መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ ቀደም ብየ ገልጬ ነበር። አሁን ደግሞ የጀመሩበትን አላማ ልጠቁም እወዳለሁ።
በግብፅ የአስዩጥ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶክተር ሐሰን ኢብራሂም ሐሰን እና በትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትምህርቶች ገምጋሚ የነበሩት ጦሀ አሕመድ ሸረፍ በጋራ በመሆን “አልሙዒዝ ሊዲኒላህ” በሚል ርእስ ስለ“ፋጢሚያዎቹ” ንጉስ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አንድ መፅሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ “አውደ - አመታትና በዓላት” በሚል ርእስ ስር ያሰፈሩት ሃሳብ “መውሊድ ለምን አላማ ታስቦ ነው የተጀመረው?” ለሚለው ጥያቄ ጥሩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡-
“(ንጉሱ) አልሙዒዝ በሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ቀን፣ በነብዩ ﷺ መውሊድ ቀን፣ በረጀብ መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በሸዕባን መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በረመዷን መጀመሪያ ቀን ከሚያስተዳድራቸው ህዝቦች ጋር ይካፈል ነበር፡፡ ይህን የሚያደርገው
* የሱኒ፞ዮቹን ነፍስ ለማረጋጋት፣
* እንዲሁም በሱኒ፞ዮች መርሆዎችና በሺዐዎች እምነቶች መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ በማሰብ ነው፡፡
* በተጨማሪም ይሄ አልሙኢዝ ሊዲኒላ፞ህ የንግስና ዘመኑን ያሸበረቀባቸውን እነዚህን በዓላት የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ እምነቶችን ለማሰራጨት ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሑሰይንን ዝክር ህያው ለማድረግ የዓሹራእ ቀንን ያከብር የነበረው፡፡ ልክ እንዲሁ የበርካታ አኢማዎችን መውሊድና ስልጣን ላይ ያለውን ገዢ መውሊድ በሚልም (የራሱን ልደት) ያከብር ነበር፡፡
* ልክ በዚህ መልኩ የህዝቦቹን ትኩረት ወደሱ ለመሳብና የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ መርሆዎችን ለማሰራጨት እነዚህን በዓላት እንደ መዳረሻ ይጠቀምባቸው ነበር፡፡” [አልሙዒዝ ሊዲኒላህ፡ 284]
ስለዚህ መውሊድ የተጀመረው ለፖለቲካዊ ትርፍ እና የሺዐን እምነት ለማስፋፋት ሲባል ነው ማለት ነው፡፡ የክርስቲያኖቹ ገና፞፣ ሁዳዴ፣ …፣ የራፊዷዎቹ የዓሹራእ በዓል፣ ገዲር ኹም፣ …፣ የእሳት አምላኪ መጁሳዎቹ ነይሩዝ ይከበሩ ከነበሩት በዓላት ውስጥ ነበሩ፡፡ የህዝብን ትኩረት ለመሳብ፣ ቅሬታ ውስጥ ያሉ ሱኒ፞ዮችን ልብ ለማረጋጋት በሂደትም ወደራሱ የሺዐ እምነት ሰዎችን ለማስገባት በማለም ነው፡፡ ቀስ እያለ በጉልበት ወደ ሺዐ እምነት መጣራት እንደተጀመረ ይታወስ፡፡ ስለዚህ አላማቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡትን የህዝብ ግፊቶች በማርገብ ይከተሉት የነበሩትን የኢስማዒሊያ ሺዐ እምነት ማስፋፋት ነበር ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ዛሬ ሱፍዮች እንደሚያስቡት “የወሃብዮች” ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ከላይ እንዳየነው የታሪክ አጥኚዎች ድምዳሜ ነው፡፡
የመውሊድ ስርኣቱ ለእኩይ አላማ የታለመ ስለነበርም ነው ሶላሑዲን አልአዩቢ “ፋጢሚዮችን” አሸንፎ ግብፅን ሲቆጣጠር አስቁሞት የነበረው፡፡ መቼም እሱንም “ወሃቢ ነው” እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የተጀመረው ኋላ በመምሉካውያን ጊዜ ነው፡፡ የመውሊድ ተግባር ዳግም ሲመለስ ሌሎቹ መውሊዶች የሌላ እምነት መሰረት ያላቸው ወይም ሺዐ-ዘመም ስለነበሩ በሱኒ፞ው አለም ገበያ አላገኙም፡፡
ከ “መውሊድ፤ ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት” መፅሐፍ ተነካክቶ የተወሰደ