🎖🎖 #የአራቱ_መዝሀብ_ባለቤቶች🎖🎖
✍🏼 አሚር ሰይድ
የአራቱ ዝነኞቹ መዝሀቦች ባለቤቶች የት እንደተወለዱ፣ መቼ እንደተወለዱና መቼ እንደሞቱ በቅደም ተከተል እነሆ
➊ - አል-ኢማሙ አቡ ሐኒፋ አን-ኑዕማን ቢን ሣቢት፡- በዒራቅ ውስጥ ኩፋ በምትባል ከተማ በ8ዐኛው ዓመተ ሂጅሪያ የተወለዱና በ150 ዓመተ ሂጅሪያ ሙተዋል
➋ - አል-ኢማሙ ማሊክ ቢን አነስ (የዳሩል ሂጅራ ኢማም)፡- በመዲነቱን ነበዊያ በ93 ዓመተ ሂጅሪያ የተወለዱና በ179 ዓመተ ሂጅሪያ እዚያው ሙተዋል
➌ - አል-ኢማሙ ሙሐመድ ቢን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይ፡- በ150 ዓመተ ሂጅራ በሻም ሀገር ውስጥ በጋዛ ላይ የተወለዱና በ204 ዓመተ ሂጅሪያ በግብፅ ላይ የሞቱ
➍ - አል-ኢማሙ አሕመድ ቢን ሐንበል (የአህለ ሱንና ወል ጀማዓ ኢማም) በ146 ዓመተ ሂጅሪያ በበግዳድ የተወለዱና በ241 ዓመተ ሂጅሪያ እዚያ የሞቱ ናቸዉ
አሏህ ሁሉንም ቀብራቸዉን ብርሀን ያድርግላቸው
🔰🔰🔰 #አራቱ_የመዝሀቦች_ባለቤቶች የአላህ
መልዕክተኛ ﷺ ሱንናን እንዳለ ወስደው በመከተልና አጥብቀው በመያዝ ዙሪያ እንዲህ ብለዋል፡-
☞ ኢማም አቡ ሐኒፋ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- ሐዲሡ ትክክለኛ ከሆነ የኔ መዝሀብ እርሱ ነው፡፡ እንዲህም ብለዋል፦ እኛ ከየት እንደወሰድነው ሳያውቅ ለእንድም ሰው የእኛን ንግግር መውሰድ አይፈቀድለትም፡፡
☞ ኢማም ማሊክ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- እኔ ስህተት የምሰራና ትክክል የምሆን የሰው ልጅ ብቻ ነኝ፤ ስለሆነም አስተያየቴን ተመልከቱ፤ በውጤቱም ከኪታብና በሱንና ጋር በገጠመ ቁጥር ያዙት፤ በኪታብና ከሱንና ጋር ባልገጠመ ቁጥር ደግሞ ተውት።
☞ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ እኔ ካልኩት በተቃራኒ በነቅል (በማጣቀስ) ሰዎች ዘንድ ማንኛውም ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሆነ ዘገባ ትክክለኛነት ያለበት ጉዳይ ሁሉ ካለ፣ እኔ በሕይወት ሳለሁም ሆነ ከሞትኩ በኋላ ከርሱ ተመላሽ ነኝ፡፡
☞ ኢማም አሕመድ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- እኔን በጭፍኑ እትከተለኝ፤ ማሊክንና ሻፊዒይን በጭፍኑ እትከተላቸው፤ ይልቁንስ እነርሱ ሁላቸውም የሀይማኖቱ ኢማሞች ነበሩ፡፡ብለዋል፡፡
⚠️ ዛሬ ግን እኛ ሙስሊሞች ስለመዘሀባቸዉ የሰጡትን አስተያየት ወደ ጎን ትተን በእነሱ ዙሪያ ስንጨቃጨቅ ስንነታረክ ብዙ ዘመናት አለፍን ...መቼ ይሆን ወደ አቅላችን ተመልሰን መዝሀቦቹን ወደ ቁርአን ሀዲስ ወስደን በቁርአን መስመር መከተል የምንጀምረዉ??
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━
4 another channal👇
t.me/Islam_and_Science
💐⭐️💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group