መውሊድን ማን ጀመረው? (በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ?)
~~~~~~~~~~~
መውሊድን የጀመሩት ከ 357 ሂ. በኋላ የነገሱት እራሳቸውን “የነብዩ ﷺ ልጅ የፋጢማ ዘር ነን” እያሉ የሚሞግቱት ሺዐዎች ናቸው፡፡ ለዚህም ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
1. ጀማሉዲን ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.)፡-
በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የመውሊድ በዓልን የሚመለከት መረጃ ሰፍሮ የሚገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ውስጥ ነበር፡፡ የኢብኑል መእሙን አባት የፋጢያ ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር፡፡ በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የኢብኑል መእሙን ስራ ከነጭራሹ አይገኝም፡፡ ይሁን እንጂ በመካከለኛው ዘመን የታሪክ ሰዎች ብዙ ክፍሎቹ እየተጣቀሱ ተላልፈዋል፡፡ በዚህ ረገድ ቀዳሚው ተጠቃሽ ደግሞ ግብፃዊው የታሪክ ፀሐፊ አልመቅሪዚ (845 ሂ.) ነው፡፡ አልመቅሪዚ ይህን ሰውየ በማጣቀስ በ 517 ሂ. የተከናወነውን የመውሊድ አፈፃፀም በሰፊው አትቷል፡፡ [አልኺጦጥ፡ 2/332] በዚያን ዘመን የሚከበሩ ሌሎች በዓላት እንደነበሩ እንዲሁ ይገልፃል፡-
“የ‘ፋጢሚያ’ ኸሊፋዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዙባቸው ዓውደ-አመታት” ካለ በኋላ እንዲህ ይላል፡- “ለፋጢሚያ ኸሊፋዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውደ- አመታት አሏቸው፡፡ እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ ﷺ ልደት ቀን፣ የዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁንና)፣ የፋጢመቱ አዝዘህራእ ዐለይሃስሰላም ልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያለ ይዘረዝራል፡፡ ከውስጣቸው የፋርስ፣ የሺዐ እና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ሁዳዴ ያሉ የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው በመቅሪዚ የተዘረዘሩት፡፡ [አልኺጦጥ፡ 1/436]
መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ፡፡ በሌላ ኪታቡም ላይ “በረቢዐል አወል ላይ (የ‘ፋጢሚዮቹ’ ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላል፡፡ [ኢትቲዓዙል ሑነፋእ፡ 2/48] በተጨማሪም “ረቢዑል አወል ላይ የነብዩን ﷺ ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ባህል ሆኖ ቀጠለ” ይላል፡፡ [ኢትቲዓዙል ሑነፋእ፡ 3/101]
2. ዐብዱስሰላም ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.)፡-
ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው፡፡ ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በሶላሑዲን አልአዩቢ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል፡፡ በፋጢሚያዎች መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ አድደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል፡፡ “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው፡፡ እንዲህ አይነት የአይን ምስክር ባለበት እውነታውን መሸምጠጥ እራስን መሸወድ ነው፡፡ ለናሙና ያክል ንግግሩን ቀንጨብ ላድርግ፡-
ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبيّ صلّى الله عليه وسلّم، ومولد أمير المؤمنين عليّ بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر…
“ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ ﷺ መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ ዐለይሃስሰላም መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን ዐለይሂመስሰላም መውሊድ እና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው፡፡ …” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219]
3. አልቀልቀሸንዲ (821 ሂ.)፡-
ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ሸንጎ ሲያወራ “ሶስተኛው መሰባሰብ በረቢዐል አወል ወር 12 ላይ በነብዩ ﷺ መውሊድ ላይ የሚኖረው መቀመጥ ነው” ካለ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካል፡፡ [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576]
4. አስሱንዱቢ (1,097 ሂ.):-
“የተከበረውን ነብያዊ መውሊድ በመዘከር የማክበሩን ሀሳብ የፈጠሩት ፋጢሚዮች እንደሆኑ በርግጥም ያደረግኩት ምርምር፣ ፍተሻ፣ ጥናትና ክትትል አመላክቶኛል” ይላል፡፡ [ታሪኹል ኢሕቲፋል ቢልመውሊዲ አንነበዊ፡ 62]
5. ሙሐመድ ቡኽየት አልሙጢዒይ፣ የቀድሞው የግብፅ ሙፍቲ (1,354 ሂ.):-
“(እነዚህን መውሊዶች) ካይሮ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠሯቸው የ‘ፋጢሚያ’ ገዢዎች ናቸው፡፡ የመጀመሪያቸውም አልሙዒዝ ሊዲኒላህ ነው፡፡ ከመግሪበል ዐረቢ ተነስቶ በ ሸዋል 361 ሂ. ወደ ግብፅ አመራ፡፡ በረመዷን ካይሮ ገባ፡፡ የመውሊዶችን ሱንና የፈጠሩት እነሱ ናቸው፡፡ የነብዩ መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የክብርት ፋጢመቱ አዝዘህራእ መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን መውሊድ እና ስልጣን ላይ ያለው ኸሊፋ መውሊድ ናቸው፡፡ አልአፍዶል ኢብኑ አሚሩል ጁዩሽ እስከሚሰርዛቸው ድረስ እነዚህ መውሊዶች በተነደፈላቸው መስመር ቀጠሉ፡፡ … ከዚያም አልኣሚር ቢአሕካሚላህ ዘመነ ኺላፋ የተጠቀሱትን መውሊዶች ሰዎች ሊረሷቸው ከተቃረቡ በኋላ ዳግም መለሳቸው፡፡ በኢርቢል ከተማ በተገለፀው መልኩ የተፈጠረው መውሊድ ከዚህ ‘ካይሮ ላይ የ‘ፋጢሚያ’ ኸሊፋዎች ናቸው ቀድመው የጀመሩት’ ከሚለው ጋር አይጣረስም፡፡ ምክንያቱም የ‘ፋጢሚያ’ መንግስት ሰኞ ሙሐረም 10/567 ዓ.ሂ. ላይ አልዓዲድ ቢላህ አቡ ሙሐመድ ዐብዱላህ ኢብኑል ሓፊዝ አልሙስተንሶር ሲሞት አክትሟልና፡፡ ከፋጢሚያዎች በፊት በኢስላማዊ መንግስት ውስጥ መውሊዶች አይታወቁም ነበር፡፡”
ሸይኹ የ “ፋጢሚያዎቹንም” የሙዞፈሩንም መውሊዶች በዝርዝር ካተቱ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “ፋጢሚያዎችና ሙዞፈሩድዲን የነብዩ መውሊድ ላይ ይሰሩት የነበረውን አንተ ካወቅክ ‘የተፈቀደ ነው’ ብሎ ለመወሰን የማይቻል እንደሆነ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ትደርሳለህ፡፡” [አሕሰኑል ከላም፡ 44፣ 66]
6. ኡስታዝ ዐሊ ፊክሪ (1,372 ሂ.)
“የመጀመሪያው (መውሊዶችን) ካይሮ ላይ የጠነሰሳቸው የ‘ፋጢሚያ’ ገዢዎች ናቸው፣ በ4ኛው ክፍለ-ዘመን፡፡ ስድስት መውሊዶችን ነው የፈጠሩት፡፡ የነብዩ መውሊድ፣ የኢማም ዐሊይ መውሊድ፣ የክብርት ፋጢመቱ አዝዘህራህ መውሊድ፣ የሰይዳችን ሑሰይንና ሐሰን ረዲየላሁ ዐንሁም መውሊድ፡፡ አልአፍዶል ኢብኑ አሚሪል ጁዩሽ እነዚህን መውሊዶች ውድቅ አድርጓቸው ቆይተው ከዚያ በዓልሓኪም ቢአምሪላህ ጊዜ በ 524 ሂ. ዳግም ተመለሱ፡፡” [አልሙሓዶራቱል ፊክሪያህ፡ 84]
ስለዚህ መውሊድ ቀድሞ በሺዐዎች እንደተጀመረ የማያወላዳ ማስረጃ እየቀረበ፤ ንጉስ አልሙዞፈር (630 ሂ.) ነው የጀመረው ማለት ማንም ቢያወራው ከመረጃ የተራቆተ ባዶ ወሬ ነው፡፡ ምክንያቱም እሱ ቀድሞ የተጀመረን ነገር ነውና ያስቀጠለው፡፡ ምክንያቱም እሱ “ፋጢሚያዎች” ከወደቁ በኋላ ነውና የተሾመው፡፡
“ፋጢሚዮች” ከኢስማዒሊያ ሺዐ ቅርንጫፎች ውስጥ መሆናቸው ላይ ውዝግብ የለም፡፡ ይሁን እንጂ የነብዩ ﷺ ልጅ “የፋጢማ ዘር ነን” ማለታቸውን ብዙሃኑ የታሪክ ፀሐፊዎች አያምኑትም፡፡ ብቻ ጥቂትም ቢሆኑ “በጊዜው የነበሩ ተቀናቃኝ መንግስታት የነዙት ፕሮፓጋንዳ ነው” ያሉ ስላሉ ይህን ክፍል ትቼዋለሁ፡፡ “የነብዩ ﷺ ዘር መሆናቸው ምን ይ