አስ-ሱንና


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


አስ- ሱንና
ሱናሕ የኑሕ መርከብ ናት የተሳፈረባት ይድናል ወደ ኻላ የቀረው ይሰምጣል !!
🫵ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የነብያት ሁሉ ጥሪ ናት ☝️

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🎊ታላቅ  ሙሀደራና ቢሻራ ፕሮግራም🎊
              ➖➖➖➖➖

【በዕለተ እሁድ ረጀብ 19/1446ھ】

«ታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች የሚሳተፉበት»

⏰ከምሽቱ  2:40ጀምሮ የሚተላለፍ ይሆናል !

ተጋባዥ ኡስታዞች እና የክብር እንግዶቻችን
~
🎙ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሒዛም -ከየመን
🎙ኡስታዝ አቡ-ሒዛም - ከሰመራ
🎙ኡስታዝ ኸድር አህመድ _ከከሚሴ
🎙ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢድሪስ_ከሀርቡ
🎙ኡስታዝ አቡ አብዲረሂም አብዱረህማን  ሹመት_ከጃሚዓቱል-ኢስላሚያህ - መዲና
---
☞እንድሁም የአህሉ ተዉሂድ መርከዝ አሚሮችና ወንድሞችም ይሳተፋሉ! 

❝በአህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ❞ 💡የሚተላለፍበት አድራሻ↓↓↓↓↓↓
https://t.me/sefinetunuh
https://t.me/sefinetunuh
=


አልሐምዱሊላህ❤

በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት በይፋ ተፈፅሟል።

በኳታር አደራዳሪነት ሲደረግ የነበረው የሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈፀመ።

በዚህም መሰረት በሀማስ እጅ ያሉ እስራኤላውያን የሚለቀቁ ሲሆን በእስራኤል እጅ ያሉ ፍልስጤማዊያንም ይለቀቃሉ። የተኩስ ድምፅ የማይሰማ ሲሆን የእስራኤል ጦር ከጋዛ ለቆ ይወጣል።
በመደመሪያዎቹ ቀናትም አስቸኳይ እርዳታን የያዙ 600 መኪኖች ወደ ጋዛ ይገባሉ።
በጋዛ ላይ የሚደረጉ የጦር በረራዎች የሚቆሙ ሲሆን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል።

ከዚያም ጋዛን እንደገና የመገንባት ስራ በአለምአቀፍ ዘመቻ ይጀመራል።

አልሃምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀል!!!

©


قال بعض العلماء: إنا ‌لم ‌نطلب ‌العلم ‌لنحيط به كله، إذ لا سبيل إلى ذلك، ولكن لنستكثر من الصواب ونستقل من الخطأ.
اللطائف والظرائف (ص47)


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


በደቡባዊ ካሊፎርኒያ፣ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የሰደድ እሳት ለመግታት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተሰማሩ።
በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል የተባለውን ይህንን የሰደድ እሳት ለማጥፋት ወደ 939 የሚሆኑ እስረኞች በካሊፎርኒያ የማረሚያ እና መልሶ ማቋቋም መምሪያ (ሲዲሲአር) በሚመራው የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም ታቅፈው በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፉ ነው ተብሏል።
ባለፈው ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም. በሎስ አንጀለስ ተቀስቅሶ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት እየተሳተፉ ያሉ ታራሚዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ይገኛል።
ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ከ10 ሺህ በላይ ህንጻዎችን ያወደመው እና 37 ሺህ ሄክታር የሚሸፍን መሬት ያቃጠለውን ሰደድ እሳት ለመግታት በሺዎች የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተሰማርተዋል።
በሰደድ እሳቱ ቢያንስ እስካሁን 11 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

©
#እሳት


የመሬት መንቀጥቀጥ ጥንቃቄው 3 ነው። 1) ከወንጀል ተውበት ማድረግ 2) ዱአ ማድረግ 3) በሸሀዳ በውዱእ አዝካር ብሎ መተኛት
👉 ከዛ ውጭ መንግስትም በለው ማን መላሽ የለውም።


መሬት መንቀጥቀጥ መንስዔው ምንድነው?

ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“በነዚህ ቀናት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፤ አላህ ጥራት ይገባውና ባሮቹን ለማስፈራራት እና ለማስጠንቀቅ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከመሬት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም ሰዎች የሚጎዱ እና የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ እና ሰዎችን የሚያስከፉ ክስተቶች ሁሉ ከሺርክ እና ከአመፅ መንስኤዎች የተፈጠሩ ናቸው።”
📚መጅሙዕ ፈታዋ ወመቃላት (9/149)












🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
          ቁ/272

የዕለተ ረቡዕ 1/7/1446 ዓ.ሂ ትምህርት

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

  ዳውንሎድ ለማድረግ ይህን ይጫኑ

🔗https://rb.gy/hwu4b3

▪️1/ የሆነ ስራ ለመስራት ፈልጌ የአጎቴ ልጅ ብር ሊያበድረኝ ነበር የሚኖረው ሳውዝ አፍሪካ ነው እዛ የሚሰሩ ልጆች ሲጋራና ዊግ ይሸጣሉ አብዛሃኞቹ የአጎቴ ልጅ እነዚህን ይሸጣል አይሸጥም አላውቅም የሱን ብር ተቀብዬ መስራት እችላለው?

▪️ 2/ ከዚህ በፊት አከራይቼ ነበረ ተከራዮቹ የቤት ክራዩን ሳይከፍሉ ከጠፉ 3 አመት ይሆናቸዋልና የቤት ክራዩን ብር እነሱ ጥለውት ከሄዱት እቃ ሽጬ መውሰድ እችላለሁኝ?

▪️3/ እኔ ሰለምቴ ነኝ ቤተሰቦች ክርስቲያን ናቸው እህቴም ሰልማ ነበር ቤተሰብ ጋር በሄደችበት ክርስቲያን ልጅ አገባች እናት መልስ ልትጠራቸው ፈልጋ ብር አነሳት እናቴን በብር ባግዛት በሃራም መተባበር ይሆንብኛል?

▪️4/ እኔ ከባለቤቴ ጋር ተጣልቼ ከአሁን በኋላ ካንተ ጋር መኖር አልፈልግም ብዬ ማልኩኝ ከዛም በኋላ ሰዎች አስታረቁን አብረን መኖር ጀመርን ለማሃላው ምን ማድረግ አለብኝ?

▪️5/ ነሲሓ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው እርሶ ይህን ያክል እያስተማሩ በሴቶች ላይ በዚህ ልክ እየለፉ ጥሩ አኽላቅና ስነ–ምግባር  እንዲኖረን በአላህ ፍቃድ እየሰሩ ቢሆንም እኛ ሴቶች ግን በሰው ህይወት ገብተን የሚመለከተንንም የማይመለከተንንም እያወራን እንገኛለን። ስለ ሰው ባል፣ ሚስት፣ልጆች ባጠቃላይ ስለ፣ ብሔር ስለ ሀብት፣ ስለ ሸይኽ፣ ስለ ደርሳዎች የሚቀረን የለም። የቀራን እስከማንመስል ኢልም ላይ ያለን እስከ ማንመስል በጣም የሚያሳፍር ባህሪ ነው የምናንፀባረቀው ነሲሓ ያስፈልገናል ።

▪️6/ ወንድ የእጅ ጌጥ መልበስ ሀራም ነው?

▪️7/ እናቴ የማታ ደርሶችን ለመከታተል ለደህንነቴ ከመስጋት የተነሳ አትፈቅድም እና እሷን እሺ ብዬ ልታዘዝ ወይስ እንቢ ብዬ ወደ ደርስ ልሂድ?

▪️8/ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ልደት እንኳን አደረሰህ ማለት እንዴት ይታያል? ከማለትም አልፎ ቀለል ያለ ስጦታ ሰጥቶ አላህ እድሜህን/ሽን ያርዝመው ማለትስ?

▪️9/ ለወገብ ህመም፣ ውፍረትን ለመቀነስ፣ ለግፊት፣ ለስኳር ፣ለኮልስትሮልእና ለብዙ አይነት በሽታዎች ለመቀነስ ዶክተሮች እስፖርት ያዛሉና ሙዚቃ ሳይኖር ለሴቶች በሴቶች አሰልጣኝ እስፖርት መስራት እንዴት ይታያል? 

▪️10/ ለመድረሳ ግንባታና ለመስጂድ ግንባታ እንዲሁም ለመድረሳ ወጪ የዘካን ገንዘብ መስጠት ይቻላል?

▪️11/ የቅርብ ቤተሰብ ችግርተኛ እያለ የዘካን ገንዘብ ለመድረሳ መስጠት እንዴት ይታያል ?

▪️12/ የዛሬ 3 አመት አካባቢ በህመም ምክኒያት የረመዷን መፆም አልቻልኩም ነበርና በስኣቱ ባለማወቅ ለሚስኪን አብልቼ ብቻ ትቼው ነበር ቀዷእ ማውጣት እንዳለብኝ ያወቅኩኝ አሁን ነው ግን አሁንም በጣም እያመመኝ ስለሆነ መፆም አልችልም ምን ማድረግ ነው ያለብኝ?

▪️13/ ከአባት ቀድማ የሞተች ሴት ልጅ ከአባቷ ንብረት ድርሻ/ውርስ አላት?

ከአባትዋ ቡሃላ የሞተችስ የምትወርስ ከሆነ ድርሻዋ ለልጆችዋ ይደርሳል?

ከደረሳቸውስ በህይወት ካሉ እህቶች እኩል ነው?


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ይደመጥ‼

በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም


መንገደኛ (ሙሳፊር) የሆነ ሰው ኢማም ሆኖ ሲያሰግድ ባገሩ ነዋሪ የሆነ (ሙቂም) ሰው ከተከተለው ኢማሙ አሳጥሮ ቢሰግድ ተከታዩ ሞልቶ መስገድ አለበት። ይሄ የዑለማእ ወጥ ስምምነት (ኢጅማዕ) ያለበት ጉዳይ ነው ይላሉ ኢብኑ ቁዳማህ - ራሒመሁላህ። [አልሙግኒ፡ 2/64]


ኒቃቧንም ትለብሳለች፤ ትምህርቷንም ትማራለች‼

ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች‼

ፍትሕ በመላው ሃገሪቱ በተደጋጋሚ በሒጃብና ኒቃብ ጉዳይ በደል ለሚፈፀምባቸው ሙስሊም ተማሪዎች‼


እናንተዬ… ይሄ ሰው ይህን ያክል ያስፈራል እንደ⁉️
================================
✍ እኔ ፖለቲካ አይመቸኝም። ከዲኔ አንፃር ጥቅሙ ካመዘነ ብቻ ሃሳቦች የማነሳባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ፤ ይኖራሉም።

ዛሬ ስለ ፖለቲካ ላወራ ሳይሆን፤ በርካታ በሺዎች የሚቆጠር ነፍጥ ያነገበ ታጣቂ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ጫካ ገብቶ እየተዋጋ ባለባት ሃገር፤ አንድ ግለሰብ በፌስቡክ ገፁ በዚህ ደረጃ የአንድትን ሃገር ታላላቅ ሚዲያዎችና ታላላቅ ባለስልጣናት ከላይ እስከ ታች በዚህ ደረጃ ማስጨነቁ አግራሞትን አጭሮብኛል።

ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው በዚህ ደረጃ የሆነ ነገር ባለ ቁጥር የሚያስጨንቃቸው?!

የሚገርመው ሌላ የሚተቹበት ቢያጡ፤ በአንድ ወቅት ስለ እስልምና የተናገራትን ነገር ዶክመንተሪ ላይ አቅርበዋታል። በነርሱ ቤት ሙስሊም ያልሆነው ሰው እንዲጠላው ለማድረግ ነው። ንግግሩ ያኔ የድምፃችን ይሰማ ጊዜ ይመስለኛል፤ እስልምና ሲነካ ኦሮሞም እንደተነካ ማሰብ አለበት የሚል ነገር ተናግሮ ነበር መሰል። በሜንጫ ያላትም ነገር ነበረች መሰል። ሁሉንም አቅርበውታል።

ኢሬቻ ላይ ወጥሮ የሚያከብር ሰው ባይሆን፤ በዲኑ የሌለ ጠንካራ፣ ከኢሬቻና መሰል በዓላት የራቀ፣ ጺሙን ያሳደገ፣ ሱሪውን ያሳጠረ… ሰው ቢሆንማ ፎቶውን ብቻ ደጋግመው ቀባብተው ዶክመንተሪውን ማድመቂያ ያደርጉት ነበር። በአጭሩ ሙስሊም ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኛና ዋና ቁልፍ መሪ መሆን ከባድ ይመስላል። ለማጠልሸት የሄዱበትን ርቀት ሳየው፤ ምን ያክል እንቅልፍ የሚነሳቸው ሰው መሆኑን ነው የተረዳሁት።

ለማንኛውም አላህ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን። እርሱንም በዲኑ የበለጠ ጠንካራና ጠቃሚ የበለጠ የሚፈራ ያድርገው።  ለካ ብዙዎቹ ከላይ እስከ ታች የሚጠሉት በዲኑ ነው። ስንትና ስንት ያሳለፈ ሰው ሌላ የሚያስተቸው ነገር አጥተው ነው ዘለው ከእምነቱ ጋር በተያያዘ ነገር የሚተቹት?


በነገራችን ላይ ተቃዋሚ መኖሩ መሪውን አካል ያነቃቃል፣ ለህዝብም ጥቅም ጥሩ ነው። ተቃዋሚ ከሌለ፤ መሪ ከርሱ ውጭ አማራጭ ያለ ስለማይመስለው ህዝብ ላይ ሊተኛ ይችላል፣ ሃገርም በሚፈለገው ደረጃ እድገቷ ላይፋጠን ይችላል። ተቃዋሚ የጎደሉ ነገሮችን ሲያነሳ፣ መሪ ከትችት ከመዳን እነዚያን ክፍተቶች ለመሙላት ወዶ ባይሆንም ተገዶ ይጥራል
©




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት መልእክቶችን ማበረታታት ይገባል። ክፋት የሚናገሩትን ብቻ እያራገብን ሁሉንም ጥግ ማስያዝ አይጠቅመንም። እየታሰበበት።
=
©


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ነብዩ በሌሎች መፃሀፍት

Показано 20 последних публикаций.