መዝሙር 22 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ መከራ እየተቃረበ ነውና፣ የሚረዳኝም የለምና፣ ከእኔ አትራቅ።
¹² ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።
¹³ እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣ አፋቸውን ከፈቱብኝ።
¹⁴ እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።
¹⁵ ጒልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤ ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።
¹⁶ ውሾች ከበቡኝ፤ የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፎአል፤ እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።
¹⁷ ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።
¹⁸ ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
¹⁹ አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ አጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
²⁰ ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።
²¹ ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።