አምናለሁ ግን አላምንም
ልጁ የታመመበት አባት ነው:: ጌታን "ቢቻልህስ ልጄን ፈውስልኝ" አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ይህን ጊዜ ሰውዬው "ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፥ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፡ አለ" ማር. ፱፥ ፳፬
የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው" ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም? ያምናል እንዳንል "አለማመኔን" ይላል ፤ አያምንም እንዳንል "አምናለሁ" ይላል:: የቸገረ ነገር ነው? ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: አላዋቂው እኔ ግን አምናለሁ አለማመኔን እርዳው የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::
እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው? ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ። አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ:: ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና ክደዋለሁ:: ኑሮዬ "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት መደብ ነው:: (ቲቶ ፩፥፲፮)
አቋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው:: ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሳ ዐረገ ብዬ አምናለሁ::
በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ አላውቀውም:: የምተርከው ክርስቶስ እንጂ የሚተረክ ክርስትና የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::
መች በዚህ ያበቃል:: እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው:: ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢአት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ:: እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው:: ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው እላለሁ::
እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ? ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም:: ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው:: እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው:: አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው:: እማራለሁ አለመማሬን እርዳው:: ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የኤፌሶን ወንዝ
@mekra_abaw