የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የባለአክስዮኖች የምክክር መድረክ ተካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ባለአክስዮኖች ጋር በባንኩ 20ኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተላለፉ ውሳኔዎች ዙሪያ ምክክር አካሄደ።
ዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በፕላኔት ሆቴል በተካሄደ የምክክር ስብሰባ በጉባኤው ላይ የተደረጉ ውይቶች እና ጉባኤው ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰበሳቢ በአቶ አለም አስፋው በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ቦርዱ የምክክር መድረኩን ያዘጋጀው ከባንኩ ባለአክስዮኖች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለአክሰዮኖች በዚሁ አካባቢ የሚገኙ በመሆናቸው በጉባኤው መገኘት ባይችሉም በጉባኤ ላይ የተነሱ ሀሳቦች እና ውሳኔዎችን የማሳወቅ ኃላፊነት ስላለበት እንደሆነ ተገልጿል ።
ባንኩ በ2015/16 የበጀት ዓመት ባከናወነው እንቅስቃሴ ካለፈው በአጅጉ ከፍ ያለ ትርፍ ማስመዝገቡንና ከዚህ ውስጥ 20 በመቶ የትርፍ ድርሻ ለባለአክስዮኖች እንዲከፋፈል በጉባኤው መወሰኑን ተገልጿል ።
በተጨማሪም የባንኩን ተከፈለ ካፒታል ለማሳደግ ሁሉም ባለአክስዮኖች የትርፍ ድርሻቸውን ለአክስዮን ማሳደጊያ እንዲያውሉ በጉባኤው ላይ በተደረሰው ስምምነት መሰረት በትግራይ ክልል የመገኙ ባለአክስዮኖችም የትርፍ ድርሻቸውን ለካፒታል ማሳደጊያ እንዲያውሉ እንዲሁም አዳዲስ ተጨማሪ አክስዮኖች እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል።
የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት በመሳደግ የተወዳዳሪነት አቅም መጎልበት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በውይይቱ ከባለአክስዮኖች የተገኘ አበረታች ምላሽ እና ምክረ ሐሳብ እንዳለ በመውሰድ ማኔጅመንቱ በቀሪው የበጀት ዓመት ባሉት ጊዜአት በዕቅዱ ውስጥ አካቶ እንደሚሰራ አስታውቋል።