በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 32 #ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ፣ 43 የሚሆኑ ደግሞ ምሽት ላይ ይገባሉ ተብሏል
#በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን መንግስት አስታወቀ።
#ሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማይናማር በእገታ ሥር ቆይተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩ 133 ኢትዮጵያ መካከል 32ቱ ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ሲል ገልጿል፤ ሌሎች 43 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁሟል።
ቀሪዎቹ በታይላንድ ማቆያ የሚገኙ 58 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ኤምባሲው ጥረት እያደረገ ይገኛል ብሏል።
በተጨማሪም #ጃፓን በሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃያሳያል።
[ @MadoNews ]