በነቀምት ከተማ በሁለት ተማሪዎች ላይ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ እና በቪዲዮ ቀርፆ ለማህበራዊ ሚድያ ያሰራጩ ሁለት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በነቀምት ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ውስጥ በሁለት ተማሪዎች ላይ የመድፈር ጥቃት ሲፈፀም በቪዲዮ ቀርፀው ለማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩ ሁለት ተከሳሾች እና ደፋሪው ግለሰብ በፍጥነት ተከታትሎ ለህግ በማቅረብ ውሳኔ ማሰጠቱን የነቀምት ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
የነቀምት ከተማ አስተዳር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ጥቄሳ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የተባለው ግለሰብ በነቀምት ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ የ17 ዓመቷን ታዳጊ ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች እያለ መንገድ ላይ ጠብቆ ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር አስገድዶ ወደ ጫካ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ተገልጿል። አንደኛው ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የ17 ዓመቷን ልጅ በዱላ እየደበደበ የለበሰችውን ልብስ ሲያወልቅ እና የመድፈር ጥቃት ሲፈፅምባት ሁለተኛ ተከሳሽ ጫላ ዑመር እና ሶስተኛ ተከሳሽ ፍራኦል ታሪኩ የተባሉት ግለሰቦች በእጅ ስልካቸው ቪዲዮ በመቅረፅ ከባህል እና ወግ ውጪ አስነዋሪ ተግባሩን ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።
በተጨማሪም አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ ከሁለቱ ግብረአበሮቹ ጋር በመቀናጀት የ15 አመቷን ታዳጊ ጠልፈው አንደኛ ተከሳሽ የተከራየበት በመውሰድ አንደኛ ተከሳሽ የመድፈር ጥቃት ሲፈፅምበት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሳሽ የመድፈር ጥቃቱን በእጅ ስልካቸው በመቅረፅ ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የ15 ዓመቷን ታዳጊ ከነቀምት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ውስጥ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጠልፎ በመውሰድ ከግብረአበሮቹ ጋር በማስገባት በዱላ በመደብደብ ልብሷን እንድታወልቅ በማድረግ የመድፈር ጥቃት ሲፈፀምባት ሁለቱ ግብረአበሮቹ በእጅ ስልካቸው ቪዲዮ በመቅረፅ አስነዋሪ ድርጊቱን ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን የነቀምት ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎቹን ያስቆጣ እንደነበረ ዋና ኢኒስፔክተር ፍሮምሳ ገልፀዋል።
ፖሊስም ይህንን ከማህብረተሰቡ ባህል እና ወግ ውጪ የሆነን ድርጊት በመከታተል በጥቂት ቀናት ውስጥ የድርጊቱ ፈፃሚዎች እና ተባባሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል የዚህ ድርጊት ዋነኛ ፈፃሚ እና ተባባሪዎች ላይ ምርመራ መዝገቡን በስፋት በማጣራት በሆስፒታል በተገኘ የምርመራ ውጤት እና በተጎጂዎች ቃል እንዲሁም ተከሳሾች የሰጡት የእምነት ቃል በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለአቃቤ ህግ የላከ መሆኑን ተገልፆል። አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ አንቀፅ 620 ንዕስ አንቀፅ 2 እና ንዑስ አንቀፅ 4 በመጥቀስ በጭካኔ በማሰቃየት የመድፈር ጥቃት በመፈፀም እጅግ አስነዋሪ እና የማህበረሰቡን መልካም ስነምግባር እና ፀባይ በተፃረረ መልኩ የተፈፀመ ድርጊት ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸው ክስ የተመሠረተባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
በአቃቤ ህግ የቀረበውን ክስ ሲከታተል የነበረው የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ 12 ዓመት እስራት ሲቀጣ ሁለተኛ ተከሳሽ ጫላ ዑመር ድርጊቱን በቪዲዮ ቀርፆ በማሰራጨት እና ተጎጂዋን በመጥለፍ ተባባሪ በመሆኑ በ 4 ዓመት እስራት ሲቀጣ ሶስተኛ ተከሳሽ በድርጊቱ ያለው ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ በአንድ ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ዋና ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ጢቄሳ ጨምረው ለብስራት ገልፀዋል።
በሰመኃር አለባቸዉ