Meribah Times - መሪባ ታይምስ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በአገራችንና ቀጠናችን ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን በዚህ ቴሌግራም ገፅ እንጋራለን !!!
This channel provides political, economical and social information, analysis on Ethiopia and the horn of Africa!!!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




መልካም ዜና

#ቲክቶክ ከቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳነት ትራምፕ በተሰጠው ዋስትና ወደ አገልግሎት ለጊዜው መመለሱን አስታወቀ።

#UnitedStates #SocialMedia #TiktokBan #China #DonaldTrump


#ታላቅ_የምሥራች_ከወደ_ፌዴራል_ከፍተኛ_ፍርድ_ቤት

እናት ፓርቲ የመሠረተውን ክስ በተመለከተ!
***
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር "ሕገ ወጥ መኾኑን" በመግለጽ እናት ፓርቲ ክስ መመሥረቱ ይታወሳል። ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ዛሬ ጥር ፱ ቀን  ፳፻፲፯ ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ ሚያዝያ ፫ ቀን ፳፻፲፭ የወጣውና "ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ መወሰኑን እናት ፓርቲ ለመላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉ ለነበሩ ፍትሕ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በደስታ ይገልጻል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥር ፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


ልባቸውን ጨምሮ ከወገባቸው በታች ተጣብቀው የተወለዱት አሜሪካዊ ጥንዶች ማርገዛቸው  እየተነገረ ነው።

እነዚሁ አንድ ማህፀን ያላቸው አቢ እና ብሪቲና ሂንሲል ከአንድ ወር በኋላ 35ኛ እድሜያቸውን የሚያከብሩት ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች "ልጅ ለማግኘት መንገድ ላይ ነን" ሲሉ በቲክቶክ ላይ ያጋሩ ሲሆን 'ሳያረግዙ አልቀረም' የሚል ግምት በስፋት እየተናፈሰ ይገኛል።

** የሚወልዱት ልጅ እናቱ ማን ልትሆን ነው? የሚል ድንገትም አዲስ ህግ የሚያስፈልገው ጥያቄም አስነስቷል።
ምንጩ ፊደል ነው።


Erasmus Mundus GOALS Scholarship 2025/27 in Europe 🇪🇺 (Fully Funded)

2 Year Master Degree Program Prepared by Five Universities in France, Portugal, Lithuania, Luxembourg, and Poland.

The Scholarship Covers Airfare, Meals, Accommodation, Visa, Tuition, Insurance, Allowance.

Visit: https://opportunitiescorners.com/erasmus-mundus-goals-scholarship/

Deadline: 16th February 2025

@MeribahTimes


"የመንግስት አካላት ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ጥሰቶቹ  እንደቀጠሉ ይገኛሉ"- ኢሰመጉ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በተደረገ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት፣አረጋውያን እና ሴቶች በታጠቁ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

ምርመራው የተደረገው ከታህሳስ 7ቀን2016 እስከ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሚገኙ 20 ቀበሌዎች በተፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች የንጹሀን ህይወት ማለፉን ለማወቅ መቻሉን ኢሰመጉ ገልጿል።

ይህን ተከትሎም የፌደራል እና የኦሮምያ ክልል መንግስታት በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የመጡትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቂ ትኩረት በመስጠት የህዝቡ ሰላም ተጠብቆለት የመኖር መብቱን እንዲያስከብሩ አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም በኦሮምያ ክልል በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች የፌደራልና የኦሮምያ ክልል መንግስታት የጸጥታ አካላት ጥቃቶች ሳይደርሱ ቅድመ የመከላከል ስራን መስራት፣ ተፈጽመው ሲገኙም አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ስራን በትኩረት በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል፡፡

@MeribahTimes


የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ከ #አየር መንገድ
-------
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ሙያ መስክ የስራ ቅጥር አውጥቷል።


መወዳደር የምትፈልጉ ዝርሩን በተከታዩ የአየር መንገዱ ሊንክ ታገኛላችሁ 👇

https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

#ኢትዮጵያ
#ET
@MeribahTimes


የስራ ማስታወቂያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ
------

በበረራ አስተናጋጅነት ጀማሪ ሰራተኞችን ለመቅጠር አየር መንገድ ማስታወቂያ አውጥቷል።


ዝርዝሩ በፎቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለተጨማሪ ግን ይህን ሊንክ ይጠቀሙ 👇👇

https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies#collapsetwo_6

@MeribahTimes


የስራ ማስታወቂያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ
------

በበረራ አስተናጋጅነት ጀማሪ ሰራተኞችን ለመቅጠር አየር መንገድ ማስታወቂያ አውጥቷል።


ዝርዝሩ በፎቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለተጨማሪ ግን ይህን ሊንክ ይጠቀሙ 👇👇

https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies#collapsetwo_6

@MeribahTimes


በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ መጠየቁ ተገለጸ

በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ገለጹ።የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ለአሜሪካ ድምጽ እንደገለጹት የብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተያይዞ ቋሚ ደመወዝ የሚያገኙ ሰራተኞች ለከፍተኛ የኑሮ ፈተና እየተዳረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"በተለይም ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኘው ሰራተኛ ቀን ቀን እየሠራ ማታ ማታ ሆቴሎች ላይ ፍርፋሪ እየለመነ እያደረ ነው።" ያሉት ፕሬዝዳንቱ የኑሮ ጫናው በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያያለ መሆኑን ጠቁመዋል።

አክለውም ከዚህ በፊት በሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ ዙርያ ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ጋር ተደጋጋሚ  ውይይቶች መደረጋቸውን አስታውሰው ነገር ግን እነዚህ ውይይቶች ይበል የሚያሰኝ ውጤት አለማስገኘታቸውን ተናግረዋል።በመሆኑም የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ሌሎች የኑሮ ፈተናውን ሊያቀሉ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚንስትሩን በድጋሚ በደብዳቤ መጠየቃቸውን አመላክተዋል።

Via Addis Standard

@MeribahTimes


የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች ሸማቾች ማህበር በሶስት መደብ የሰራተኛ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል ።

ገንዘብ ያዥ ፣ አካውንታት እና ሽያጭ

ዝርዝሩን ፎቶው ላይ ይመልከቱ ☝️☝️


ትራምኘ እና የስደተኞች ጉዳይ

ፕሬዝዳንት ትረምፕ ከመመረጡ ቀናቶች በፊት፤ ትረምፕ ሊመረጥ እንደሚችል እና የኢምግሬሽን ጉዳዮችን አስመልክቶ በጣም ጥብቅ እርምጃዎችን እንደሚወስድ፤ በዚህም ኢትዮጵያኖች ጭምር ተጠቂ እንደሚሆኑ ገልጬ ነበር።

ፕሬዝዳት ትረምፕ ቶም ሆማንን በኢምግሬሽን እና ቦርደር ጉዳዮች በመሾም የዲፖርቴሽን እቅዱ ሲሪየስ እንደሆነ አሳይቷል። ቶም ሆማን በመጀመሪያዎቹ 90 ቀናት ውስጥ ብቻ ብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ዲፖርት ማድረግ እንደሚቻል እና ያንንም ለመፈጸም ሚሊተሪውን ጭምር እንደሚጠቀም ገልጿል። ይሄም ማለት በየሆቴሎቹ የICE ኦፊሰሮች በድንገት እየገቡ መፈተሽ፣ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታዎች ድንገተኛ ፍተሻ እና ማጣራቶችን በማድረግ፤ የቪዛ ጊዜያቸውን የተላለፉ ሰዎችን ጨምሮ ዶክመንት የሌላቸውን ሰዎች በማሰር ዲፖርት ማድረግ የቶም ሆም ተልዕኮ ይሆናል።

ኢትዮጵያኖች ምን ያድርጉ፤

1) በተለይ የቪዛ ጊዜያችሁን ተላልፋችሁ በአሜሪካ ያላችሁ ሰዎች በፍጥነት ወደ ሕጋዊ ስታተስ ራሳችሁን መቀየር። ለምሳሌ አሳይለም ፋይል ካላደረጋችሁ ፥ ፋይል ማድረግ፤

2) የአሳይለም ሂደታችሁ በፍርድ ቤት  እየተከታተላችሁ ያላችሁ ፥ የፍርድ ቤት ቀጠሮአችሁን በአግባቡ መከታተል። ከጠበቆቻችሁ ጋር በቅርበት መስራት፤

3) ያለሥራ ፈቃድ በካሽ የምትሠሩ ሰዎች ይሄ ከፍተኛ አደጋ ሊጥልባችሁ እንደሚችል ማወቅ እና ጥንቃቄ ማድረግ፤

4) በመጨረሻም ሁልጊዜ ዜናዎችን፣ በኢምግሬሽን ጉዳዮች ያሉ መረጃዎችን መከታተል እና ማድረግ የሚገቡንን ጥንቃቄዎች ዘወትር ማድረግ።

ሙሉአለም ጌታቸው

@MeribahTimes




በመንግስት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው”- ኢሕአፓ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ “የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት ቢሆንም በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ህይወት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል” ብሏል፡፡

ኢሕአፓ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህገመንግሥቱን የመንግሥት አካላት ራሳቸው ካላከበሩት እንዴት ሊያስከብሩት ይችላሉ “በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደረጉት ግድያዎች ይቁሙ” ሲል አሳስቧል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከመዘገብ ቢቆጠቡም በውጪ የመገናኛ ብዙሀን ጭምር ጥቃቱ መፈጸሙን እየገለጹ መሆኑን እና ፓርቲውም አጣርቻለሁ ያለውን በየክልሉ የደረሱትን ጥቃቶች አስታውቋል፡፡

ፓርቲው አጣርቻለው ባለው መሰረት ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች የሟቾችን ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን እና ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥም ነፍሰጡሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት አመላክቷል፡፡

በመሆኑም  “ወደፊት ትውልድ እንዲከፍል በብድር በመጣ የጦር መሳሪያ ንጹሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄድ አግባብነት የለውም”፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ለማለት እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በዝምታ ማስቀጠል አይችልም ሲል ኮንኗል፡፡

ኢሕአፓ  መንግሥት በተለይ የጦርነት አውድማ በተደረጉት በአማራ፣በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝና በደቡብ ክልሎች ዉስጥ የሚደረገውን ህገመንግሥቱን እየጣሱ ያሉትን፣ መንግሥት መር የዜጎች ግድያዎችን በጥብቅ ማውገዙን እና  ጦርነቶቹ አሁኑኑ ይቁሙ ሲልም አሳስቧል፡፡

@MeribahTimes


Репост из: ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
ህዝቡ በጣም ገቢው አድጎ ስለበለፀገ አምና በሳንቲሞች ይጨምር የነበረው የትራንስፖርት ዋጋ አሁን እስከ እጥፍ በሚሆን ጭማሪ አሳይቷል...

የመዓት ግዜ!

@EliasMeseret


በልማት ሰበብ የሚደረግ የቤት ማስለቀቅ ዘመቻ የማህበረሰቡን መብት ያማከለ መሆን ይገባዋል ሲሉ ፓርቲዎች አስታወቁ

ፓርቲዎቹ አሻራ የሚቀመጠው ታሪክን በመደምሰስ እና በሕዝብ ሰቆቃ ላይ አይደለም ብለዋል

እናት ፓርቲ ፣የኢትዮጵያ ህዝቦች ለአብዮታዊ ፓርቲ ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ እየተደረገ ያለው በልማት ሰበብ የሚደረግ ፈረሳ የብዙ ሺ ሰዎችን ህይወት እያመሰቃቀለ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ በመጀመሪያ የወንዝ ዳር ልማትና የጫካ ፕሮጀክት በሚል ተጀምሮ አሁን የኮሊደር ልማት በሚል መጠኑን እና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው አሻራ በማሳረፍ ሰበብ የመቶ ሺዎችን ህይወት እንዳመሰቃቀለ እና ባስ ሲልም ለሞት እንደዳረገ አስታውቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ አደረግን ባሉት ማጣራት ቤታቸው የፈረሰባቸው እና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ህመም የተዳረጉ፣ ስራቸው የተቋረጠ እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በድንጋጤ የሞቱ ሰዎች ስለመኖራቸው ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ የበለጠ ማማር እና መዘመን እንዳለባት ሁሉም የሚቀበል ቢሆንም ከተማው የኛ አሻራ የለበትም በሚል የማፍረሻ ምክንያት እየፈለጉ ነዋሪውን ማፈናቀል ተቀባይነት የለውም ሲሉ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም መንግስት በህገመንግስት የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብር እና “በልማት ሽፋን ከሚደረግ ደባ” እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡

#አዲስማለዳ


ኢሕአፓ፣ የአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት “ሕዝባዊ ቁጣ" ሊቀሰቅስ ይችላል ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።

የኮሪደር ልማቱ የነዋሪዎችን “ሰብዓዊ መብቶች የጣሰ" መኾኑን የጠቀሰው ኢሕአፓ፣ የከተማዋ ልማትና ዕድገት ከነዋሪው "መብት መከበር” እና “ከጥቅሞቹ መጠበቅ” በተነጠለ ኹኔታ ሊታይ እንደማይገባ ገልጧል።

የኮርደር ልማቱ፣ የበርካታ ነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች፣ አነስተኛ እና ከፍተኛ የንግድ መደብሮች ማፍረሱን ኢሕአፓ በመግለጫው ጠቅሷል።

ፓርቲው፣ የከተማዋ አስተዳደር ድርጊቶች፣ የነዋሪዎችን "ኹኔታ ያላገነዘቡ" እና ምቹ ጊዜን ያልጠበቁ” ናቸው በማለትም ወቅሷል።

#ዋዜማ


Репост из: Meseret Media
የሚኖርበት ቤት ለልማት በሚል የፈረሰበት እና ስራ እንዳይሰራ የተከለከለ ወጣት ራሱን አጠፋ

(መሠረት ሚድያ)- ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ የሆነ አዲሱ ካሳሁን የተባለ ወጣት ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ አካባቢ በሚገኘው 'በፀጋህ ሆስፒታል' ፊት ለፊት ነዋሪ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ራሱን አጥፍቷል።

አዲሱ ነጠላ ከሚሸጥበት ኡራኤል ቤተከርስቲያን አካባቢ ስራ እንዳይሰራ ሁለት ግዜ በደንብ አስከባሪዎች ተባሮ እና ንብረቱም ተወስዶበት እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቅርብ ሰው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከትናንት በስቲያ ምሽት ማታ ወደ ቤቱ ሲገባ የሚኖርበት ቤት በነጋታው ጠዋት እንደሚፈርስ ሲነገረው ተስፋ በመቁረጥ ስሜት እዛው ቤቱ ውስጥ ራሱን እንዳጠፋ ለመሠረት ሚድያ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰው ጥቆማ ያሳያል።

የልጅ አባት የሆነው እና በቅርቡ የወለደች ባለቤት ያለው ወጣቱ ይህን ድርጊት ከፈፀመ በኋላ ትናንት ስድስት ሰአት ላይ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ቀብሩ እንደተፈፀመ ሰምተናል።

መሠረት ሚድያ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ይመኛል።

መሠረት ሚድያ- የህዝብ ድምፅ!

@MeseretMedia


አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የድህረ ምረቃ ትምህርት ምዝገባውን ዛሬ ያጠናቅቃል 👇👇👇

Addis Ababa University has extended the application for admission until Friday October 11, 2024.  Please continue to fill out the application form on the university portal (https://portal.aau.edu.et) and submit your documents in person to #203 of the Registrar office.


አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርት የቅበላ ማመልከቻ ድረ-ገጹን እስከ ጥቅምት 1, 2017 ድረስ ለአመልካቾች ክፍት ማድረጉን እናሳውቃለን:

Application Guide for Graduate Programs for the 2024/25 Academic Year

1. If you apply on female and disability scholarship, you need to check the department-level admission requirements on the following link:
http://admission.aau.edu.et/GraduateProgramsOnly Additionally, your CGPA should be 2.75.

2. If you choose the sponsor type as either MOE or Government make sure to attach your sponsorship letter and bring the original sponsorship letter in person along with your credentials.

3. Note that the GAT exam is valid only from 13/9/2024 onwards. GAT exam before the date mentioned above or NGAT exam is not
acceptable.
@addisababauniversityofficial

https://t.me/MeribahTimes


Репост из: Asham TV

Показано 20 последних публикаций.