❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ክፍል 30
ምን እያወራና እየቀባጠረ እንደሆነ ግራ ገባኝ።
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ስለምን እያወራ እንደሆነ ጠየኩት።
ተረጋግቼ እንድቀመጥና አጉል ማስመሰሉ እንደማይጠቅመኝ ነገረኝ።
የዛኔ ነገሮች ከአቅሜ በላይ ሆኑብኝ ለመረዳት ተቸገርኩ በትክክል እዛጋ የነበረው ችግር ምን እንደሆነ አልገባ አለኝ።
ተረጋግቼ ቁጭ አልኩና ይቅርታ አለቃ እሺ አሁን እየተፈጠረ ያለውንና ለማለት የፈለከውን ቀስ ብለህ አስረዳኝ ምክንያቱም እኔ ለምን እዚህ እንደመጣሁ እራሱ አላቅም አንተ እንደ ጠያቂ ነገሮችን ግልፅ አድርግልኝ አልኩት።
ጥሩ አውርቼ እስክጨርስ እንዳትተነፍስ ምን እንደተፈጠረ በቅደም ተከተል ላስረዳህ ላንተ ምታቀውን ነገር መድገም ቢሆንም ግን የስራ ግዴታዬ ስለሆነ ልንገርህ አለኝ።
እያዳመጥኩ እንደሆነ ገለፅኩለት።
ትናት አንተ ወደክለብ ለመዝናናት አምርተህ ነበር አደል??
እና ክለብ ውስጥ በምትሰራ አንዲት ሴተኛ አዳሪ የተነሳ አንተና አንድ ሰው ግጭት ውስጥ ገባችሁ።
መጣላት ጀመራችሁ ሀይለኛ ፀብ ውስጥ ስትገቡ ወደ ውጭ ወጥታችሁ በግል መደባደብ ጀመራችሁ ።
ሁለታችሁም ተጎድታችሁ እራሳችሁን ስታችሁ ወደቃችሁ እሱ በዛው ሞተ አንተ ደሞ ሀኪም ቤት ሄደህ ነቃህ አለኝ።
ዝም ብዬ አየሁት የሟችን ፎቶ ማየት እችላለሁ??? ብዬ ጠየኩት
ስልኩን አውጥቶ አሳየኝ ሟቹ እዮብ ነው።
አንዳንዴ ነገሮች ተፈጥረው ግን በትክክል ያንን አምነን መቀበል ሚያቅተን ሰአት አለ።
በሰአቱ እየተሰማኝ የነበረው ስሜት ምን እንደሆነ በትክክል ባላውቅም ከፊት ለፊቴ ተቀምጦ የነበረውን ሰው ግን በጥርሴ በጣጥሼ ብጥለው ሁላ እርካታ እንደማይሰማኝ ጠንቅቄ አቃለሁ።
መጮህ ጀመርኩ እዮብ ጓደኛዬኮ ነው እሱ ላይ ጨክኜ እጄን ማንሳት እራሱ አልችልም ንገረኝ ምንድነው የተፈጠረው ንገረኝ ሞተ ማለት ምን ማለት ነው።
ብዬ በሀይል መጮህ ጀመርኩ እየጮኩ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ እየደከመኝና መናገር እያቃተኝ መጣ ።
ከዛ ቡሀላ በድጋሜ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ እራሴን ሀኪም ቤት አገኘሁት
🔻ክፍል 31 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33