የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ፌዴሬሽን በፓርላማ በአዋጅ ሊመሰረት ነው
=======================
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2012 ዓም (ክርስቲያን ፖስት)
ጠቅላይ ሚንስቴሩ ሰኔ 13 ቀን፣ 2011 ዓም ቁጥራቸው አራት መቶ ለሚደርሱ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መሪዎች ያቀረቡትን የአንድነት ጥሪ ተከትሎ የተቋቋመው ምክረ ሐሳብ አቅራቢ ግብረ ኃይል ዛሬ የካቲት 21/2012 ዓ.ም በጠራው ስብሰባ ላይ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንዲህ አሉ፦ “የግብረ ኃይሉ ስራ ዛሬ ይጠናቀቅ ቢባል እንኳን መቼም የማልለያቸው ወንድሞቼን አግኝቻለሁ፤ ወዳጅነታችን ይቀጥላል።”
በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት ማለዳ 2:30 ላይ በሰዓቱ የጀመረው ስብሰባ በሰዓቱ ግን ሊጠናቀቅ አልቻለም። ከመርሃ ግብሩ ውጪ በመለኮት አቀነባባሪነት የተጀመረው ንስሃ እና አንዱ ለአንዱ ያሳየው የይቅርታ ልብ ያዘነበው ፍቅር “ውጡ ውጡ አይልም እዛው ቅሩ እንጂ ...” የሚለውን ዝማሬ የሚያስታውስ ነበር።
#አባቶች_ተላቀሱ፣ ወጣት ሐዋርያቱ እርስ በእርስ በይቅርታ አነቡ፣ አንዳንዶች አባቶች እግር ላይ ወደቁ። አባቶች ሳይቀሩ በአንድ ወገን እርስ በእርስ በሌላ ወገን ልጆቻቸውን እየፈለጉ ሲተቃቀፉ ሲላቀሱ አረፈዱ።
#ፍቅር ስብዕና ያለው አካል እሱም መለኮት የሆነው እግዚአብሔር ነው። እርሶ ተገኝቶ ማን በክብሩ ይቆማል? ለቅሶ እና ሳግ ያለ ዕቅድ ያዘነበው ቤት ተው ቢባሉ አልሰማ ባሉ መሪዎች የደስታ ድባብ ተሞላ። ሁሉ በእንኳን ደስ አለህ እየተላቀሰ ተቃቀፈ። አባቶች ከደስታ ብዛት በልጆቻቸው ቢለመኑ እንኳን ማቆም ተሳናቸው። በየ ጥጋ ጥጉ ወዲህ በደስታ ወዲያ በንስሃ እና በይቅርታ ሁሉ አነባ።
#ለምን ?
-በሕግ ፊት እኩል መቆም የሚያስችል፣
-እርስ በእርስ የሚያቀራርብ፣
-አስተምህሮ እና ልምዶችን የሚገራ፣
-በሀገሪቱ ውስጥ ለሚከሰቱ ጉዳዮች በጋራ ድምጽ የሚያሰሙበት፣
-አደጋዎች ሲከሰቱ በአንድነት ድጋፍ፣ ለማድረግ የሚያስችል ወዘተ. . . ተቋም
ለመመስረት ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ነበር።
“ፎቶ ኮፒ እና ዶክመንት ይዘን በየቢሮው የምንሮጥበትን ጉዳይ ወደ መቃብር
የሚከት ነው” ያሉት የሕግ አማካሪው አቶ ኒቆዲሞስ ናቸው።
“ቀደም ባሉት ዓመታት ጥያቄ የነበረው የመኖር ነበር...” ያሉት የመካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት #ቄስ_ዮናስ ተቋሙ ከምክር ቤት ይልቅ #ፌዴሬሽን ቢሆን የተሻለ መሆኑን አንስተዋል። በመግቢያ ጸሎታቸውም #በአንድ ተስፋ እና #በአንድ ጌታ መተሳሰራችንን አስታውሰዋል።
“አባቶች እራቁታቸውን ለተገረፉለት፤ ከተማ አይገባችሁም ተብለው ዳር ዳር ለሄዱለት ወንጌል እኛ ዛሬ አምሮብን፣ ተሸልመን እና ደምቀን እንዴት እናስኪደው ብሎ ለመነጋገር ዕድል የሰጠንን እግዚያብሔር ይመስገን” በማለት የቃለ #ህይወቱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢያሱ የመግቢያ ጸሎት ባቀረቡ ጊዜ ከስብሰባ መንፈስ ወደ ምስጋና ጉባኤው ተቀየረ። በስብሰባ ወቅትም በቅርቡ ከ120
በላይ የቃለ ህይወት አጥቢያዎች ሲቃጠሉ በጋራ ድምጽ የሚያሰማ አለማስታወሳቸውን ገልጸው ተቋሙን እውን ለማድረግ የቤት ስራቸውን ፈጥነው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ጉባኤተኛውን ሁሉ ቀልብ ሲገዙ የነበሩት የመድረኩ አጋፋሪ ቄስ ደረጄ ከአንደበታቸው ማር ይዘንብ ነበር።
ግብረ ኀይሉ ከ25 ጊዜያት በላይ ለመደበኛ ስብሰባ መቀመጡ፤ ከተለያዩ ቤተ እምነት መሪዎችና ኅብረቶች ጋር ምክክር ማድረጉ እና የምሥረታ ረቂቅ ዐዋጁን ለማዘጋጀት የሕግ ባለሙያዎችን ማሳተፉ በተናጋሪዎች ሁሉ አስመስግኖታል።
አስቀድመው የቤት ስራቸውን የሰሩት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መሪዎች መጋቢ ጻድቁ እና መጋቢ ዘሪሁን ጥቅሙን እና ጥንቃቄ ቢደረግበት ያሉትን ጉዳይ አንስተዋል። በተለይ መጋቢ ዘሪሁን ሌሎች ፈጥነው እንደነሱ እንዲሰሩ እና ዛሬም መልካም ፈቃዳቸው ከሆነ በሙሉ ድምጽ መግባባታቸውን እንዲገልጹ በጠየቁ ጊዜ ረ ረ ረ ጅ ሙ ሙ ሙ ጭብጨባ ተከተለ።
#ከዛማ_ፍቅር_ነገሰ !
ለማንኛውም፦
-ተቋሙ ከሁለት ሳምንታት በኋላ በይፋ የመሥራች ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።
-ተቋሙ ሲመሰረት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትን አሁን በሕግ ከሚታወቁበት ከተራ የማኅበርነት ምዝገባ በዐዋጅ ወደ ሚደነገግ የሃይማኖት ተቋምነት የሚያሸጋግራቸው ይሆናል።
-የተቋሙ ጊዜያዊ ስያሜ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ፌዴሬሽን ነው
-የተቋሙ መሪዎችን ለመምረጥ አብያተ ክርስቲያናት ለተከታታይ ቀናት በአንድነት የጾም ጸሎት ዐዋጅ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
-ምሥረታው በሚሊኒየም አዳራሽ አማኞች በተገኙበት ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።
#ማስታወሻ
በ1952ቱ የፍትሓ ብሔር ሕግ በዐዋጅ የተቋቋመችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን በዐዋጅ ለማቋቋም የሚንስትሮች ምክር ቤት መወሰኑና ውሳኔው ለተወካዮች ምክር ቤት መላኩ ይታወሳል።
ፎቶ፦ ከማህደር
©ዐቢይ ታደለ /ኪያ/
@Christianpost1
@Meleket_Tube