#ግን_ለምን⁉️
ማንቸስተር ዩናይትድ ለምን ይሄንን መለያ መጠቀም አቆመ?
የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት የሆነው የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ዩናይት ዳግም መልሶ ያልተጠቀመው አንድ መለያ አለው።
በ1996 ኤፕሪል ወር ዩናይትድ በዋንጫ ፉክክር በሚያደርገው ግስጋሴ ወደ ሳውዝሀምፕተን አምርቶ ባደረገው ጨዋታ ለውድድር ዓመቱ የተዘጋጀውን በምስሉ ላይ የምትመለከቱንን አማራጭ መለያ በማድረግ ወደ ሜዳ ይገባል። በጨዋታው ከፍተኛ ብልጫ የተወሰደበት ቡድኑ 3ለ0 እየተመራ እረፍት ይወጣል። በእረፍት ሠዓት የቡድኑ አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ግራጫ ቀለም ያለው መለያ የቡድኑን ተጫዋቾች እንደረበሸና በፀሀይ እርስ በርስ በቀላሉ እንዳይተያዩ እንዳደረገ በማመን ተጫዋቾች መለያውን እንዲቀይሩ ያዛሉ።
ተጫዋቾቹም ከእረፍት መልስ ነጭ እና ሰማያዊ ቀለም ያለውን ሦስተኛ መለያ ቀይረው ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን ምንም እንኳን ጨዋታውን ባያሸንፉም በሁለተኛው አጋማሽ እጅግ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገዋል። ከዛ ጨዋታ በኋላም ይህ ግራጫ ቀለም ያለው መለያን ማንቸስተር ዩናይትድ ተጠቅሞ አያውቅም።
© gofere sports wear
@Manchester_unitedfansz