በልማት ሰበብ የሚደረግ የቤት ማስለቀቅ ዘመቻ የማህበረሰቡን መብት ያማከለ መሆን ይገባዋል ሲሉ ፓርቲዎች አስታወቁ
ፓርቲዎቹ አሻራ የሚቀመጠው ታሪክን በመደምሰስ እና በሕዝብ ሰቆቃ ላይ አይደለም ብለዋል
እናት ፓርቲ ፣የኢትዮጵያ ህዝቦች ለአብዮታዊ ፓርቲ ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ እየተደረገ ያለው በልማት ሰበብ የሚደረግ ፈረሳ የብዙ ሺ ሰዎችን ህይወት እያመሰቃቀለ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ በመጀመሪያ የወንዝ ዳር ልማትና የጫካ ፕሮጀክት በሚል ተጀምሮ አሁን የኮሊደር ልማት በሚል መጠኑን እና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው አሻራ በማሳረፍ ሰበብ የመቶ ሺዎችን ህይወት እንዳመሰቃቀለ እና ባስ ሲልም ለሞት እንደዳረገ አስታውቀዋል፡፡
ፓርቲዎቹ አደረግን ባሉት ማጣራት ቤታቸው የፈረሰባቸው እና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ህመም የተዳረጉ፣ ስራቸው የተቋረጠ እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በድንጋጤ የሞቱ ሰዎች ስለመኖራቸው ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ የበለጠ ማማር እና መዘመን እንዳለባት ሁሉም የሚቀበል ቢሆንም ከተማው የኛ አሻራ የለበትም በሚል የማፍረሻ ምክንያት እየፈለጉ ነዋሪውን ማፈናቀል ተቀባይነት የለውም ሲሉ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት በህገመንግስት የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብር እና “በልማት ሽፋን ከሚደረግ ደባ” እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡
#አዲስማለዳ