ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ለመላክ አቅዳለች ተባለ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያሏትን ውስን የስጋ ምርት ተቀባይ ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር እና ከዘርፋ ያላትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች ሲል የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።
በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በአብዛኛዉ የስጋ ምርቷን ጥቂተ በሆኑ የገልፍ ሀገራት ላይ ለሽያጭ ታቀርባለች።
ይህም ሊሆን የቻለዉ የእነዚህን ሀገራት የምርት ጥራትና ደህንነት መስፈርትን ብቻ በማሟላቷ እንደሆነ ተናግረዉ ችግሩን ለመፍታት ሌሎች ሰፋፊ የገበያ መዳረሻዎችን ለማፈላለግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት ይህን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳህሉ በተለይም እንደ ቻይና ወደሚገኙ የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ምርቱን ለመላክ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ይህ እውን እንዲሆን ከዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ጎን ለጎን ለዉጪ ገበያ የሚቀርቡት የስጋ ምርቶች ጥራታቸዉንና ደህንነታቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።የቻይና ገበያ ሁሉንም የኢትዮጵያን የስጋ ምርት መቀበል የሚችል በመሆኑ ከዘርፋ የተሻለ ገቢን ለማግኘት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
በተለይም የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ለመላክ መታቀዱ የተገለፀ ሲሆን በዘርፋ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ይህን እድል ለመጠቀም የመቀቀያ ማሽኖችንና ሌሎች ግብአቶችን በማሟላት ላይ ይገኛሉ።
በቅድስት ደጀኔ