውሊድ ተከሽኖ
~~~~ ~~~~ ~
ከኢኽዋን ቡድን አብይ መታወቂያዎች አንዱ ለቢድዐ አንጃዎችና ለቢድዐ ድግሶች ሽፋን መስጠት ነው። በዚህ ረገድ ከሚነሱት ውስጥ አንዱ የመውሊድ ቢድዐ ነው። በየአመቱ በአንድ ወይም በሆነ መንገድ ለመውሊድ ሽፋን ሲሰጡ ማየት የተለመደ ነው፦
* ከፊሎቹ በቀጥታ ለመውሊድ ቢድዐ ሽንጣቸውን ገትረው ይሟገታሉ፤ ከነ ምናምኑ ከሱፍዮች ጋር እኩል ያከብራሉ።
* ከፊሎቹ መውሊድን ማክበርም፣ አለማክበርም ከዑለማእ ተገኝቷል በዚህ ልንጨቃጨቅ አይገባም በማለት ለዚህ በሺርክና ቢድዐ ለታጨቀ የዲን ነቀርሳ በዓል ውግንና በማሳየት ነቃፊዎቹን ፅንፈኛ አድርገው ይስላሉ።
* ከፊሎቹ በሽርክ፣ በቢድዐና በጭፈራ ከታጀበው የሱፍዮች መውሊድ ላይ ተገኝተው “ሆደ ሰፊነታቸውን” ያሳያሉ። እውነትም የሆድ ስፋት እንጂ የህሊና ስፋት ይህንን አይቀበልም።
* ከፊሎቹ አመት ጠብቀው በዚህ ሰሞን በግጥም፣ በነሺዳ፣ በኤግዚቢሽን፣ በባዛር፣ ... ብቻ በየትም በየትም ብለው የሆነ ስም ፈልገው ሽር ጉድ ይላሉ። ሱፍዮቹ ዘንድ ከነሱ ያልራቁ ለዘብተኞች ሆነው ሲታዩ፣ መውሊድን ነቃፊዎች ዘንድ ደግሞ የሱፍዮቹን ኮተት የሚፀየፉ መስለው ይታያሉ።
የመውሊድ በአል በብዙ ጥፋቶች የታጀበ ቢድዐ እንደሆነ አሳልፈናል። ከመሆኑም ጋር የነዚህን ሰዎች “በአይነቱ ለየት ያለ” የመውሊድ አከባበር ተከትሎ “ከጥፋት የፀዳ ከሆነስ ይፈቀዳል ወይ?” የሚል ጥያቄ ሲነሳ ያጋጥማል። እንዲህ አይነት ጥያቄ የሚያነሳ ሰው በርግጠኝነት መሰረታዊ የቢድዐ ግንዛቤ የለውም። ቢድዐነቱ ከተረጋገጠ በኋላ “ከጥፋት ከፀዳስ?” ማለት “የአሳማ ስጋ ከታጠበ ይበላል ወይ?” ብሎ እንደመጠየቅ ነው። የአሳማ፣ የውሻ፣ የበክት ስጋ ታጠበም አልታጠበም ነጃሳ ነው፣ ሐራም ነው። ስለታጠበ የሚቀየር ብይን የለም። ቢድዐም ልክ እንዲሁ ነው። ነብዩ ﷺ “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው”፣ “ወደ እሳት የሚያደርስ ነው”፣ “ፈፃሚውም የተረገመ ነው”፣ “ከተውበት የተጋረደ ነው” ብለዋል። ይህ ሁሉ የተባለው ሌላ ጥፋት ሲታከልበት ሳይሆን በቢድዐነቱ ብቻ ነው። ሌሎች ጥፋቶች ሲጨመሩ የጥፋቱ ክብደት እንደሚጨምር የሚሰወር አይደለም። ልክ የአሳማ ስጋ ብቻውን መብላትና በቢራ እያወራረዱ መብላት አንድ እንዳልሆነው ማለት ነው። የቢራው መቅረት አሳማውን ሐላል እንደማያደርገው፣ የሌሎች ጥፋቶች መቅረትም መውሊድን ፍቁድ አያደርገውም። በመውሊድ ላይ የሰላ ሂስ የሰነዘሩት ታጁዲን አልፋኪሃኒ (734 ዓ. ሂ.) ረሒመሁላህ ይሄ ቢድዐ በሰለፎች ዘመን ያልታወቀ አጉል ፈሊጥ መሆኑን ካስረገጡ በኋላ እንዲህ ሲሉ ጉዳዩን ለሁለት ከፍለው ያስቀምጡታል፦
“አንዱ፡- አንድ ሰው ከራሱ ገንዘብ ለባለቤቱ፣ ለጓደኞቹና ለቤተሰቡ የሚያዘጋጀው ነው። በዚህም መሰባሰብ ላይ ምግብን ከመብላት ላያልፉና ወንጀሎችን የማይፈፅሙ ከሆነ ነው። ይህንን ነው የተጠላ ቢድዐና አስቀያሚ ነገር እንደሆነ የገለፅነው። ምክንያቱም የዘመናት መብራት፣ የሃገራት ውበት የሆኑት ምሁራኖችና የኢስላም ሊቃውንት የሆኑት ቀደምት የአላህ ታዛዦች አልሰሩትምና።
ሁለተኛው፡- ወንጀል የሚገባበትና (ይህን ቢድዐ ለማክበር ገንዘብ ለመሰብሰብ) ትኩረት የሚበረታበት ነው። አንዳንዱ ነፍሱ የተንጠለጠለ ሆኖ፣ ከግፉ ህመም የተነሳ ልቡ እያሳመመው የሆነን ነገር እስከሚሰጥ የሚደርስበት ነው። ዑለማዎችን አላህ ይማራቸውና ‘እፍረት አስይዞ ገንዘብን መውሰድ በሰይፍ እንደመውሰድ ነው’ ይላሉ።
በተለይ ደግሞ በዚህ ላይ ከጠገቡ ሆዶች ጋር እንደ ድቤና ዋሽንት ያለ በከንቱ መሳሪያዎች የታጀበ ዘፈን ካለ፣ እንዲሁም ወንዶች ከወጣቶችና ከዘፋኝ ሴቶች ጋር መቀላቀል ከኖረ ወይ ከወንዶቹ ጋር ተቀላቅለው ወይ ደግሞ ከከፍታ ላይ ዘልቀው፣ እየተጣጠፉ በመጨፈር፣ ከዛዛታ ውስጥ መስመጥና አስፈሪውን (የቂያማ) ቀን መዘንጋት የሚደረስበት ነው።
ልክ እንዲሁ ሴቶች ብቻቸውን ሲሰባሰቡ ያለምንም ሀፍረት ድምፃቸውን በዘፈንና በነሺዳ ከፍ ያደርጋሉ። ከተለመደው የቁርኣን አቀራርና ዚክር አልፈው ከሸሪዐው ይወጣሉ። የላቀው ጌታ {ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና} ማለቱን ይዘነጋሉ። ይሄ ክልክል በመሆኑ ላይ ሁለት ሰዎች አይወዛገቡበትም። ስርኣት ያላቸው አስተዋዮች በጥሩ አያዩትም። ይሄ የሚፈቀደው የሞቱ ቀልቦችን ከያዙና ወንጀልንና ሃጢኣትን ከሚያበዙ ሰዎች ዘንድ ነው። እንዲያውም ልጨምርህና እነሱ እንደ ዒባዳዎች እንጂ እንደ መጥፎና ክልክል ነገሮች አይቆጥሩትም። ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን!! ‘ኢስላም እንግዳ ሆኖ ነው የጀመረው። እንግዳ ሆኖም ይመለሳል።’” [አልመውሪድ ፊ ዐመሊል መውሊድ]
ኢማሙ ሸውካኒም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- “ ‘መውሊዱ ላይ ለምግብ መሰባሰብና ዚክር ብቻ ከሆነ ይፈቀዳል፣ አብረውት የሚያጅቡት ነገሮች ክልክል መሆናቸው ክልክልነቱን አያሲዝም’ የሚሉ ሰዎች ማመሀኛ ፉርሽነቱ ከዚህ ላይ ግልፅ ይሆንልሀል። ምክንያቱም እኛ እራስህ እንዳመንከው መውሊድ ቢድዐ ከመሆኑ ጋር በልምድ ከብዙ መጥፎ ነገሮች ጋር የተቆራኘና ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ ሆኗል። ከምግብና ከዚክር ውጭ ያሉ ነገሮችን የማያካትቱ መውሊዶችን ማግኘት ከቀይ ድኝ የበለጠ ፈታኝ ነው።” [አልፈትሑ ረባኒ፡ 2/1090-1091]
በነገራችን ላይ ኢኽዋን እንደ ቡድን በጣም ግርግር ይወዳል። ድግሶቹ ላይ አጅነቢ ሴቶችን ካላጋፋ አይደምቅለትም። ከስንት አንድ ካልሆነ በስተቀር የኢኽዋን ድግሶች በዚህ የታወቁ ናቸው። የሚፈለገውም ተሽቀርቅረው በሚገኙ ሴቶች አማካኝነት ወንዶቹን መሳብ ነው። ሴቶቹም እንዲህ አይነቱን ትርምስ ይፈልጉታል። በዚህ መልኩ እየተሳሳቡ ድግሱን ማድመቅ!! ስለዚህ ካላስፈላጊ ቅልቅል፣ በሙዚቃ መሳሪያዎች ከታጀቡ ዜማዎች፣ ከንቶፈንቶ የፀዳ ድግስ እዚያ ሰፈር ብዙም አይጠበቁም። እንዲያውም ከዚህም አልፎም በሺርክ የታጨቁ መንዙማዎች ሳይቀሩ ሊገኙ ይችላሉ።
በሆነ ተአምር ተሳክቶ ከነዚህ ነገሮች ቢፀዳ እንኳ የመውሊድ ዝግጅት ከሐራምነት አይወጣም። ምክንያቱም ቢድዐ ነዋ!! እንዲያውም ግልፅ ከሆኑ ወንጀሎች የከፋ ጥፋት ነው። “ቢድዐ ሸይጧን ዘንድ ከወንጀል የከበደ ነው” ይላሉ ታላቁ ሰለፍ ሱፍያኑ ሠውሪ። [ዘሙል ከላም፡ 5/121] አንዳንዱ ግን “በርግጥ መውሊድ የተወገዘ ቢድዐ ነው። ቢሆንም ያን ያክል ከባድ ነገር አይደለም” ይላል። በርግጥም ቢድዐዎች ደረጃቸው አንድ አይደለም። ቢሆንም ልናስተውለው የሚገባን ነገር አለ። ሻጢቢ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ ‘ከቢድዐዎች ትንንሽ የሆነ አለ’ ስንል ይህ ግን ከገደቦች ጋር እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። እነሱም፡-
1. ላይዘወተርበት
2. ወደሱ ላይጣሩበት
3. ህዝብ በሚሰበሰብበት ወይም ደግሞ ሱናዎች በሚፈፀሙበትና የሸሪዐ መታወቂያዎች በሚንፀባረቁበት ላይፈፀም እና
4. ላያቃልልና ላይንቅ ነው። ካቃለለው ይሄ ንቀትን ነው የሚያሳየው። ወንጀልን መናቅ ከራሱ ከወንጀሉ የከበደ ጥፋት ነው።” [አልኢዕቲሷም፡ 2/551-557]
ስለዚህ መውሊድ ላይ የተለመዱት ጥፋቶች ባይኖሩ እንኳን አፈፃፀሙ በራሱ እንደትንሽ ቢድዐ የሚያስቆጥረው አይደለም።