የኦሮሚያው ባለስልጣን ተገደሉ ‼️
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሱሉልታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አበበ ወርቁ እና የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ነጋሽ ድሪባ፣ አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዛሬ ከቀትር በኋላ በፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት መገደላቸውን ተሰማ።
። የቡድኑ ታጣቂዎች ድንገተኛ ተኩስ የከፈቱት፣ ዋና አስተዳዳሪው፣ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊና በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላት ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀስበታል ወደሚባለው 'ሞዬ ጋጆ' በተባለ ሥፍራ ላይ ሲደርሱ እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹን በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላትን አፍነው እንደወሰዱም ምንጮች ጠቁመዋል።
ቁጥራቸው ያልታወቀ የጸጥታ ኃይል አባላት በጥቃቱ ሲገደሉ፣ በርካቶች ደሞ ቆስለው ጫንጮ ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል። አበበ ከኹለት ዓመት በፊት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ኾነው ከመሾማቸው በፊት፣ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነበሩ።
ዋዜማ