💛💞መልካም ልቦች™💞💛


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩
👉 @Z_afro ያነጋግሩ::

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


ሽልማታቸውን ገቢ አድርገናል ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን!


አንድ ልጁ ታስሮበት ብቻዉን የቀረ ገበሬ እስር ቤት ላለ ልጁ እንዲህ ሲል ፃፈ፦

“ዉድ ልጄ

ይኸዉልህ አንተ በመታሰርህ ምክንያት በዚህ አመት እርሻ ቦታዉ ላይ ድንች ሳልዘራ ጊዜዉ ሊያልፍብኝ ነዉ፤ እኔ እንደሆንኩ ከእንግዲህ ደክሜያለሁ፤ምነዉ በኖርክልኝ ኖሮ" አፍቃሪ አባትህ፡፡

ከሳምንት በኋላ ገበሬዉ መልስ መጣለት፤ ምላሹም “አባባ፤ የድንቹን መደብ እንዳትቆፍር፤ ሰወቹን → የቀበርኳቸዉ እዚያ ነዉ:: ያንተዉ ልጅህ" ይላል፡፡

በሚቀጥለዉ ንጋት ላይ የፖሊስ መዓት መጥቶ የድንቹ ማሳ ላይፈሰሰ፤ የተቀበሩትን አስክሬኖች ለመፈለግ ሲቆፍሩ ቢዉሉም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም ። ስለዚህ ገበሬዉን ይቀርታ ጠይቀዉ ሄዱ፡፡ ወዲያዉ ልጁ ለአባቱ እንዲህ የሚል ሌላ ደብዳቤ ፃፈ

አባቴ፤ አሁን ድንችህን መዝራት ትችላህ፤ ካለሁበት ችግር አንፃር ላደርግልህ የምችለዉ ነገር ቢኖር ይሄ ብቻ ነዉ

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

3.2k 0 11 6 113

1.ስራ የለኝም እና ምን ሠርቼ የተሻለ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

2. ስራ አለኝ ግን በማገኘው ደሞዝ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልኩም እና
እንዴት ተጨማሪ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

3.ተማሪ ነኝ ግን ከትምህርቴ ጎን ለጎን ቢዝነስ በመስራት ለነገዬ የሚሆን ገቢ እንዴት ማግኘት ችላለው? ከሆነ

ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።

ስራውን መጀመር ሆነም ስለስራው ማንኛውንም መረጃ ለማግኘት  በውስጥ ያናግሩኝ 📥  

🧑‍💻 @YaredTT25


💝የናንተን ባላውቅም እኔ እወዳቹዋለሁላይክ ማድረጋችሁን አትርሱ!

4.1k 0 0 31 358

❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  37


እራሴን ቀጠቀጥኩ እራሴ ለራሴው መሳሳት አልቻልኩም ከጉዳቴ በላይ ጥፋቴ ጎልቶ ታየኝ።
አለማስተዋሌ ከኔ አልፎ ሌላ ሰው ላይ ያደረሰውን ጠባሳ ሳይ በራሴ አፈርኩኝ።

ለኔ ሞት በሚገባኝ ሰአት ነው እስር ቤት የገባሁት።
ለካ መኖሬም ለሆነ ሰው አስፈላጊ ኖሯል።

እራሴን በጠላሁት ሰአት ሁሉም ሰው የጠላኝና ፊቱን ያዞረብኝ መስሎኝ ነበር ግን አንድ ሰው ድንገት ወደ ህይወታችን መጥቶ ብቻውን ለኛ አለም መሆን ይችላል።
ነገሮች ከረፈዱ ቡሀላ ሲገቡን እንዴት ልብን እንደሚያደማ እንዴት እንደሚያም እኔ ምስክር ነኝ።


እጄ ከዛ በላይ መሰንዘር ሲያቅተው ከሻወር ቤት ወጥቼ ሶፋው ላይ ቁጭ አልኩ ጣልያንጋ ደወልኩ።

መፅሀፉን አንድ ባንድ ለሱ መተረክ ጀመርኩ ።
ነገርኩት..... እኔና እሷ ከተለያየንበት ምሽት አንስቼ ለሱ መተረክ ጀመርኩ መፅሀፉ ላይ ልእልት ለመጀመሪያ ጊዜ እኔን ያየችበትን ቀን አንስቶ ብትተርከውም ከዛ በፊት ያለውን ለሱ መንገር አልፈለኩም ባልነበርኩበት ሰአት የተፈጠረውን ብቻ መተረክ ጀመርኩ ...

ያኔ እኔና ልእልት የተለያየንባት ምሽት ላይ ልእልት ፀንሳ ነበር።
እኔን በመፈለግ ትምህርቷን አቆመች ጠዋት የወጠች ማታ እግሯ እስኪዝል ድረስ ፈልጋኝ ወደ ቤት ትገባለች ለመመረቅ ወራት ሲቀራት የለፋችበት ትምህርት ውሀ በላው።

እኔን በመፈለግ ውስጥ እራሷን አጥታው ሳታስበዎ አረገዘች ማርገዟን ያወቀችው ቆይታ ነበር።
ቤተሰቦቿ የሷን ምርቃት ቀን ጓጉተው ሲጠብቁ ትምህርቷን እንዳቆመች ሰሙ ቀሱ ብቻ አላቆመም ማርገዟም ታወቀ እንዴት አንገትሽን ደፍተሽ በተከበርንበት ሰፈር ታዋርጅናለሽ ብለው ከቤት አባረሯት ለተወሰነ ቀን እኛ ቤት አረፈች ግን ወንድሟ ካንዴም ሁለቴ እሷን ለመግደል ሲሞክር በግድ ተረፈች ቀስ በቀስ ወሬው የሰፈር ሰዎች ጆሮ ደረሰ የሰፈር ሰው ድሮም ዝምተኛ መስላ ዲቃላዋን ተሸከመች ለመሆኑ አባቱንስ ታውቀው ይሆን እያሉ ማውራት ሲጀመሩ የልእልት ቤተሰቦች በሀፍረት ቤታቸውን ሸጠው ልእልት ወደማታቀው ቦታ ሄዱ ።

ቤተሰቧን ዘመዶቿን ጎረቤቶቿን እኔንም ጨምሮ ባንዴ ያጣችው ልእልት እራሷን ለማጥፋት ብዙ ጊዜ ተነስታ ሆዷ ውስጥ ያለው ፅንስ እያሳዘናት ትታዋለች ።
በስተመጨረሻም እራሷን ከዛ ሰፈር ማሸሽ ስላለባት የኛን ቤት አከራይታ ለራሷ ትንሽዬ ቤት ተከራይታ እራሷን ለማስተዳደር ብትሞክርም ህይወት ከብቸኝነትና ከእርግዝናጋ በጣም ከባድ ሆነባት በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየሆነች  ምግብ ሳትበላ ሶስትና አራት ቀናቶች ያልፉ እንደነበርም ተናግራለች።
በዛ ላይ እርጉዝ ሆና እንኳን የመደፈር ሙከራ ደርሶባት ለትንሽ ነው የተረፈችው ስለ አጋጣሚው የፃፈችውን ሳነብ ይሰቀጥጠኛል።

እኔ እንዲሁ ቀለል ቀለል አደረኩት እንጂ እሷ ያየችው ስቃይና መከራ እንዲሁ ተወርቶ ሚያልቅ አደለም ።

በምቾትና በድሎት የቤተሰቦቿ አይን ማረፊያ ሆና ተንከባክበው ተቆጣጥረው የውጭውን ህይወት እንዳታቀው ጓደኛ እንኳኖ እንዳይኖራት አድርገው ካሳደጓት ቤተሰቦቿ ቤት በድንገት ወጥታ ብቻዋን አይዞሽ ባይ ሳይኖራት ድንገት በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ እራሷን ስታገኘው ምን እንደሚሰማት ማሰብ ልብን ያደማል።

ደሞኮ በዛ ሁላ ችግር ውስጥ ሆና እንኳን ከምንም በላይ መቋቋም የከበዳት ነገር የኔ ናፍቆትና ልቧ ላይ የሚሰማት የፍቅር ህመም እንደሆነም ፅፋለች......
ጣልያን ቀጥታ እና እንዴት እዚህ ልትደርስ ቻለች ታዲያ ብሎ ጠየቀኝ

ልእልት የተከራየችበት ሰፈር በጣም የድሆች ሰፈር ሚባል ነበር።

ባጋጣሚ እነሱ ሰፈር ላይ የሚቀረፅ ፊልም ነበር ።
እሷ በዛን ሰአት ምጧ መጥቶ ጮኸች ጩኸቷን የሰሙት ፊልም ሰሪዎችና የሰፈሩ ሰው ተሰበሰበ ፊልም ሚሰሩት ሰዎች በራሳቸው መኪና ወደ ሀኪም ቤት አደረሷት ።
ወለደች ለልጇ ምታለብሰው ልብስ አልነበራትም ሚጠይቃት አብሯት ያለ እሷ እስክትወልድ ጓጉቶ ሚጠብቅ ልጇን አቅፎ  ወደ ቤት ሚወስድላት ሰው አልነበራትም።

ባጋጣሚ ቢኒያም የተባለው የፊልሙ ባለቤት ስለሷ መጠየቅ ይጀምራል ።
የሰፈሩ ሰው ታሪኳን ምንም እንደማያቁና ብቸኛ እንደሆነች ነገሩት።

ያንን ሲሰማ የሷን ጉዳይ እሱ እንደሚጨርሰውና ፊልም ቀረፃ ለተወሰነ ጊዜ እንደሚቆይ ተናግሮ  ሌሎቹን አሰናበታቸው።

በወለደችበት ሰአት ከሀኪም ቤት አስወጥቶ ልጇን ታቅፎ ቤቷ ወሰዳት ውስጡን ሲያየው ባዶ ሲሆንበት አራስ ልጅ እዚህ ቤት ውስጥ መቆየት የለባትም ብሎ ቤቱ ወስዶ ሰራተኛ ቀጥሮ እንድትታረስ አደረጋት ።

ከዛ ቡሀላ ቀስ በቀስ ታሪኳን እየነገረችው ስትመጣ በጣም ስላሳዘነችው በራሱ እየከፈለ አስተማራት እሷንም ልጇንም እንደልጆቹ አድርጎ አሳደጋቸው ብልህ ማጋነን አይሆንብኝም በቃ ምናለፋህ ልእልት ትመኘው የነበረውን ህይወት በሙሉ ነው የሰጣት ።
አስተምሮ አስመርቆ ለልጇ ሞግዚት ቀጥሮ በተማረችበት እየሰራች ጎን ለጎን ስነ ፅሁፍን አስተማራት የራሷን ታሪክ መፃፍ ጀመረች በዛን መሀል እሱ የጋብቻ ጥያቄ አቅርቦላት ወደ ፍቅር ህይወት ገቡ ተጋቡ ተጋቡ ሰማኸኝ ጣልያን አልኩት።

እየሰማሁህ ነው ግን አንድ ነገር እንድታደርግልኝ እፈልጋለሁ መፅሀፏን በነገው እለት ለኔ እንድትልክልኝ መፅሀፉን ማንበብ እፈልጋለሁ አንተ የነገርከኝ ከላይ ከላይ ነው ውስጡ ስንት ነገር አለው አለኝ።
እሺ በቃ ይሄ ነው የመጨረሻ ንግግርህ አልኩት።
ከመቅፅበት ጠባቂዎች መጡ ብሎ ስልኩን ዘጋው ።

🔻ክፍል  38 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

4.1k 0 13 13 329

ትወዱኛላችሁ😂👇

3.3k 0 0 28 125

አንድ ክፍል ልጨምርላችሁ እፈልጋለሁ ግን እየተፃፈ ስለሆነ ነገ ላይለቀቅ ይችላል ከተስማማን ልጨምርላችሁ ነገ ካልተለቀቀ ግን ተጠያቂ አታረጉኝም ከተስማማችሁ #ኮሜንት አድርጉልኝ!

3.4k 0 0 37 131

ስላቆየንባችሁ ይቅርታ ቤተሰቦቼ በ አንዳንድ የግል ጉዳዮች ነው የዘገየነው እናስተካክላለን✌️


❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  36

ምናልባት እሷን ማገኝበት ትክክለኛ ሰአት መች እንደሆነ ማጣራቱ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል በሩጋ ሄጄ እሷን አስጠራትና ስትመጣ በስለት በሳስቻት እኔ ከዛ አካባቢ እሰወራለሁ አለቀ።

እቅዴን ስጨርስ ቀጥታ ወደ ተግባር ለመግባት ትንሽ ከራሴጋ ግብ ግብ ፈጠርኩ ግን አንዱ ልቤ ከሴጣን የባሰ ጭካኔን ተለማምዶታል መሰለኝ እንድወስን ገፋፋኝ።

ተወሰነ.....

አረፋፍጄ  ከእንቅልፌ ተነስቼ ልብሴን ለባበስኩ ስራ እንደሚሄድ ሰው ቁርሴን በላሁ ስለቴን ከተትኩኝና ጉዞ ወደ ልእልትጋ ጀመርኩ።
ደረስኩኝ ።

ሰፈሩን ቃኘት ቃኘት አደረኩት ጭር ያለ ነው።
ሰአቴን ተመለከትኩ አምስት ሰአት ሆኗል ።

ከዛ በላይ ሰአት ማባከኑ አስፈላጊ መስሎ ስላልታየኝ በድፍረት ሄጄ በሩን አንኳኳሁ ደጋግሜ ኳ ኳ ኳ .... ተከፈተ አንዲት ልጅ መጥታ ከፈተችልኝ ሰራተኛቸው ናት።
አቤት አለችኝ

ይቅርታ ልእልት ትኖራለች አልኳት።

ልእልት የቤት ስሟ መስሎኝ ሌላም ሰው ያቀዋል እንዴ እሯ አዎ አለች አለችኝ።
በቃ ጥሪልኝ አልኳት።

በሩን እላዬ ላይ ጠርቅማ ዘግታው ገባች።
ቢያንስ ለአምስት ደቂቃ ያህል ቆምኩኝ ማንም ሰው አልመጣም።
እኔ ስለቴን ከኋላ አውጥቼ በእጄ እንደያስኩት ኪሴ ውስጥ ከትቼ እየጠበኳት ነበር።
በስተመጨረሻም በሩ ተ ከ ፈ ተ.....

ልእልት በቀኝ በኩል ትንሽ ልጅ ታቅፋ በግራ በኩል ደግሞ መፅሀፍ ይዛ በሩ ተከፈተ ቀጥታ ቋ የሚል ድምፅ ስሰማ ዝግጁ ሆኜ ቆሜ በሩ ተከፍቶ ልክ ሳያት ሰውነቴ ድርቅ አለ አይኔ የታቀፈቻት ልጅ ላይ አረፈ።

ህፃኗ ልክ ስታየኝ እማ ማነው እኔ ፊልሙ እያመለጠኝኮ ነው ለምንድነው ይዘሽኝ የወጣሽው አለቻት አፏ ከማር ይጣፍጣል አውርታ ባልጨረሰች የሚያስብል ለዛ ነው ያለው።
እናቴን በህፃን ልጅ ተመስላ እያየኋት መሰለኝ ምናቸውም አይለይም ፀጉሯ ልክ እንደናቴ ሉጫ ነው።
አፍንጫዋ ስር ትንሽዬ ጥቁር ነጥብ አለችባት እናቴም ነበረባት ቅንድቧ ግጥም ያለ ነገር የእናቴም ልዩ ምልክቷ ቅንድቧ ግጥም ማለቱና አፍንጭዋ ስር ያለችው ጥቁሯ ነገር ነበረች።

ልክ እንደናቴ ቸኮሌት ከለር ያላት ድንቡሽብሽ ናት አላቅም የሰው ልጅ በህይወቱ በዚህ ልክ መመሳሰል እንደሚችል  ያን ቀን ነው ያወኩት አይኔን ከህፃኗ መንቀል አቅቶኝ እንዳፈጠጥኩ እንባዬ ወረደ እናቴን ያየኋት ያገኘኋት ያህል እሷን ማቀፍ መንካት ፈልኩ ዝም ብዬ በደመ ነፍስ እጄን ዘረጋሁ ልእልት ኩስትር እያለች እየጠበኩህ ነበር ለማንኛውም እንካ ይሄንን አንብብ ብላ መፅሀፉን እጄ ላይ አስቀምጣው በሩን ፊቴ ላይ ወረወረችው
ደጋሜ የማንኳኳት ሞራሉ አልነበረኝም ።

ፊቴን አዙሬ መሄድም አልቻልኩም እናቴን ድጋሜ አግቼ ትቻት የሄድኩ ያህል ተሰማኝ ከበሩ ትንሽ ጠጋ ብዬ ቆምኩኝ ለካ አንዳንዴ ለመቆምም ጉልበት ያስፈልጋል መሬቱ እራሱ እንደከዳኝ ነበር የተሰማኝ እንዳበደ ሰው ድንገት ፊቴን አዙሬ ሄድኩ መፅሀፉን ብቻ ጥብቅ አድርጌ ይዤ ተራመድኩ ቀጥታ ወደ ጣልያን ቤት አመራሁ ገብቼ ቁጭ አልኩ መፅሀፉን ለማንበብ እየተንቀዠቀዥኩ አገላብጬ አየሁት ፀሀፊዋ ልእልት ናት።
ሙሉ ለሙሉ እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መፅሀፍ ነው።

የመፅሀፉ እርእስ የፍቅር ክፋቱ  ይሰኛል።

መግቢያው ላይ መፅሀፉ የልእልት እውነተኛ ታሪኳ ምንም ሳይጨመርበት ሳይቀነስበት ከልጅነቷ ጀምሮ ያሳለፈችውን የህይወት ፈተና የሚያትት እንደሆነ አነበብኩ።

መፅሀፉን ለማንበብ ይበልጥ እየቋመጥኩ የመጀመሪያውን ገልፅ ገለፅኩት ከዛ ቡሀላ ፈጣሪ በሚያቀው ለደቂቃ ከተቀመጥኩበት ሳልንቀሳቀስ ካጎነበስኩበት ቀና ሳልል መፅሀፉን አንብቤ ጨረስኩት ።
የመጨረሻዋን ስንኝ አንብቤ ቀና ስል ጭንቅላቴ ለሁለት ሲከፈል ታወቀኝ የሞት ሞቴን ተነስቼ ሽንት ቤት ገባሁና መስታወት ፊት ቆምኩኝ አይኔ ደም መስሏል ከግማሽ ቡሀላ ሙሉ በሙሉ እያለቀስኩ ስላነበብኩት ነበር አይኔ የቀላው።

ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ህይወቴ ውስጥ ድንገት የሚፈጠሩት ነገሮች ለመቀበል በጣም ስለሚከብዱ  ቶሎ ለመቀበል እራሱ እየተቸገርኩ ነው ሁሌም ቢሆን ህልም እየመሰለኝ እስክነቃ መጠበቁ የህይወቴ አንድ አካል ሳይሆን አይቀርም።

እንደለመድኩት መጮህ መቆጣት አልቻልኩም።
ዝም አልኩ የመፈጠሬ ትርጉም እስኪጠፋብኝ ድረስ ነበር ግራ የገባኝ።

ለሆነ ደቀቂዎች ማሰብ አልቻልኩም ከልቤ ዝም አስባለኝ።

ድንገት ብንን እንዳለ ሰው ተነስቼ ሽንት ቤት ገባሁ የሱሪዬን ቀበቶ አውልቄ ይዤው ነበር ሻወሩን ከፍቼ ቆምኩና እራሴን እስኪበቃኝ በቀበቶው ቀጠቀጥኩት ደም እስኪተፋ እጄ እስኩዝል ሲያንስህ ነው ሲያንስህ ነው እያልኩ......


🔻ክፍል  37 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

4.1k 0 14 5 201

ተጨምሯን ራሱ ላይ


እናንተ አጥሯል ለማለት እንጂ ላይክ ለማድረግ አትሆኑም በጣም ያሳዝናል

4.7k 0 0 34 537

❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  35

በተቻለኝ መጠን ወደሷ ሚያቀርቡኝን ፍንጮች ማፈላለግ ጀመርኩ።

ያለኝ አማራጭ ልእልት ስለፃፈችው መፅሀፍ በደንብ አጣርቼ በመፅሀፏ በኩል እሷን ማግኘት ነው።
እዛው አዳማ ሁለቱን ቀን አሳለፍኩ ፐውስጤ ዝም ብሎ የመንቀዥቀዥ ነገር ቢያበዛም ሰውነቴ ግን የምር ስለዛ ነገር መታዘዝ አልፈለገም።

ጨጓራዬ ላይ የሚሰማኝ ስሜት እሳት እራሱ መች ያቃጥላል ብዬ እስካስብ ድረስ ነበር ህመሙ።

አስታውሳለሁ ማክሰኞ ቀን ከጠዋቱ 2:30 ሲል ምን ከተቀመጥኩበት እንዳስነሳኝ ሳላውቅ እንደ እብድ ብድግ ብዬ ከቤት ወጣሁ ።

በሩን እራሱ አልቆለፍኩትም ዝም ብዬ ቀጠሮው እረፍዶበት እንደቸኮለ ሰው ፈጠን ፈጠን እያልኩ መራመድ ጀመርኩ።

የት ለመሄድ እንደዛ እንደምቻኮል ልቤም ጭንቅላቴም ምንም አያቁም።

ቆም ብዬ ሳስተውል በጣም ብዙ ሰዎች ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ እና እየሄዱ ውር ውር ይላሉ።

አንዲት እናት ነጭ በነጭ ለብሰው ምርኩዛቸውን ይዘው ሲራመዱ አየሁና ቀልቤን ስበውት ወደነሱ ጠጋ ብዬ እኔን መደገፍ እንደሚችሉ ነገርኳቸው።
በዛች ቅፅበት እኔ እናቴ በህይወት ብትኖርልኝ ኖሮኮ እንደዚህ ነበር ይዣት ቤተክርስቲያን የምሄደው ብዬ እያሰብኩ ነበር።

ሴትዮዋ በነፃነት ተደግፈውኝ አብረን መራመድ ጀመርን ።
ልክ ግማሽ መንገድ ላይ ስንደርስ ቆም አሉ አዩኝና ልጄ ፈጣሪ ይባርክህ።

ልጅ ኖሮኝ ቤተክርስቲያን ለመሳም ስሄድ ከጎኔ ደገፍ አድርጎ እናቴ እያለ እያጫወተኝ ደጀ ሰላም ደርሶ መመለስ የልጅነቴም የወጣትነቴም ህልሜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ምን የመሰለ ጠንበለሉን ልጄን ሰው ገደለብኝ ።
እኔ ለማየት የምሳሳለትን ልጄን እነሱ በጩቤ ወጋግተው ወንፊት አደረጉብኝ እኔ ግን ምንም አላልኳቸውም እጄን ወደሰማይ ዘርግቼ ለፈጣሪ አሳልፌ ሰጠኋቸው።
ይኸው ዛሬ ሙሉ ወጪዬን እየሸፈኑ ይጦሩኛል አሉኝ።
ዝም አልኳቸው።
ልጄ ይቅርታ ማድረግ ማለት እራስህን ነፃ ማውጣት ነው የሰው ልጅ ስለታሰረ አደለም ሚማረው ይቅር ስትለው እራሱ ህሊናው አሳስሮ ያስቀምጠዋል ።
ልጄ ይቅር በል ሰዎች ካደረጉብህ ይልቅ ያደረጉልህን አትዘንጋ አሉኝ።
በሰአቱ ፈጣሪ በሰው ተመስሎ እንዳወራኝ ያህል ተሰማኝ ለምን እንደዛ እያንቀዠቀዠ ከቤት አስወጥቶ እዚች ሴትዮ ላይ እንደጣለኝ ለራሴም ግራ ገብቶኝ ሚያወሩትን ወሬ ተመስጬ ማዳመጥ ከመጀመሬ በሩጋ ደረስን ።
እሳቸው ዘንጋቸውን ለኔ አሲዘውኝ ተንበርክከው ተሳለሙ ፀለዩ እኔ ግን በሩጋ ቆም መሳለም እራሱ ውርደት መስሎ ታየኝ ቀና ብዬ ቤተክርስቲያኑን ለማየትም አፈርኩና ፊቴን አዙሬ ቆምኩ.....

ሴትዮዋ ከተንበረከኩበት ብድግ ብለው ዘንጋቸውን እየተቀበሉኝ አትገባም ገብተን እንቀመጥ እንጂ አሉኝ።
እርሶ ተደርጎሎት ነው እኔ ምን ፍለጋ ልግባ ብያቸው ከበሩ ተመለስኩ።

እንዲሁ እየተንቀዠቀዥኩ ወደ አስፋልቱ መራመድ ጀመርኩ ።
አስፋልቱጋ ስደርስ ልሻገር ወይስ ልቁም ግራ ገብቶኝ ቆምኩኝ አይኔ በዛ ቅፅበት ጭንቅላት ጭውው የሚያደርግ ነገር ላይ አረፈ።

በዛኛው አስፋልት ልእልት ነጠላዋን ለብሳ አብሯት ከነበረው አንዱ ሰውዬጋ እየተራመደች አየኋት።

እዛው በቆምኩበት ልቤ እየመታ ለመተንፈስ ሲቸግረኝ እራሴን ተመለከትኩት።

ከመቅፅበት ተሻገርኩኝ እሷ መሆኗን ማመን ስላቃተኝ ከኋላ ከኋላቸው መከተል ጀመርኩ በዛ ሰአት ምን እንደምወስን አላቅም ባዶ እጄን ባዶ ኪሴን ነው የወጣሁት ሄጄ የማውራት ፍላጎቱም ሞራሉሞ የለኝም ።
ዝም ብዬ እየተከተልኩ አረማመዷን ተመለከትኩት አልተቀየረም ያው ነው።

የሆነ ሰአት ላይ ቄጤማ ለመግዛት ፊቷን አዞረች እራሷ ናት ቁጥብ ፈገግታዋ አልተቀየረም  አሁንም እረጋ እንዳለች ነው።
አብሯት ያለው ሰውዬ አይን አይኗን ያያታል ፈገግ ስትል ፈገግ ይላል።

እኔ መዳረሻቸውን ለማየት ጉዞዬን ከነሱ ኋላ አድርጌ እስከመጨረሻው ተከተልኳቸው ወደ አንድ ትልቅ ጥቁር በርጋ ሲደርሱ አንኳኩ እኔ ተደብቄ ቆሜ እያየኋቸው ወደ ውስጥ ገብተው በሩ ተዘጋ።
ሳቄ መጣ ቀና ብዬ ተመለከትኩና ገና በርህጋ ደርሼ ብመለስ ጠላቴን እጄ ላይ ጣልክልኝ በቁም ነገር ፀልዬ ቢሆንማ የእዮብንም ገዳዮች በሬ ላይ አምጥተህ ትጥልልኝ ነበር አልኩና ተመልሼ ወደቤት ሄድኩ መንገዱ እንዳይጠፋብኝ እያንዳንዱን ነገር ምልክት እያደረኩ ነበር የወጣሁት።
ቤት ገብቼ ቁጭ ከማለቴ በምን ተአምር እዚህ ቦታ ልእልት እንደተገኘች ማሰቡ ከጭንቅላቴ በላይ ሆኖ ዝም አስባለኝ



ቀጣይ ልእልትጋ ትጥቄን አሟልቼ ለመሄድና የሷን ነገር በቀላሉ ጨርሼ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ወሰንኩ በዛውም ነገሮች ለኔ ጥሩ ነው ሚሆኑት ከዚህ ከተማ ከወጣሁ ማን ያገኘኛል አድራሻዬን አጥፍቼ ቀጣዩን ስራ አጣድፈዋለሁ ብዬ ወሰንኩ


🔻ክፍል  36 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

4.7k 0 14 12 510

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

          #አትጥቀሰኝ

ሳይሰነዝር 'ሚጥል
ሳይገል የሚረታ፣
አንዳች ጉልበት አለው
ያይንህ ስልምልምታ።

እንኳንስ ጨክነህ
አርገብግበህብኝ፣
ድሮም እኔ ልጅት
ፍርሃት አለብኝ፣
እኒያ ውብ ዓይኖችህ
ወደኔ ካመሩ፣
ይመስሉኛል ውስጤን
የሚመረምሩ፣
ያስጎነብሱኛል እንደ
ጨረር ግለት፣
አንተን ለመጋፈጥ
ያሳጡኛል ጉልበት።

ታዲያ ለምንድን ነው....
እንደምንም ችዬ
ሆኜ እንደጠንካራ፣
ወዳንተው ለማዬት
በድንገት ሳመራ፣
ተዘጋጂ ሳትል
ወይ ሳታሳውቀኝ፣
በአይኖችህ ጠቅሰህ
ቀልቤን የምትሰርቀኝ?

አስበኸው ይሆን
ወይስ ሳታስበው፣
የእኔን ሁለመና
ወዳንተ ምትስበው?

ደጋግሞ እጅ መስጠት
ባይኖችህ ብለምድም፣
በአንተ አይነት ጩልሌ
መሸነፍ አልፈቅድም፣
አካሌ እንደባዳ ልቀቂኝ እያለ
ሁሌ ከሚወቅሰኝ፣
ልለምንህ በቃ በምትወደው ነገር
ተወኝ አትጥቀሰኝ።


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን


❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  34


መልሼ ደወልኩለት አያነሳም።

ሌሊቱን ሙሉ ቤቱን ስቃኝ አደርኩ እያንዳንዷ እቃ ፅዱና ውድ ናት።
ጠርሙስ ነገር ሳገኝ እያነሳሁ መሬት ላይ እከሰክሰዋለሁ ኖርማል እቃ ሲሆን ደሞ አልፈዋለሁ።
ውስጤ ያለው ነገር እንዴት እንደሚወጣልኝ ግራ ሲገባኝ ከጠርሙሱ ስባሪ አንዱን አንስቼ እጄን ቆረጥኩትና ደሜን አፍስሼ መሬት ላይ ማንጠባጠብ ጀመርኩ።

አላቅም ምን እንደተፈጠረ ግን ምንም እርካታ ሊሰጠኝ አልቻለም ውስጤ ማላቀው ስሜት ይተናነቀኛል ወይ ጮኬ አይወጣልኝ እኔጃ ግን አንቆ ይዞ እያሰቃየኝ ነበር።

እንደምንም ነጋልኝና ጣልያን ደውሎ ማውራት ጀመርን እሱ ሚያቃቸው ሰዎች ስላሉ ልጆቹን ማፈላለጉን እሱ እንደሚጨርሰው እስከዛ እኔ ውጭ ላይ የሚሰሩ ጉዳዮችን እንድጨራርስለት ነገረኝ ተስማማሁ።
በር ተንኳኩቶ ቁርስ መጣልኝ ጣልያን እንደላከልኝ ነገሩኝ እጁ ሰፊ እንደሆነ ይበልጥ  አረጋገጥኩ።

ቁርሴን በላልቼ ሶፋ ላይ ቁጭ ብዬ tv ከፈትኩ ዘፈን ስሰማ ጭንቅላቴ እየተረበሸ ሲያስቸግረኝ ዝም ብዬ መቀያየር ጀመርኩ።
አጋጣሚ ግን ቅይር ሳደርግ አይኔንም ጆሮዬንም ያዝ ሚያደርግ ነገር አየሁ።
ልእልትን በቴሌቪዥን መስኮት ተመለከትኳት ልክ እኔ ክፍት ሳደርገው በመጨረሻም ማለት ምፈልገው ተስፋ አትቁረጡ ከዛሬ መከራው የነገው ድላችን እጅግ ጣፋጭ ነው በርቱ ሁላችሁም መፅሀፌን ተጋበዙልኝ።
በተጨማሪም ማመስገን ምፈልገው አካል አለ ውዱ ባለቤቴን ማመስገን እፈልጋለሁ አለም ፊቷን ባዞረችብኝና ነገሮች ያበቁ በመሰለኝ ሰአት እጄን ይዞ ያቀናኝ እሱ ነው እና ኑርልኝ እወድሀለሁ ልጄም እወድሻለሁ አመሰግናለሁ አለች።

አይኔ ነው ወይስ ተሳስቼ ነው ግራ ገባኝ ጋዜጠኛዋ ስሟን ጠርታ እንግዳዋ ስለሆነች ስታመሰግናት እሷ መሆኗን አረጋገጥኩ ።
ከተቀመጥኩበት ማን እንዳነሳኝ አላቅም ተስፈንጥሬ ተነሳሁ .......ንግግሯ ደጋግሞ በጆሮዬ ተመላለሰ ውዱ ባለቤቴ እና ልጄ በቃ ይሄ ንግግር እየደጋገመ እየመጣ ሰላም ነሳኝ

ወጥቼ ሲጋራ ገዛሁና አጨስኩ ምንም መቀዝቀዝ አልቻልኩም ።
እየቀናሁ ይሁን ወይ ደሞ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላቅም ሳያት ለምን ልቤ በዛ ልክ እንደመታም አልገባኝም።
ተናግራ ስትጨርስ ፈገግ ስትል  አብሪያት ለምን ፈገግ እንዳልኩ እራሱ ፈጣሪ ነው ሚያቀው

በሰአቱ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ልቤን ጭንቅላቴን እንዴት ላረጋጋው የመታፈን ስሜት ተሰማኝ።

ቀጥታ ጉዙ ወደ አዲስ አበባ አደረኩኝ።
የድሮ ሰፈራችን ሄድኩኝ ማስታወስ ወደማልፈልገው ህይወት ተመለስኩ ለምን እዛ እንደሄድኩ አላውቅም ግን ሰፈር ደርሼ የኛን ግቢ በር አንኳኳሁ ሚመልስልኝ ሳጣ ደጋግሜ አንኳኳሁ ትንሽ ቆይቶ በሩ ተከፈተ ወጣት እርጉዝ  ናት ሰላምታ አቀረበችልኝ እኔም በክብር መለስኩላት።
ልእልትን ፈልጌ ነበር አልኳት ማናት ልእልት አለችኝ የዚህ ቤት ባለቤት አልኳት እኛኮ ነን ባለቤቶቹ አለችኝ።

ውስጤን ለማረጋጋት እየሞከርኩ አይ ከእናንተ በፊት የነበረችውን ፈልጌ ነበር አልኳት ።
እሷ ምንም እንደማታቅና ቤቱን እነሱ ገዝተውት እየኖሩ እንደሆነ ነገረችኝ።
ከማበዴ በፊት ልረጋጋ ብዬ እራሴን አረጋግቼ አመስግኛት የእነ ልእልትን ቤት አንኳኳሁ የነሱንም ቤት ሌላ ሰው ከፈተውና ከዚህ በፊት የነበሩት ሰዎች ሸጠው እንደወጡና የት እንዳሉ እንደማያውቁ ነገሩኝ።

ሳቄ ይሁን እንባዬ አላውቅም ግን እኩል መጡ ።
የውሸት ፈገግታ ፈገግ አልኩና  ፊቴን አዙሬ ሄድኩኝ።
ከአምስት አመታት ቡሀላ የእናቴን መቃብር ለማየት ሄድኩ።
በሰአቱ ያለሁበት ሁኔታ ለኔም ስላልገባኝ እናቴ የሰጠችኝንም ብቸኛ ማስታወሻ ሌላ ሰው ወስዶት ማየቴ ስላመመኝ ሄድኩና ፊት ለፊቷ በርከክ ብዬ አየኋት ምን እንደማወራት ጨነቀኝ ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ ገባኝ ።
ማውራት ሲያቅተኝ እናቴ እንዳትፈርጅብኝ ቀጣይዋ ሟች ልእልት ናት ብዬ ከመቃብሯጋ ተነስቼ ሄድኩ



🔻ክፍል  35 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

5.4k 0 16 30 306

❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  33

ሰውነቴ በቶሎ ማለት በሚቻል መልኩ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገባ።
ብዙ አመት ሰውነቱን በስፖርት እንደገነባ ሰው ሆንኩኝ።

ሰዎች ከንግግሬ በፊት ሰውነቴን አይተው ይፈሩኛል ብል ውሸት አይሆንብኝም።

እስር ቤት ውስጥ ብዙ ሰዎች በራስ መተማመን ያለው ጠንካራ ማንንም ማይሰማ ማንንም የማይፈራ አድርገው ያስቡኛል እኔ ግን ውስጤ ባዶ ስለሆነ ነው ደፋር የሆንኩት ምኖርለት ምሳሳለት አለሁልህ የምለው አለሁልህ የሚለኝ ሰው ስለሌ ሞት ለኔ ብርቄ አደለም እሱ ደሞ ድፍረትን ወለደልኝ።

ብቻ አምስት አመታትን በእስር ቤት ውስጥ አሳለፍኩ ።
እስር ቤት ላንዳንዱ የፅሞና ጊዜ ይሆንና እራሳቸውን እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል።
አንዳንዶቹንም ደሞ ከበፊት የበለጠ ሴጣንና ጨካኝ ሰው እንዲሆኑ ያደርጋል አብዛኛው ግን ጭንቀቱን ለመርሳት እራሱን ሱስ እና ፀብ ውስጥ የሚከት ነው።

እኔም አምስት አመት ከመቼው እንደሞላኝ እንኳን ሳላውቅ ማክሰኛ ቀን አራት አመት ከስድስት ወር ከአስራ አራት ቀን ታስሬ የመፈቻ ጊዜዬ እንደደረሰና ነፃ እንደሆንኩ ተነገረኝ።
በመጀመሪያ የዛሬ ተፈቺዎች ተብሎ ስሜ ሲጠራ ተሳስተው እንደሆነ ስለገባኝ ዝም ብዬ ተኛሁ አብረውኝ የነበሩት በደስታ ሲዘሉ እንዲረጋጉና በስተት እንደሆነ እንዲያስቡ አድርጌ አፋቸውን ዘግተው ቁጭ አሉ።
በድጋሜ ጠባቂዎቹ መተው ለመውጣት እንድዘጋጅ ሲነግሩኝ ግን አላመንኩም ደጋግሜ እርግጠኛ መሆናቸውን ጠየኳቸው አዎ አሉኝ።

የለበስኩትን ልብስ ለብሼ ለመውጣት ተዘጋጀሁ።
ውስጥ ያሉትን ተሰናበትኳቸው ስወጣ ጣሊያን ነገሮች እስኪስተካከሉ ለአንዳንድ ነገር ይሁንህ ብሎ ብር ሰጠኝ እሱን ተቀብዬ ወጣሁ።

የመጀመሪያ ከግቢው እንደወጣሁ ወደ አስፋልት ስቀርብ የመኪና ድምፅ ስሰማ እራሱ ስቅጥጥ እያለ እየጨነቀኝ ነበር።
ሰው ሳይ መደብደብ ያምረኛል ቢሆንም እቅዴን ማሳካት ዋናው ታርጌቴ እንደሆነ ስለገባኝ አርፌ መንገድ ጀመርኩ ብዙም አልተጓዝኩም አንድ ልጅ መጣና ስልክ ሰቶኝ ሄደ።

በዛ ሰአት ብቸኛ ሚያስፈልገኝ ነገር ስልክ እንደሆነ አቃለሁ ከማነው ብዬ መጠየቁ እራሱ ጅልነት መስሎ ተሰማኝና ዝም ብዬ ተቀበልኩ።
ወዲያው ጣሊያንጋ ደወልኩና ነገርኩት።
እሱም አሪፍ አጋጣሚ እንደሆነና እሱ ቤት ሄጄም ማረፍ እንደምችል ነገረኝ።

ጉዞ ወደ አዲስ አበባ አደረኩ።

እንደደረስኩ የመጀመሪያው ስራዬ እዮብ ወደሞተበት ቤት ማምራት ነበር ።
ሄድኩኝ ሰዎች ድንገት አይተው እንዳይለዩኝ ስናፕ ሹራብ ለብሼ ፊቴን በግማሽ ሸፈንኩት።

ደረስኩ ቤት ከክለብነት ኖርማል እንደ ግሮሰሪ ነገር ሆኗል።
አላመንኩም ተጠግቼ ሰዎችን ለመጠየቅ ሞከርኩ ሁሉም አዎ ክለብ ነበር በቅርቡ ነው እንደዚህ የተቀየረው አሉኝ።

ንዴቴ ወደር አልነበረውም በቃ ለዚህ ነው ይሄን ያህል አመት የለፋሁት ላላገኛቸው ላልበቀላቸው ነው ከራሴጋ ክርክር ጀመርኩ።
ደውዬ ለጣልያን ነገርኩት።
ቀጥታ ወደ አዳማ ሂድና እኔ ቤት ግባ ከዛ ማታ እኔና አንተ እናወራለን እነሱን ማግኘት ለኔ ቀላል ነው መርማሪ ፖሊስ እራሱኮ በኔ ልክ አይመረምርም አለኝ...


🔻ክፍል  34 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

6k 0 26 19 235

1 ክፍል ይጨመር❤

4.9k 0 1 25 130

❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  32

ብቻ  የእስር ቤትን ህይወት ከጀመርኩ ቡሀላ ያ ዝምተኛው ባህራን ጠፋ ።
ሱስም እንደጉድ መጠቀም ጀመርኩ ጎን ለጎን ደሞ የፍልስፍና መፅሀፎችን እያነበብኩ ሰዎች ላይ ያለኝን ንቀት እየጨመርኩ መጣሁ።
እስር ቤት ውስጥ ጓደኛ የለኝም።
ውጭ ላይ ምኖርለት ምናፍቀው ሰው የለኝም ።
በስተት የሴት ስም ሲጠራ ከሰማሁ የማስበው ሰል ልእልት ነው ግን አትናፍቀኝም እራሴን ከስሜቴ እያሸሸሁ ይሁን የምር ልቤ ደንድኖ አላውቅም ግን ምን እያሳለፈች እንደሆነ ህይወት እየፈተነቻት ይሁን እየካሰቻት ማወቅ እፈልግና ድጋሜ እተወዋለሁ።

ብዙ ጊዜ በህልሜ አያታለሁ ።
እሷን በህልሜ ያየኋት ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ የሆነ ሰው ካልደበደብኩ ውስጤ ያለው ስሜት አይወጣልኝም።
በጣም ብዙ ጊዜ ጨለማ ክፍል ውስጥ ተቆልፎብኛል ግን ደሞ ጨለማ ለኔ ሚያስፈራኝ ነገር አደለም እንደውም በተቃራኒው ጨለማ ሲሆን ደስ ይለኛል ምንም የማየው ነገር ሳጣ እየሞትኩ እንደሆነ አስብና ሰላም ይሰማኛል።

አንዳንዴ ደሞ መሞቴን እጠላዋለሁ ተራ ሰው ሆኖ መሞት ያስፈራኛል ልክ እንደጓደኛዬ እዮብ ቀባሪ በሌለበት አልቃሽ በታጣበት መሞት ያስፈራኛል።


ብቻ ህይወት ወደናንተ ፈተና ይዛ ስትመጣ በላይ በላይ እየደራረበች ነው በዛው ልክ ደሞ ስኬትንም ስትሸልመን በላይ በላይ ነው።
ለኔ ፈተናን ይዛ መጣች እዛው በዛው እየተደራረበ  ፈተናው ሌላ ፈተናን እየወለደ መልካም የነበረው ህይወቴ ምስቅልቅሉ ወጣ።
እራሴን ያገኘሁበትንና ያለሁበትን ቦታ አስብና እበድ እበድ ይለኛል።
ምናልባት ህይወቴ መስመር ባይስት ኖሮ እንደተለመደው ስራዬን ሰርቼ ወደቤቴ ተመልሼ የእናቴን እግር አጥቤ ከሷጋ እየተሳሳኩ የተከበረውና አሪፍ ህይወቴን እየኖርኩ ይሆን ነበር ነበር ነበር ።

ብቻ እስር ቤት ውስጥ ያሳለፍኩትን ህይወት አሁን ላይ ማውራቱ ለማንም አይጠቅምም ትርፉ የደረቀን ቁስል እንዳዲስ መነካካት ነው።

ጭካኔን ,ለሰው ልጅ አለመራራትን, ህይወትን በትክክል መጥላት እንዴት እንደሆነ ,እራስን አለመውደድ, ወዘተ.... ብዙ ነገሮችን ያሳየኝ ብቸኛ ቦታ እስር ቤት ነው።
ከዛ ለመውጣት ምጓጓበት ትልቁ ነገር የእዮብን ገዳዮች መበቀል መፈለጌ ብቻ ነው።
ፊታቸው ለብዙ ጊዜያት ጭንቅላቴ ላይ ተቀርፆ ነው የቆየው።
ቁጭ ባልኩበት ቅፅበት ሀሳቤ ላይ ሚመጣው ነገር አጊቼ አናታቸውን ሳፈርሰው ነው
እስር ቤት ውስጥ ሆኜ አሪፍ ገንዘብ እሰራ ነበር።
እንዴት ካላችሁኝ አንዳንዴ እርስ በራሳቸው ይጣሉና አንዱን ማጥቃት ሲፈልጉ የሆነ መላ ደጎም አድርገውኝ እኔ እቀጠቅጥላቸዋለሁ።
በዛ ገንዘብ አገኛለሁ ከዛም በተጨማሪ ውስጥ ላይ ነገሮችን በጣም እየተላመድኩ ስሄድ እስር ቤት ውስጥ ዋና ካፖ ጣሊያን ከሚባለው  ልጅጋ ተግባባን እሱ ለአስራ ሶስት አመት እስር ቤት ውስጥ አሳልፏል።

እዛው እስር ቤት ሆኖ በስልክ ብቻ እያስጨረሰ  አዳማ ላይ ምን የመሰለ ቪላ ቤት ሰርቷል።
ቤት ኪራይ ሳይከፍል የሆድ ወጪ ሳይኖርበት ዘና ብሎ እየኖረ ካፒታሉን ሚያሰፋ ሰው ቢኖር ጣልያን ነው።

የመጀመሪያ ቀን ስንተዋወቅ በሰው አስጠርቶኝ ልብህን አደንቅልሀለሁ ወንድ ልጅ ጉልበት ባይኖረው እንኳን ልብ ካለው ይበቃል ወንድ ወንድ ሲሆን ደስ ይላል አለኝ።

እስር ቤት ውስጥ ሚሰሩ ስራዎችን በሙሉ አሳየኝ ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንዳለብኝ ከሱጋ ከሆንኩ ቡሀላ ደሞ በደንብ  ተማርኩ።
ውስጥ ላይ ስልክ ሰጠኝ።
እስረኞች ወደ ውጭ/",ቤተሰቦቻቸውጋ መደወል መደውል ሲፈልጉ እያስከፈልኩ አስደውላቸዋለሁ።

በተጨማሪም ሰውነቴን ለመገንባት ስፖርት ጀመርኩ።
የኔ ከሌሎቹ ሚለየው ሌሊት 7,8,9,10,11 ሰአት በቃ ሰአት አልመርጥም ተነስቼ እየሰራሁ ሊሆን ይችላል
ሌሊትና ቀኑ ለኔ ምንም ልዩነት የላቸውም።
ቀኑ መሄዱን ብቻ ነው ምፈልገው።
እንዴት እንደሆነ አላቅም ግን ውስጤ አስር አመት ሙሉ እስር ቤት እንደማላሳልፍ ይነግረኛል።
ነገሮች በቶሎ ተስተካክለው ነፃ እንደምሆን ከዛ ውጭ ላይ የእዮብን ገዳዮች ገድዬ በዛውም እናቴን ያሳጣችኝን ፋኖስን ተበቅዬ ተመልሼ እስር ቤት ከመግባቴ በፊት እራሴን አጥፍቼ እንደምገላገል እቅዴን አውጥቼ ከጨረስኩ ሰነባብቻለሁ እድል ፊቷን ወደኔ እስክታዞር መታገስ ነው.......

🔻ክፍል  33 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

5.8k 0 18 5 160

5 min 👍


❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  31

ሁኔታዎች ተደግመው ይሁን ወይ እስካሁን የሰማሁት ቅዠት አላቅም ብቻ መቀበል ያልፈለኩት የሆነ ነገር አለ።

ወዲያው የቅድሙ ዶክተር ተመልሶ ገባና ውስጥህ ልክ አደለም በጣም የሀይል እጥረት አለብህ እራስህን አትንከባከብም እንዴ ???
ለማንኛውም አሁን መውጣት ትችላለህ አለኝ።
ተነስቼ ወጣሁ።
በሰአቱ ሆስፒታሉንም ፖሊሶችንም እራሴንም በእሳት ማንደድ ብችል ደስ ይለኝ ነበር።
ተመልሼ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ገባሁ ማረፊያ ክፍል አስገቡኝ።
ቁጭ አልኩ ከራሴጋ ማውራት ጀመርኩ ባህራን ንቃ ትናት እናትህን ቀበርክ ዛሬ ደሞ አንድ ከጎንህ የነበረውን እዮብን ገደልክ ተብለህ ተከሰስክ ማለትም እዮብ ሞቷል ገለውታል እነዛ የክለብ ጠባቂዎቹ እዮብን ቀጥቅጠው ገለውታል ንቃ በቃ እዮብም ሞቷል አሁን አንተ ደሞ እስር ቤት ልትበሰብስ ነው ማንም ስላንተ ግድ አይሰጠውም ማንም አንተን አያስታውስህም እያልኩ ከራሴጋ አውራሁ።

በሰአቱ ልእልትጋ ማስደወል እሷን ማግኘት ፈልጌ ነበር ግን ድጋሜ ለሷ ችግርን ማሸከም አልፈለኩም ለኔ ስትል ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ስትንከራተት ትምህርቷን ቤተሰቦቿን ስትተው ስትሰቃይ ማየት በራሱ ለኔ ሌላ ሞት ነው።
እዛጋ የኔ ህይወት ያበቃለት ነገር ሆኖ ሳለ ድጋሜ እሷንም መረበሹ እኔንም እረበሸኝ።


......ነገሮች እንደቀልድ እየተፋጠኑ ሄዱ።
እዮብን በመግደሌ ሞተብን ብሎ የመጣ ቤተሰብ የለም ከሳሽ የለኝም ።
ፍርድ ቤቱ ብዙ ነገሮችን ከመረመረ ቡሀላ እዮብ በጣም ብዙ ህመም የነበረበት ሰው እንደሆነና  ለመኖር ቢበዛ 6 ወር ብቻ የቀረው ሰው እንደነበር አጣሩ።
በዛም እኔ እሱን በጣም ባልደበድበው እንኳን በራሱ አቅም ማጣት ጉዳቱ ከፍ እንዳለበትና ሁለታችንም በሰአቱ ከመጠን በላይ ጠጥተን መስከራችን ብቻ .... ብዙ ብዙ ማስረጃዎች ከታዩ ቡሀላ እኔ የአስር አመት እስራት ተፈረደብኝ።

ከቀናቶች ቡሀላ ወደ ዘዋይ ተላኩኝ።
እዛ የእስር ጊዜ ሀ ተብሎ ተጀመረ።

እስር ቤት ውስጥ ሁሉም የየራሱ ቡድን አለው።
ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ያለው ፀብ ውጭ ላይ እራሱ በዛ ልክ ያለ አይመስለኝም።
ሁሉም እራሱን ክብሮ ለማድረግ ይሯሯጣል።
አንዱ በድንገት ብቻውን ከታየና ሲናገሩት መልስ ካልሰጠ ያ ሰው መጫወቻ ሆኖ ነው ሚቀረው።
እኔ እዛ እስር ቤት በገባሁበት ሰአት ልቤ በቀልን ተሸክሞ ሞት ናፍቆኝ ነበር።
ምንም ቢፈጠር የሚያስፈራኝም ሆነ ወደኋላ ሚመልሰኝ ምንም ነገር የለም  ከፊት ለፊቴ አስር ሰዎች ሊደበድቡኝ ቢመጡ ወደኋላ ምልበት ምክንያት የለኝም ዝም ብዬ ያገኘሁት ላይ መሰንዘር ደም ማየት የሆነ ሰው ወድቆ እያቃሰተ መመልከት ብቻ ነው ሰላም ሚሰጠኝ።

የመጀመሪያ በገባሁ ሳምንታቶቹ ውስጥ ከጀርባዬ ሁለት ቦታ ተወጋሁ ግን አልሞትኩም።
በድጋሜ ወር ሳይሞላኝ ሆዴ ላይ ሌላ ጩቤ ተሰካብኝ የዛኔም አልሞትኩም
እስር ቤት ውስጥ እየቆየሁ በሄድኩና ከሰዎችጋ በተጣላሁ ቁጥር ውስጤ ያለው ሴጣን እየባሰበት ጭካኔዬ እየበረታ ከሰዎችጋ ለምን አየኸኝ ብሎ መጣላት ሆነ ስራዬ።

ከታሳሪዎቹ ውስጥ አንድም ጠያቂ የሌለኝ ብቸኛው ሰው እኔ ሳልሆን አልቀርም።
ሁሉም በየቀኑ ሚመጣላቸው ምግብ ልብስ ብር እንደጉድ ነው።
ብዙ ጠያቂ ያላቸው ታሳሪዎች የመወደድና የመፈለግ እድላቸው ሰፊ ነው ምክንያቱም እስር ቤት ውስጥ ምግብ ለብቻ አይበላም ልብስም ብዙዎቹ ለጋራ ነው ሚጠቀሙት።
ለምሳሌ አንድ እኛ ክፍል ውስጥ ታስሮ የነበረ አንድ ሰው የመፈቻ ጊዜው ቢደርስ ከለበሰው ልብስ ውጭ ልብስ ይዞ አይወጣም ይዞ ከወጣ እንደፋራ ነው ሚታየው።


🔻ክፍል  32 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

7.8k 0 22 31 215

❤️ የፍቅር ጥግ ❤️


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

                        ክፍል  30

ምን እያወራና እየቀባጠረ እንደሆነ ግራ ገባኝ።
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ስለምን እያወራ እንደሆነ ጠየኩት።
ተረጋግቼ እንድቀመጥና አጉል ማስመሰሉ እንደማይጠቅመኝ ነገረኝ።
የዛኔ ነገሮች ከአቅሜ በላይ ሆኑብኝ ለመረዳት ተቸገርኩ በትክክል እዛጋ የነበረው ችግር ምን እንደሆነ አልገባ አለኝ።

ተረጋግቼ ቁጭ አልኩና ይቅርታ አለቃ እሺ አሁን እየተፈጠረ ያለውንና ለማለት የፈለከውን ቀስ ብለህ አስረዳኝ ምክንያቱም እኔ ለምን እዚህ እንደመጣሁ እራሱ አላቅም አንተ እንደ ጠያቂ ነገሮችን ግልፅ አድርግልኝ አልኩት።

ጥሩ አውርቼ እስክጨርስ እንዳትተነፍስ ምን እንደተፈጠረ በቅደም ተከተል ላስረዳህ ላንተ ምታቀውን ነገር መድገም ቢሆንም ግን የስራ ግዴታዬ ስለሆነ ልንገርህ አለኝ።

እያዳመጥኩ እንደሆነ ገለፅኩለት።

ትናት አንተ ወደክለብ ለመዝናናት አምርተህ ነበር አደል??
እና ክለብ ውስጥ በምትሰራ አንዲት ሴተኛ አዳሪ የተነሳ አንተና አንድ ሰው ግጭት ውስጥ ገባችሁ።
መጣላት ጀመራችሁ ሀይለኛ ፀብ ውስጥ ስትገቡ ወደ ውጭ ወጥታችሁ በግል መደባደብ ጀመራችሁ ።
ሁለታችሁም ተጎድታችሁ እራሳችሁን ስታችሁ ወደቃችሁ እሱ በዛው ሞተ አንተ ደሞ ሀኪም ቤት ሄደህ ነቃህ  አለኝ።

ዝም ብዬ አየሁት የሟችን ፎቶ ማየት እችላለሁ??? ብዬ ጠየኩት
ስልኩን አውጥቶ አሳየኝ ሟቹ እዮብ ነው።

አንዳንዴ ነገሮች ተፈጥረው ግን በትክክል ያንን አምነን መቀበል ሚያቅተን ሰአት አለ።
በሰአቱ እየተሰማኝ የነበረው ስሜት ምን እንደሆነ በትክክል ባላውቅም ከፊት ለፊቴ ተቀምጦ የነበረውን ሰው ግን በጥርሴ በጣጥሼ ብጥለው ሁላ እርካታ እንደማይሰማኝ ጠንቅቄ አቃለሁ።

መጮህ ጀመርኩ እዮብ ጓደኛዬኮ ነው እሱ ላይ ጨክኜ እጄን ማንሳት እራሱ አልችልም ንገረኝ ምንድነው የተፈጠረው ንገረኝ ሞተ ማለት ምን ማለት ነው።
ብዬ በሀይል መጮህ ጀመርኩ እየጮኩ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ እየደከመኝና መናገር እያቃተኝ መጣ ።
ከዛ ቡሀላ በድጋሜ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ እራሴን ሀኪም ቤት አገኘሁት


🔻ክፍል  31 ነገ ማታ 2:30  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።


      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
 💔
@MELKAM_LBOCH13 💔
💔 
@MELKAM_LBOCH13 💔

➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33

7.8k 0 22 17 206

እናንተ ከምትከፉብኝ 1 ፓርት ልጨምር😘


ትንሽ ጠብቁኝ
!

Показано 20 последних публикаций.