የወለጋ ህዝብ የአገዛዙን አረመኔነት ቀድሞ የተረዳ ነው። የወለጋ ኦሮሞ በአብይ አህመድ አሊ እጅግ የተገፋም የተደበደበም ህዝብ ነው። አብይ አህመድ አሊ ከፍተኛ ክህደት ከፈጸመባቸው አካባቢዎች እና ፖለቲከኞች ወለጋዎች በቀዳሚዎቹ ረድፍ ያሉ ናቸው። የወለጋ ኦሮሞ የድሮን ቦንብ የሚዘንብበት ነው። እነ አብይና ሽመልስ ቡድን ይህ መንግስት የኦሮሞ መንግስት ነው የሚሉትን ቀልድ የወለጋ ኦሮሞ በተለይና ሁሉም ኦሮሞ አልተቀበለውም፤ ሊቀበለውም አይችልም። አገዛዙ በወለጋ ያለውን አማራም ሆነ ኦሮሞ ከገደለ በኃላ እርስ በእርስ እንደተገዳደለ አድርጎ የሚያቀርብ የሞት ነጋዴ እንጅ ለማናቸውም ህዝብ የሚወግን እንዳልሆነ ሁሉም ያውቁታል። በመሆኑም አገዛዙ የጋራ ጠላታቸው መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነት ይህ ነው። ስለሆነም በወለጋ የፋኖ አደረጃጀት መመስረቱ ለኦሮሞው የትግል አጋሩ የሚሆንለት ደስታው እንጅ የሚያስደነግጠው አይደለም። የአገዛዙን ጭካኔና ጦረኝነት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትም ይሁን የፋኖን የህዝብ ድጋፍ የምታውቅ ከሆነ የፋኖ ምስረታ የሚፈታው ችግር እንጅ የሚያመጣው ጉዳት እንደማይኖር ማመን ይኖርብሃል። [ የወለጋውን ሰው ኮሎኔል ገመቹ አያናን ቃል ልብ ብለህ ብትሰማው በዚያ ቀጠና ያለው የአማራ የኦሮሞ ህዝብ መስተጋብር ምን ያህል ጥልቅና የማይነጣጠል መሆኑን ትረዳበታለህ]:: ስለዚህ በወለጋ የፋኖ መደራጀት የሚያስፈነድቀው እንጅ የሚያስከፋው ኦሮሞ የለም፤ ከአገዛዙ ቡድን ውጭ። [የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ግንኙነትና አኗኗር እነ አብይ ኦሮማራ ብለው እንዳሾፉት ያለ አይደለም፤ በማይናወጥ መሰረት ላይ የተገነባ ነው]::
ከዋናው ጠላት በቀር ሌሎች ልዩነቶችን ሁሉ በሳይንስም በጥበብም መፍታት የምናካሄደው አብዮት መርህ ነው። በትግሉ ምዕራፍ የሚኖረን ሚና በድህረ-ትግል ሊኖረን የሚገባውን መልክእ ይወስናል። አገዛዙ ውሎ እያደረ ያለው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን እኛ በበቂ ባለመቀናጀታችን ድክመት ምክንያት ነው።
አገዛዙ የማድረግ አቅም ካገኘ ሁሉንም ወንጀሎች ለመፈጸምና የህዝብ ለህዝብ ግጭት ለማስነሳት እንደማይመለስ መረዳትና ይህን እድል እንዳያገኝ በቅንጅት መስራት በዚያው ያለው የአማራና የኦሮሞ ወጣት እና የሁላችንም ስራ ይሆናል።
ይህ የበዛብህ በላቸው አቋም ነው ብዙዎችም ይስማሙበታል።